✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል አምስት [፭]
ንጉሥ ሄሮድስ እና ሰብአ ሰገል
ከሩቅ ምሥራቅ የመጡት ነገሥታት (ሰብአ ሰገል) ለዓመታት ያህል ተጉዘው ኢየሩሳሌም ከደረሱ በኋላ፡
"አይቴ ሀሎ ንጉሠ እስራኤል ዘተወልደ ከመነሃብ ሎቱ አምሃ ወሰጊድ" ..... ይዘን የመጣነውን መባዕ እና ስግደት እናቀርብለት ዘንድ የተወለደውሕፃን ወዴት ነው ‘’ ? ወርቅ ለመንግስቱ፣ ዕጣን ለክህነቱ፣ ከርቤ ስለሞቱ እና በረክትለት ዘንድ የተወለደው የዓለም ንጉሥ የት አለ ? እያሉ ሲፈልጉና ሲያፈላልጉ በመልእክተኞቹ አማካኝነት የሰማው የኢየሩሳሌም ንጉሥ ሄሮድስ ይህ ምን ዓይነት ነገር ነው ? የትስ ያለ የዓለም ንጉሥ ነው ? የሚወለደውስ ከማንና መቼ ነው ? አሁን ገና በተወለደ ጊዜ እንዲህ ነገሥታትን ያሰገደ ሕፃን ሲያድግማ እኔንም ያሰጋኛል፤ አልፎም ያጠፋኛል ብሎ እጅግ ከመፍራትና ከመደንገጡ የተነሳ ነገሥታቱን አስጠርቶ ስለ ነገሩ አስፍቶ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም በኮከብ መሪነት ለዓመታት ያህል መጓዛቸውንና አጠቃላይ የአመጣጣቸውን ታሪክ ተረኩለት፡፡ ታሪኩን ሰምቶና ተረድቶ ከበቃ በኋላ ንጉሡ ሄሮድስ ለነገሥታቱ ስለ ሕፃኑ ጠቅላላ ሁኔታ እንዲያጠኑ ሲመለሱም ምስጢሩን እንዲገልጹለት አደራ ብሎ ካሰናበታቸዉ በኋላ መልዓከ እግዚአብሔር ተገልጾ በሌላ መንገድ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ስለነገራቸውና ምስጢሩንም ስለገለጸላቸው የሄሮድስ ተንኮላዊ አደራን ወደ ጎን ትተው መልአኩ እንደነገራቸው በሌላ መንገድ ወደሃገራቸው ተመለሱ፡፡ከሰብአ ሰገል መረጃን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡
ሰብአ ሰገል ወደ እርሱ ባለመመለሳቸው የተበሳጨው ሄሮድስ የራሱን እርምጃ ለመውሰድ ወሰነ፡፡ ምንጊዜም ሄሮድስ የሚፈልገው በቤተልሔም የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ የተባለውን ሕፃን ክርስቶስን አግኝቶ መግደል ነው።
ስለሆነም ሕፃኑ ክርስቶስ ያለበትን ቦታ የሚጠቁም ሰው አላገኘም፡፡ ትክክለኛውን መረጃ ባያገኝም ከሰብአ ሰገል አንደበት የሰማውን ለእንቅስቃሴው መነሻ አድርጎ ተነሣ፡፡
ሄሮድስ እንደመረጃ የተጠቀመው ፡- ሰብአ ሰገልን የመራቸው ኮከቡ የተገለጠበትን ዘመን ነው፡፡ ሰብአ ሰገልን ጠይቆ የኮከቡን ዘመን ተረድቶ ነበር፡፡ ኮከቡ ለሰብአ ሰገል ከተገለጠ ወይም ሰብአ ሰገልን መምራት ከጀመረ ሁለት ዓመት እንደሆነው በጥንቃቄ ተረድቷል፡፡ ሰብአ ሰገልን የመራቸው ኮከብ ሁለት ዓመት ከሆነው የአይሁድ ንጉሥ የተባለው በቤተልሔም የተወለደው ሕፃን ክርስቶስም ሁለት ዓመት ሊሆነው ይችላል የሚል ግምት መገመት ጀመረ ፡፡
ቦታው ቤተልሔም መሆኑ እና የአይሁድ ንጉሥ የተባለው ሕፃን የሁለት ዓመት ሕፃን መሆኑ በመረጃ ተደግፏል፡፡ ነገር ግን በቤተልሔም ብዙ የሁለት ዓመት ሕፃናት ይኖራሉ፡፡ የአይሁድ ንጉሥ የተባለውን ሕፃን እንዴት ለይቶ ማወቅ ይቻላል?የሄሮድስ ልቡ የሚረጋጋበት መፍትሔ አላገኘም፡፡ ሌላ አማራጭ መፈለግ ግድ ሆነበት፡፡ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ በቤተልሔምና በአውራጃዋ የሚኖሩትን ሁለት ዓመት የሆናቸውን እና ከሁለት ዓመት በታች የሆኑትን ሕፃናት መግደል አማራጭ የሌለው የጭንቀቱ መፍትሔ አድርጎ ወሰደው፡፡
መፍትሄውም በቤተልሔም ሕፃናት ላይ ይህን የእልቂት ትእዛዝ ማስተላለፍ በማሰብ ነው፡፡ ሄሮድስ ከቤተልሔም ሕፃናት አንዱ ተነስቶ እንዳይቀር እጅግ ይጠነቀቅ ነበር፡፡ ወታደሮቼ በየሰፈሩ እየዞሩ ሕፃናትን ቢገድሉ ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን ይሰውራሉ ሕፃናቱም ከሞት ያመልጣሉ ከሚያመልጡትም ሕፃናት አንዱ ክርስቶስ ሊሆን ይችላል፡፡
ሌላው ደግሞ የሚገደሉት ሕፃናት ከሁለት ዓመት በታች መሆናቸው በግምት አይታወቁም በማለት ይጨነቅ ነበር፡፡ ሄሮድስ ብዙ ሐሳቦችን ሲያንሸራሸር ከቆየበኋላ ሁሉም ሕፃናት በቤተመንግሥቱ አንድ ቀን ቢገኙ የተሻለ ነገር እንደሆነ አሰበ፡፡ ነገር ግን ሕፃናቱ እንዴት እንደሚሰበሰቡ ሌላ ፈተና ሆነበት በንጉሣዊ ትእዛዝ ወላጆች ልጆቻቸውን እየያዙ እንዲመጡ ቢደረግ በኃይል ወይም በግድ የሆነ ነገር ውጤታማ እንደማይሆን እና ብዙ ሕፃናት እንደሚቀሩ መገመት አላቃተውም፡፡
የቤተልሔም ሕፃናት አንድ ሳይቀር እንዲሰበሰቡ ለማድረግ የወላጆች ፈቃደኝነት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ ንጉሥ ሄሮድስ በቤተልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
ማቴ፪፥፲፮-፲፰
ሄሮድስ ሕፃናትን ለመግደል በቤተመንግሥቱ ለመሰብሰብ የተጠቀመበት ምክንያተ ፈጠራ
የሄሮድስ ቅንዓት እጨመረ ከመሄዱም በላይ ነገሥታቱን ሲጠብቅ ሁለት ዓመት መሆኑን ተከትሎ በነገሩ ተሳልቀውበት (አታልለውት) በሌላ መንገድ መሄዳቸዉን ከተረዳ በኋላ ሰይጣን የጭካኔ ጦሩን መዞ አንድ ጊዜ በልቦናው ላይ ስለተከለበት ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች ያሉ ሕፃናት ሁሉ በእርዳታ ስም በየሀገሩ እንዲሰበሰቡ የሚል ሰይጣናዊ የአረመኔነት መግለጫ የሆነ አዋጅ በብሔራዊ ደረጃ አሳወጀ፡፡
ሄሮድስ ሕፃናትን በቤተመንግሥቱ ለመሰብሰብ አንድ ምክንያት ፈጠረ፡፡ እንዲህም አለ የሮሙ ንጉሥ ቄሣር የላከው መልእክት ከእኔ ደርሷል፡፡
ሁለት ዓመት የሆናቸውን እና ከሁለት ዓመት የሚያንሱትን ሕፃናት እንድቆጥር ቄሣር አዞኛል፡፡ ለሕፃናቱ ወላጆች ገንዘብ እና ልብስ ይሰጣቸዋል፡፡ ሕፃናቱም በቤተመንግስት በመልካም አስተዳደግ ያድጋሉ፡፡ ማርና ወተት እየተመገቡ ጥበብ እየተማሩ በቤተመንግስት አድገው የመንግስት ሠራተኞች ይሆናሉ፡፡ ይህንም የተንኮል አነጋገር በአዋጅ አስነገረ፡፡ ያን ጊዜ አይሁድ የሮሙ ንጉሥ የቄሣር ቅኝ ተገዦች ነበሩን ፡፡
ሄሮድስም የአይሁድ ንጉሥ ሊሆን የቻለው ከቄሣር ተወክሎ ነው፡፡ ስለሆነም ትእዛዙ ከቄሣር እንደመጣ አድርጎ በውሸት ማዕበል ቤተልሔምን አጥለቀለቃት፡፡ ትእዛዙ ግን ከሮሙ ንጉሥ ከቄሣር የመጣ ሳይሆን የሐሰት አባት ከሆነው ከዲያብሎስ የመጣ ነው፡፡ዛሬም ሐሰት ከዲያብሎስ እየተወለደ በቤተመንግስት ያድጋል፡፡ ሐሰት ለገዢዎች የሥልጣናቸው እድሜ ማራዘሚያ ይመስላቸዋልና ነው።
ዮሐ፰፥፵፬
ንጉሥ ሄሮድስ እና የ144000 ሕፃናት ሞት በቤተመንግስት
ክፍል ስድስት ይቀጥላል.....
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem