✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል አራት [፬]
ለ.ጣኦታተ ግብጽን ለማጥፋትና ለመደምሰስ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደዱ
ግብጽ ከነገሥታቶቿ ጀምሮ ጣኦትን የሚያመልኩ አህዛብ የነበሩ ህዝቦች ነበሩ፡፡እነዚህ ጣኦታት ደግሞ የበሬ፣ የላም፣ የአንበሳ፣ የወፍ ምስል አስቀርጸው ያመልኩ ስለነበር ለዚህም ከሙሴና ከአሮን ጸሎት የተነሳ የግብጻውያን የእጃቸው ሥራ መጥፋቱን፣ እግዚአብሔር በናቡከደነጾር አድሮ ወደ ግብጽ መምጣቱን፣ ጣዖታትን ማጥፋቱን የተነበየበት ከመሆኑ በላይ በዘባነ ማርያም ኅዙል /በማርያም ጀርባ ታዝሎ/ በፈጣን ደመና በተመሰለች ከእመቤታችን ጋር ወደ ግብጽ ተሰዳለች፡፡ሊቃውንት እመቤታችንን ሲመስሏት ደመና ኢሳይያስ የሚሏትም ስለዚህ ነው፡፡በዚህ ትንቢት ላይ እንደተገለጸው ግብጽ በጣዖታት የተሞላች በመሆኗ የጌታችን ስደት በግብጽ ያሉ ጣዖታትን ለማጥፋት እንዲሆን ተጠቅሷል።
ግብጻውያን ከጥንት ጀምሮ በማስመሰል ደንጊያ ጠርበው እንጨት አለዝበው ማዕድን አቅልጠው የእንስሳትን ምስል የላም፣ የፍየል፣ የአንበሳ የወፍ ምስልን በመቅረጽ ያመልኩ ስለነበር ከተማዋ በጣኦታት የተሞላች ነበር ፡፡
እነዚህን ለማጥፋት የጌታ ስደት ወደ ግብጽ ይሆን ዘንድ ትንቢት አናገረ።ጌታችን ጣኦታትን ሊያፈርስ ወደ ግብጽ ተሰደደ ገና ከተማዋ ሲገባ በጣኦታቱ ላይ ያደሩ አጋንንት ይጮሁ ጣኦታቱም ይሰባበሩ ጀመር ። ከዚህም ባሻገር በኛ ሕይወትም ውስጥ ጌታን ለመቀበል ጌታ ስራ እንዲሰራብን በቅድስና ለመኖር የልብን ጣዖታት ማጥፋት ማጽዳት ይገባል።
አልያ ጌታንና ጣዖትን በልባችን ማኖር አንችልም ቅዱስ ጳውሎስ "መኑ ደመሮ ለብርሃን ምስለ ጽልመት" "ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር መስማማት አለው ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው።እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና፡፡ያለው ለዚሁ ነው፡፡
ቅዱስ ዳዊት፡- መዝ፹፫፥፫ "ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች ዋኖስም ጫጭቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች።" በማለት ሲተነብይ ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች ሲል ነቢያት የተነበዩት ፍጻሜውን በእመቤታችን ማግኘቱን አንድም እመቤታችን በስደት ግብጽ መኖርያዋ ማድረጓንዋኖስም ጫጭቶችዋን የምታኖርበትሲል ዮሴፍና ሰሎሜም የሚኖሩበት ቤት ማግኘታቸውን ተናገረ።
ለእመቤታችን ማደሪያ ጠፍቶ ማደሪያዋንግብጽ ማድረጓን ተንብየዋል፡፡ነቢዩ ሆሴዕ፡- "እስራኤል ሕጻን በነበረ ጊዜ ወደድኩት ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት" ሆሴ ፲፩፥፩
እስራኤል በግብጽ ሳሉ እንደተመረጡ ከ፤ዚያም አገር አውጥቶ መንግስት ይሆኑ ዘንድ እንዳበቃቸው የተናገረበት ትንቢት ከመሆንና፥ ጋር የጌታችን ወደ ግብጽ መሰደድ ሔሮድስ እስኪሞት በዚያ መቀመጡን ከዚያም መመለሱን የሚያመለክት መሆኑን ቅዱስ ማቴዎስ የነቢዩን ቃል ፍጻሜአድርጎተናግሯል። ማቴ ፪፥፲፭
ሐ ሰው መሆኑን ለመግለጽ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደደ
ኢየሱስ ክርስቶስ አገሩን ሳይለቅ ከሄድሮስ ዓይን መሠወር ይችል ነበር።ነገር ግን በአምላካዊ ጥበቡ ከሄሮድስ ዓይን ተሰውሮ ቢሆን ሥጋ መልበሱ ሰው መሆኑን አይገለጽም ነበር።በሄሮድስ ዓይን የማይታይ ከሆነ ሥጋ ሳይለብስ የለበሰ መስሎየተገለጸ ሥጋና አጥንት የሌለው/ምትሐት/ ነው በተባለም ነበር።
ከአዳም አካል አንድም ያልጎደለው ሙሉ ዳግማዊ አዳም መሆኑን እና የለበሰው ሥጋ የሚደማ የሚቆስል በሰይፍም ሆነ በጦር ቢወጋ ጉዳት የሚደርስበት ሰብአዊ ባሕርይ ያለው መሆኑን ለማስረዳት ስደተኛ ሆነ።
ሥጋ የለበሰ ሁሉ ከጠላቱ ማምለጥ የሚችለው ከጠላቱ ፊት ዞር በማለቱ እና በመሸሹ ስለሆነ ጌታም ከጠላቱ ከሄሮድስ ለማምለጥ ሰው እንደመሆኑ ወደ ግብጽ ሸሸ፡፡
መ.ዲያብሎስን ለማሳደድ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰደደ
አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ ከገነት ከወጣ በኋላ የእግዚአብሔርና የሰው ግንኙነት እየራቀ ሄደ፡፡ይህን የፈጣሪና የፍጡር መራራቅ ያመጣው ዲያብሎስ ሲሆን በፈጣሪ መራቅ ፈንታ እርሱ መቅረብ ይፈልግ ነበር፡፡
ስለሆነም ፈጣሪው ከሰው ጓሮ ወደ ወጣበት የሰው ልጅ ሳይጠራ መምጣት ወይም መቅረብ ጀመረ።
ዲያብሎስ የአዳምን ልጆች ተቆጣጠራቸው።ልባቸውን በፍቅረ ጣኦት ሸፍኖ አምልኮተ እግዚአብሔር እንዳያዩ አደረጋቸው ብዙ የአዳም ልጆችም የአግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆን የሰይጣንን ፈቃድ ሲፈጽሙ ኖሩ።ጌታም "አሁን የዚህ ዓለም ገዥወደ ውጪ ይጣላል" ዮሐ፲፪፥፴፩በማለት ሰይጣን ዓለሙን ተቆጣጥሮት እንደነበረ ይገልጻል።
እግዚአብሔር ወልድ የሰውን ሥጋ በለበሰ ጊዜ የፈጣሪና የፍጡር ግንኙነት እንደገና ተመሠረተ።
ኢየሱስ ክርስቶስ አገሩን ለቆ በመውጣቱ ዲያብሎስን ከተቆጣጠረው ከሰው ልቡና አስወጣው ጌታ ከሄሮድስ ፊት እየራቀ ሲሄድ ዲያብሎስም ከሰው ፊት እየራቀ ሄደ።
የጌታ ስደት በተዘዋዋሪ የዲያብሎስ ስደት ሆነ ጌታ የሚቀበለው መከራ ሁሉ ዲያብሎስን በርቀት የሚመታ መሣርያ ነበር፡፡ በመጨረሻም በመስቀል ላይ የሆነው የጌታ ሞት የዲያብሎስ ሞት ሆነ፡፡
✝
በቀጣይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስደቷ ወቅት ያሳለፈቻቸውን ውጣ ውረድና ተያያዥ ክስተቶችን እንዲሁም የጉዞዋን ዋና ዋና መዳረሻዎችን ጭምር ለማስነበብ እንሞክራለን፡፡
ክፍል አምስት ይቀጥላል....
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem