✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል ስምንት [፰]
እመቤታችን ከልጇ ጋር በስደት ከተጓዘችባቸው ሀገራት መካከል፦
የድንግል ማርያም የስደትዋ ምስጢር ጸጋው የበዛላቸው ሊቁ ቅዱስ አባት አባ ጽጌ ድንግል "በሰቆቃወ ድንግል" በስፋት እንደገለጹት በዚህ ዓለም ላይ የኖረና ለወደፊትም የሚኖር ፍጡር እንደ ድንግል ማርያም አለመኖሩ አበክረው ያሰምሩበታል፡፡
ሊቁ ይህንን ድርሰታቸው
ሲጀምሩም፡-ማኅሌተ ጽጌ፡-በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ሕጸተ ግጻዌ ዘአልቦ ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ ወይሌ ወላህ ለይበል ለዘአንበቦ ከማሃ ሀዘን ወተሰዶ ሶበ በኩለሄ ረከቦ ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ.... ብለው ነው፡፡ ይኸውም እንኳንስ በዓይነ ሕሊና ወደ ምድረ ግብፅ ወርዶ ያየውና የሰማው አይደለም እንዲሁ ለይኩን ብሎ ያዳመጠው እንኳ ሳይቀር ከብዝሐ መከራዋ ተነስቶ እንደሚያለቅስ ይገልጽልናል።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስደት መንፈሳዊ ዓላማና በምሥጢረ ድኅነት ውስጥ የራሱ የሆነ ድርሻ ያለው እንጂ በአጋጣሚ የተገኘ እንዳልሆነ እንዲሁም የተነገረው ቃለ ትንቢት ለመፈጸም እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሲያትቱ ከተነገሩት ትንቢቶች መካከል፡-"ወፍኖቶሂ ዘእም ዓለም ርኢኩ አዕፃዳተ ኢትዮጵያ ይደነግፃ" ከጥንት የታሰበ መንገዱን አየሁ የኢትዮጵያ አውራጃዎችም ይደነግጣሉ።እንባቆም፫፥፮፯ የሚለው ትንቢት በማራቀቅ እመቤታችን በመዋዕለ ስደቷ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በመምጣት ሃገራችንን ጎብኝታ ሕዝባችንን በአሥራት ተሰጥታ (ከልጇ ተቀብላ) እንደሄደች በመተረክ ሊቃውንት መምህራኑ ያራቅቃሉ።
እመቤታችን ስትሰደድ ያልደረሰበት መከራ፣ ያልተፈራረቀባት ችግር ... አልነበረም፡፡ ይህም ሆኖ ግን ስለሚደርስባት ነገር ፈጽሞ አታስብም ነበር፡፡ የምታስበው ልጇ እንዳይሞትባት ብቻ ነው፡፡"ይእቲ ትበኪ ወትቤ ቀቲሎትየ ይቅድሙ፣ እም ይርአይ ለወልድየ ዘይትከአው ደሙ "ትርጉም እርሷም ይህንን ሰምታ አለቀሰች የልጄ ደሙ ሲፈስ ከምመለከትስ እኔን ያስቀደሙ፣(ሰቆቃወ ድንግል) እንደለ ደራሲ፡፡
ሀ.ገዳመ ጌራራል/ጌራራል ከተባለ ጫካ /፦
መልአክ ለዮሴፍ ሕፃኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ ካለው በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአመቤታችን ጠባቂ ዮሴፍ የእመቤታችን አክስት ወይም የሐና እህት ሰሎሜ አራቱ ጉዞአቸውን ጀምረዋል፡፡
ወደ ግብፅ እንዲሰደዱ የተነገራቸው ቢሆንም ወደ ግብፅ ከመሄዳቸው በፊት ብዙ አገሮችን ዙረዋል፡፡ ከቤታቸው እንደወጡ ጌራራል ወደተባለ ጫካ ነበር የሄዱት ማቴ ፪፥፲፫።
እነ ዮሴፍን በገዳመ ጌራራል መላዕክት እየመጡ እያጽናኑዋቸው አርባ ቀን ተቀምጠዋል፡፡ ከአርባ ቀን በኋላ አንድ አውሬ አዳኝ አያቸው፡፡ እርሱም በፍጥነት ሄዶ ማርያምንና ዮሴፍን ሰሎሜንም በጌራራል ጫካ ትላንትና አየኋቸው ብሎ ለሄሮድስ ነገረው፡፡ ሄሮድስም በጌራራ ጫካ መኖራቸውን በሰማ ጊዜ ደስ ተሰኘ፡፡ ይህንን ወሬ ላመጣለት አውሬ አዳኝ እነ ዮሴፍን ካሳየህኝ የመንግስቴን እኩሌታ እሰጥሃለው ብሎ በጣኦቱ ማለለት፡፡ ሄሮድስ በሀገሩ ሁሉ አዋጅ ነጋሪ /መልእክተኛ/ ላከ፡፡ አዋጅ ነጋሪው በሀገሩ እየዞረ ሁላችሁም የሄሮድስ ወታደሮች ነገ በሄሮድስ ቤተመንግስት እንድትገኙ በማለት አስጠነቀቀ፡፡ ወታደሮቹም የሄሮድስን ቤተመንግስት አጥለቀለቁት፡፡ ሄሮድስም ወደ ጌራራል ጫካ ላካቸው፡፡ የሄሮድስ ወታደሮች የጌራራልን ጫካ ከበቧት፡፡ ነገር ግን እነ ዮሴፍን አላገኙዋቸውም፡፡ ወታደሮቹ እርስ በራሳቸው እንዲህ ተባባሉ፡፡ እነዮሴፍ የትሄዱ ምድር ዋጠቻቸውን ? ይሉ ነበር ። እነ ዮሴፍን ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ የሄሮድስ ሰራዊት በማያውቁት መንገድ ወሰዳቸው፡፡
ለ.ጥብርያዶስ ፦
ከዚህ በኋላ የእመቤታችን ዘመድ የኬፋዝ ንጉሥ ወደ አለበት ወደ ጥብርያዶስ ሄዱ፡፡ እመቤታችንም ሄሮድስ እንደሚያሳድዳት ዘመዷ ለሆነው ንጉሥ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ሄሮድስ የሚያሳድድሽ በምን ምክንያት ነው ብሎ ጠየቃት፡፡ ይህን ሕፃን ለመግደል ስለሚፈልግ ነው አለችው፡፡
ንጉሡም እመቤታችነን ከዚህ ከእኔ ቤት ተቀመጪ አላት፡፡ ቤተሰቦቼንም ማርያም ከእርሱ ቤት መኖርዋን ለማንም እንዳይነግሩ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሄሮድስ ግን በብዙ ሀገሮች እየዞረ ቢፈልጋት ሊአገኛት አልቻለም፡፡ ሄሮድስ እንዲህ ይል ነበር፡፡ ማርያምን ምድር ዋጠቻትን? ሄሮድስ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ያደረገው ጥረት የደከመው ድካም እጅግ ብዙ ነው ያለውን ኃይል አሟጦ ተጠቅሞአል የሚፈልገውን አለማግኘቱ ደግሞ ድካሙን ውጤት አልባ አድርጎታል፡፡
ከብዙ ቀናት በኋላ ሄሮድስ ጥብርያዶስ በሚባል ሀገር እመቤታችን መኖርዋን ሰማ፡፡ እመቤታችን ወደ አለችበት ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ መልእክተኛ ላከ፡፡ ሄሮድስ የጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል፡፡
ንጉሥ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ማርያምን ከነልጅዋ ያዝልኝ ብዙ ወርቅ እና ብር እሰጥሃለሁ በእኔ እና በአንተ መካከል ጽኑዕ ፍቅር ይሆናል፡፡ ንጉሡም የሄሮድስን ደብዳቤ አንብቦ በጣም ተገረመ፡፡ እንዲህም አለ፡፡ ማርያም በእኔ ቤት መኖርዋን ለሄሮድስ ማን ነገረው? መቼም ሰው አልነገረውም ሰይጣን ነግሮታል እንጂ፡፡ የእመቤታችን ዘመድ የሆነው ንጉሡም ሄሮድስ የላከውን መልዕክት ለእመቤታችን ነገራት፡፡ እመቤታችንም በጣም ደነገጠች፡፡ ንጉሡም እኔ ከሞትኩ ትሞቻለሽ እኔ ከዳንኩ ትድኛለሽ አትፍሪ፣ ለሄሮድስ አሳልፌ አልሰጥሽም አላት፡፡"ወትቤ ማርያም ዘፈቀደ አምላከ እስራኤል ለይኩን /ማርያምም የእስራኤል አምላክ የፈቀደው ይሁን" አለች/፡፡ በዚያች ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ሲነጋ ይህን ሀገር ለቀሽ ወደ አድባረ ሊባኖስ ሂጂ አላት፡፡ በዚያም እኔ መጥቼ ተነሺ እስክልሽ ድረስ ተቀመጪ አላት፡፡ በነጋ ጊዜ መልአኩ የነገራትን ለንጉሡ ነገረችው፡፡ ንጉሡም ደስ ብሎት የሦስት ቀን መንገድ እሰከ ዛብሎን እና እስከንፍታሌም ድረስ ሸኛቷት ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡
ሐ.አድባረ ሊባኖስ ፦
ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል.....
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem