✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል ሰባት [፯]
ጥጦስና ዳክርስ (ሁለቱ ወንበዴዎች)
ጥጦስ እና ዳክርስ ሁለት ወንበዴዎች መተዳደሪያቸው ቅሚያ ነበር፡፡ እነ ዮሴፍ ከገሊላ በወጡ ጊዜ ወንበዴዎቹ ተከተልዋቸው፡፡ በበረሃ ቢፈልጓቸውም እስከ ስድስት ቀን አላገኝዋቸውም፡፡
በሰባተኛው ቀን አገኝዋቸውና ዛሬስ እግዚአብሔር ከእጃችን ጣላችሁ ብለው እየሮጠ ሄዱባቸው፡፡ ሰሎሜ አስቀድማ ልብሷን ጥላላቸው ሸሸች፡፡ወንበዴዎቹ ከእነዮሴፍ እጅ የተገኘውን ቀምተው ከሄዱ በኋላ ጥጦስ ዳክርስን እንዲህ አለው፡፡
ይቺ ሴት የነገሥታት ወገን ትመስለኛለች፡፡ ሕፃኑም ከነቢያት አንዱ ይመስለኛል፡፡ የቀማናቸውን እንመልስላቸው? ዳክርስም ጥጦስን እንዲህ ያለውን ርኅራኄ ከየት አገኘኸው? ይህን ውንብድና ያስተማርከኝ አንተ ነህ፡፡ ሌላው ደግሞ ዛሬ የቀማነው የእኔ ድርሻ ነው የራስህን ድርሻ ወስደህ የእኔን ድርሻ እንመልስላቸው ትላለህ ? አለው፡፡
እነዚህ ሁለት ቀማኞች አንድ ቀን የቀሙትን አንደኛው ሲወስድ በሌላ ቀን የቀሙትን ደግሞ ሁለተኛው ይወስድ ነበር፡፡ በዚህ ዕለት የቀሙት የዳክርስ ድርሻ ነበር፡፡ ጥጦስም ከገሊላ እስከዚህ የቀማነውን አንተ ውሰድ ይህን ለእኔ ስጠኝና ልመልስላቸው አለው፡፡
ዳክርስም በዚህ ሐሳብ ተስማማ፡፡ ዳክርስ ያልታደለ ሰው ነው፡፡ ጥሩ እድል ገጥሞት ነበር አልተጠቀመበትም፡፡ በትንሽ ርኅራኄ ብዙ በረከት አመለጠው፡፡ ወደ አርሱ ያንዣበበውን ፀጋ ለጓደኛው ሰጠው፡፡
እመቤታችን ሁለቱ ወንበዴዎች ቁመው በዚህ ሐሳብ ሲወያዩ አይታ ፈራች፡፡ ወንበዴ የቀማውን ይዞ ይሄዳል እንጂ ለምን ቁሞ ይማከራል? ምን አልባት ልጆቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ይሆናሉ፡፡ በዚህ ሕፃን ምክንያት ልጆቻችን ሞቱብን ብለው ልጄን ሊገሉብኝ ይሆናል ብላ ጽኑዕ ለቅሶን አለቀሰች፡፡
ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስም እናቱም ድንግል ማርያምን እንዲህ አላት፡፡ አይዞሽ እናቴ አታልቅሺ አይገሉኝም እንመልስላቸው እያሉ ነው፡፡ እኔ በቀራንዮ ስሰቀል እነሱም በቀኜ እና በግራዬ ይሰቀላሉ አንዱ አምላክነቴን አምኖ ይድናል ሁለተኛው ግን አይድንም፡፡
ከዚህ በኋላ ጥጦስ የተባለው ወንበዴ ገንዘባቸውን መለሰላቸውና ጌታን አቅፎ ይዞ ሲሄድ ሰይፉ ወድቆ ተሰበረበት፡፡ በጣም አዘነ፡፡ ጌታ የሰይፍህን ስብርባሪ ሰብስብ አለው፡፡ ጥጦስ የሰይፉን ስብርባሪ ሰበሰበ፡፡ ጌታም እንደቀድሞው ይሁንልህ አለው፡፡ሰይፉም እንዳልተሰበረ ሆነ፡፡
ጥጦስ ሕፃኑ ከነቢያት ወገን ይመስለኛል ብሎ የገመተው ግምት እውን ሆነለት፡፡ ተአምራቱን አየና አደነቀ፡፡ ጌታ ጥጦስን እንዲህ አለው፡፡ አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ፡፡ ጥጦስም ሄዶ ጌታ የነገረውን ሁሉ እና ያደረገለትን ተአምራት ለጓደኛው ነገረው፡፡ ጓደኛው ግን አላመነም፡፡ ጥጦስ የተባለው ወንበዴም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ በጌታ ቀኝ ተሰቅሎ ፀሐይ ስትጨልም አይቶ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት አምኖ "ጌታ ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው፡፡ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትሆናለህ"ሉቃ፳፫፥፵፪። ጌታ አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ ብሎ በጫካ የሰጠውን ተስፋ በመስቀል ላይ ፈጸመለት፡፡
እመቤታችን ከልጇ ጋር በስደት ከተጓዘችባቸው ሀገራት መካከል፦
ክፍል ስምንት ይቀጥላል.....
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem