✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል ስድስት [፮]
ንጉሥ ሄሮድስ እና የ144000 ሕፃናት ሞት በቤተመንግስት
ከዚህ በኋላ ብዙ ሕፃናት ከእናቶቻቸው ጋር በሄሮድስ ትዕዛዝ በቤተመንግሥት ለመታረድ ተሰበሰቡ፡፡ ልጅ ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸውን እየያዙ ሲሄዱ ልጅ የሌላቸው ድሃዎች ደግሞ ሀብት ንብረት ልብስ ቀለብ ለመቀበል የሀብታሞችን ልጆችን እየተዋሱ ይዘው ሄደው ነበርና በጠቅላላው በሄሮድስ ቤተመንግስት 144 000 ሕፃናት ተሰበሰቡ፡፡
ሄሮድስ በተንኮል የሰነቀው የተስፋ ዳቦ ሕፃናቱንም ወላጆችንም የሚያጠግብ መስሎ ስለቀረበ በቤተልሔም አንድ ሕፃን አልቀረም፡፡ ሄሮድስ የሚፈልገው የአይሁድ ንጉሥ የተባለው ሕፃን ክርስቶስ ግን ከ 144 000 ሕፃናት መካከል አልነበረም፡፡
ሄሮድስ በግብዝ አእመሮው ከ 144 000 ሕፃናት መካከል አንዱ የአይሁድ ንጉሥ የተባለው ሕፃን ሳይሆን አይቀርም ብሎ ሕፃናቱ እስኪገደሉ ይቸኩል ነበር፡፡ ሁሉንም ሕፃናት ግደሉ ብሎ ለወታደሮቹ ንጉሳዊ ትዕዛዙን አስተላለፈ፡፡ የሄሮድስ ወታደሮች በአንድ ቀን 144 000 ሕፃናትን አረዱ፡፡ በየሰፈሩ ለቅሶና ዋይታ ሆነ፡፡
የንጉሡ ወታደሮችም በእርዳታ ስም የሰበሰብዋቸውን ሕፃናት እጅግ በሚዘገንን መልኩ የእናቶቻችውን ጡት እንኳ በአግባቡ ጠጥተው ሳይጨርሱ አንገት አንገታቸውን በሰይፍ ቆራርጠው ጨረስዋቸው፡፡ይሁን እንጂ ይህ የሕፃናት እልቂት በንጉሱ ትእዛዝ ምክንያት ከመፈጸሙ አስቀድሞ ንጉሡ ይህንን እኩይ ሐሳብ ሲያስብ በዮሴፍ ጠባቂነት፣ በእመቤታችን እናትነትና በቅድስት ሶሎሜ ረዳትነት ያድግ የነበረው ጌታችን ይህ አዋጅ ከመታወጁና እልቂቱም ከመፈጸሙ አስቀድሞ መልዓከ እግዚአብሔር በሌሊት ለቅዱስ ዮሴፍ ተገልጾ "ተንሥእ ወንሣእ ሕፃነ ወእሞ" ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው፣ አለጊዜውም ደሙን ሊያፈሰው አጥብቆ ይፈልገዋልና እናቱንና ልጁን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ። ማቴ፪፥፩-፳፫
በማለት ተናግረውና በዚያች ሌሊት ወደ ምድረ ግብፅ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ታሪኩ በማቴዎስ ወንጌል እና ጥር ሦስት ቀን በሚነበበው በመጽሐፍ ስንክሳር ተመዝግቧል፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ ስለዚህ ጽኑዕ ኀዘን ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡"ድምፅ በራማ ተሰማ ለቅሶና ብዙ ዋይታ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች መጽናናትንም አልወደደችም የሉምና" የተባለው ተፈጸመ።ማቴ፪፥፲፰ ,ኤር ፴፩፣፲፭
ራሔል የያዕቆብ ሚስት የዮሴፍና የብንያም እናት መሆንዋ/በዘፍጥረት ፴፥፳፪ እና ፴፭፥፲፮ተጽፏል፡፡ የቤተልሔም ሕፃናት በሄሮድስ ሰይፍ በታረዱ ጊዜ ራሔል አልነበረችም፡፡ ሆኖም ልጆቻቸው የታረዱባቸው እናቶችና የታረዱ ሕፃናት የራሔል የልጅ ልጆች ስለሆኑ በልጆቻቸው ሞት መጽናናት ያቃታቸውን እናቶች በራሔል ወክሎ ይናገራል፡፡ ኤርምያስ በልጆቻቸው ሞት የሚያነቡትን የእስራኤልን ሴቶች ራሔል ብሏቸዋል፡፡
ከእመቤታችን ስደት ጋር ታሪክ ያስተናገደው የዮሴፍ ልጅ ዮሳ
የዮሴፍ ልጅ ዮሳ ከእነ ዮሴፍ ጋር አልተሰደደም ከአባቱ ቤት ቀርቶ ነበር፡፡ ሄሮድስ እነ ዮሴፍን ለመያዝ ብዙ ጭፍራ ላከ፡፡ የሄሮድስን የተንኮል ምሥጢር የሚያውቁ ሰዎች ሄሮድስ ዘመዶችህን ሊያስገድል ብዙ ጭፍራ /ወታደር/ ላከ ብለው ለዮሳ ነገሩት፡፡ የዮሴፍ ልጅ ዮሳ እየሮጠ ወደ ዘመዶቹ ሲሄድ ሰይጣን ሰው መስሎ መንገድ ዳር ተቀምጦ የት ትሄዳለህ አለው፡፡ ወደ ዘመዶቼ አለ ዮሳ፡፡ የሄሮድስ ወታደሮች ለጥቂት ቀደሙህ እሰከአሁን ዘመዶችህን ገለዋቸው ይሆናል፡፡ ምን ያደክምሃል ተመለስ አለ ሰይጣን፡፡ ዮሳም ዘመዶቼ ሞተው ከሆነ እቀብራቸዋለሁ አልሞቱም ከሆነ ሄሮድስ እያስፈለጋቸው መሆኑን አነግራቸዋለሁ ብሎ የሰይጣንን ምክር ሳይቀበል መንገዱን ቀጠለ፡፡ እግዚአብሔር ለዮሳ የአንበሳን ኃይል ሰጠው፡፡ እነ ዮሴፍ ሦስት ቀን የተጓዙትን መንገድ በአንድ ቀን ተጓዘና እነ ዮሴፍ ከደረሱበት ቦታ ደረሰ፡፡ እነ ዮሴፍ ሦሰት ቀን በተከታታይ ስለተጓዙ ደክሞቸአው አርፈው ነበር፡፡ ሰሎሜ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስታጥበው አገኛቸው፡፡ዮሳ ሰላም ዋላችሁ ሰላም አደራችሁ ሳይል እንደደረሰ በጣም የሚያስደነግጥ ቃል ተናገረ፡፡ እንዲህም አላቸው በቤተልሔም እና በይሁዳ ሕፃን ያዘለች ሴት አትገኝም፡፡ ሁሉንም ሕፃናት ሄሮድስ በሰይፍ አሳርዷቸዋል፡፡ ይህን ሕፃን ኢየሱስ ክርስቶስን ልታስገድሉት ከዚህ ተቀምጣችኋል፡፡ እመቤታችን የዮሳን ቃል በሰማች ጊዜ ሕፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሰሎሜ እጅ ተቀበለችና አቅፋ ይዛ በሌሊት ብርድ እና በፀሐይ ቃጠሎ መከራ የምቀበለው ከሞት ላላድንህ ነው ብላ ጽኑዕ ልቅሶን አለቀሰች፡፡
ሕፃኑ ኢየሱስ ክርሰቶስ ዮሳን እንዲህ አለው ድካምህ ዋጋ የሚያሰጥ ነው ነገር ግን እናቴን ስለአስደነገጥካት ይችን ድንጋይ ተንተርሰህ ተኛ አለው ፡፡ ወዲያውም ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡ አባቱ ዮሴፍ ቀበረው፡፡ እንደ እኛ እንደሰዎች አመለካከት ዮሳ የሚሸለም ሰው ነበር እንጂ የሚቀጣ ሰው አልነበረም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ዮሳ ባጠፋው ትንሽ ጥፋት በሥጋው ተቀጥቶ በነፍሱ ሕያው እንዲሆን አደረገው ፡፡ የአግዚአብሔር ወዳጆች ትንሽ ጥፋት ሲአጠፉ በሥጋቸው ይቀጣሉ፡፡ ለምሳሌ አሮን እና ሙሴ የእግዚአብሔር ወዳጆች ነበሩ፡፡ አንድ ቀን ባጠፉት ጥፋት ተቀጡ፡፡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሳይገቡ በመንገድ ሞቱ "እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር ይህን ጉባዔ ይዛችሁ አትገቡም" አላቸው። ዘኁ፳፥፩-፲፫
ጥበበኛው ሰሎምንም እንዲህ ይላል "ልጄ ሆይ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና አባት የሚወደውን ልጁን እንደሚገሥጽ" ምሳ፫፥፲፩
ዛሬስ በጌታ ላይ፣ በእመቤታችን ላይ፣ በቅዱሳን ላይ ያልተገባ የሰነፍ ንግግርንስ የሚናገሩ ምንኛ በነፍስ በሥጋ ይቀጡ ይሆን ?
ጥጦስና ዳክርስ (ሁለቱ ወንበዴዎች)
ክፍል ሰባት ይቀጥላል.....
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem