✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል ሁለት [፪]
በዚህ በወርኃ ጽጌ ( በዘመነ ጽጌ ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾመ ጽጌ መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም ነው።ወይም የትሩፋትጾም ይባላል።በቀኖና ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል።
ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ "እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል።ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።"ሉቃ፯፥፵፯ የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስየለባቸውም።የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው።
ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው።"ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ"ማቴ፮፥፲፮ የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡
ጽጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ምድሪቱ በአበባ የምትሞላበት ጊዜ በመሆኑ አበው ሊቃውንት እመቤታችንን በብዙ ኅብር መስለዋታል፡፡ በአበባ /ጽጌ/፣ በወይን ሐረግ፣መልካሙን የወይን ፍሬ አስገኝታለችና አበባ ፍሬን እንዲያስገኝ ድንግል ማርያምም ለሰው ያልተቻለውንና የማይቻለውን አንዴ ብቻ የሆነውን መለኮትን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት በማህፀንዋ ወሰነችው።
አዳምና ልጆቹ እንዳይበላ በተከለከለችዋፍሬ ምክንያት ገነትን ከሚመስል ቦታ እግዚአብሔርን ከሚያክል ጌታ ተለዩ የሰው ልጅ ድቀት ተጀመረ ሁሉን አጣ የመጀመሪያ በደል/ጥንተ አብሶ/ ማለት ይህ ነው።
የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የመለየትን ረጅም ግዜን ገፋ ገዥ የነበረው የሰው ልጅተፈጥሮ ሰለጠነበት፣ ጠላት በዛበት፣ ምድሪቱ ከፋችበት አዳምም ባለቀሰው መሪር እንባ 5500 ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህተወልጄ አድንሐልሁ የሚል ተስፋ ተሰጠው የህይወት ፍሬንም ዳግም እንዳይበላ በሱራፊ ታጠረችበት።
ይህም የሚያመላክተው ሞትን የምታመጣ ዕፀ በለስን የበላ አዳም ደግሞ ዕፀ ህይወት ቢበላ ኖሮ ካሳ የማያስፈልገው ኢመዋቲ(immortal sinner) እንዳይሆን የእግዚአብሔር ቸርነት ከለከለችው፡፡
ያ የጨለማ ዘመን ፍጹም ተስፋ ያልጠፋበት ፍጹምም ተስፋ ያልተፈጸመበት ዘመን ነበር።እግዚአብሔር ከአዳም ጀምሮ ለአርእስተ አበው ቃል ኪዳን ይገባ ነበር።
በዚህም ቃል ኪዳን ውስጥ እመቤታችን በተስፋ አበው ውስጥ ታልፍ ነበረ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በድጓ "ማርያምሰ ተሐቱውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባህርይ ጸአዳ ፤ ማርያምም በአዳም አብራክ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራ ነበር"በማለት ቅ ገልጦአታል።
ነገር ግን የአበው ተስፋ፣ የነቢያት ትንቢትሲፈፀም የድንግል ማርያም የህይወት ፍሬ/በገነት ተከልክላ የነበረችው የገነት ፍሬ/ አማናዊው ጌታ የሚበላ የሕይወት ፍሬ ሆኖ ከእመቤታችን ተወለደ ቅዱስ ኤፍሬም በሐሙስ ውዳሴ ማርያም ሲናገር " ከፈለነ ንብላዕ እምዕጸ ሕይወት ዘውዕቱ ሥጋሁ ለክርስቶስ ወደሙ ክቡር በእንተ ፍቅረ ዚአነ መጸአ ወአድኅነነ ፤ ዳግመኛ ከዕፀ ኅይወት እንበላ ዘንድ አደለን ይኸውም እኛን ስለመውደድ ሰው ሆኖ ያዳነን የክርስቶስ ክቡር ሥጋው ክቡር ደሙ ነው "በማለት እንደገለጸው፡፡
በወርኃ ጽጌ እመቤታችን ጌታን በጀርባዋአዝላ በረኀ ለበረሃ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር የተሰደደችበትን ሙሉ ታሪክ በጥልቀት ስንመለከት ፡፡
ከላይ በርእሱ የተጠቀሰውን ቃል ልጄን ከግብፅ ጠራሁት።ትሆሴዕ፲፩፥፩
የሚለውን የትንቢት ቃል የተናገረው ከክርሰቶስ ልደት በፊት በስምንተኛው ምእተ ዓመት አጋማሽ ገደማ የነበረው የብኤሪ ልጅ ነቢዩ ሆሴዕ ነው ። ሆሴዕ ማለት እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪኳ ከተዘረዘሩላት ሀገሮች መካከል ግብጽ አንዷ ስትሆን ግብጽ የብዙኀን አባት አብርሃም በረሃብ ምክንያት የተሰደደባት፣ ዮሴፍ በባርነት የተሸጠባት፣ ወገኖቹ እስራኤላውያን ለሁለት መቶ አስራ አምስት ዓመታት ያህል በባርነት የተገዙባት በኋላም የአለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር የተሰደደባት ሀገር ስትሆን መሪዎቿም አህዛብ አማልዕክቷም ጣኦታት ነበሩ።
ነቢዩ ሆሴዕ የጌታችንን ሥደት ቀድሞ በትንቢት ከተናገሩት ውስጥ አንዱ ሲሆን ልጄን ከግብፅ ጠራሁት በማለት የስደቱን ማብቃት ተናግሯል።
በዚህ ትንቢት መሰረት መሰደዱን አልተነበየም።ነገር ግን ከስደት መመለሱን መናገሩ ካልተሰደደ መመለስ የለም በመመለሱመሰደዱን ተናገረ።
የጌታን ሕይወት ከእመቤታችን የእመቤታችንን ከጌታ ለያይቶ ማየት አይቻልም መለኮታዊ ተግባራትን እና የማዳን ስራዎችን ካልሆነ በቀር ምክንያቱም ለእርሱ ብቻ የተወሰነና ሊያደርገው የተገባ የአባቱ ተልዕኮ ስለነበረ "ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም አንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁ"ዮሐ፮፥፴፰ ፣ ዮሐ ፭፥፴።
ነቢያት የተነበዩት ጊዜ ደርሶ በነቢዩ በሆሴዕ እንዳለውና መልአኩ ገብርኤል ለዮሴፍ ተገልጦ እንደነገረው አንድ ልጇን ይዛ ወደ ግብጹ ተሰደደች ማቴ ፪፥፲፫
1⃣የእመቤታችንና የልጅዋ ምክንያተ ስደት ወደ ምድረ ግብጽ
ክፍል ሦስት ይቀጥላል....
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem