✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል አስራ ሁለት [፲፪]
ከዘጠኝ ወር በኋላ ከቤቱ ወጥተው ሲሄዱ ሊባ የሚባል ባሕር ካለበት አገር ደረሱ፡፡ የዚያ አገር ሰዎች በጅራፍ እየገረፉ አባረርዋቸው፡፡ እነ ዮሴፍ ቤልቤል ከሚባል ዛፍ ስር አደሩ፡፡ ነገር ግን መልአክ ወርዶ በሰረገላ ወስዶ ካሳደድዋቸው ሰዎች አገር መካከል አስቀመጣቸው፡፡
እመቤታችንም ከእንቅልፏ በነቃች ጊዜ ያደሩበት አገር በጅራፍ እየገረፉ ያሳደድዋቸው ሰዎች አገር እንደሆነ አወቀች፡፡ እመቤታችንም የትናንቱ ጅራፍ ተመልሶ እንዳይመጣ ወደ እግዚአብሔር አጥብቃ ጸለየች፡፡ በጅራፍ የገረፍዋቸው ሰዎችም ከሰውነት ወደ ውሻነት ተለወጡ ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ሰዎች የሚቀጣበት መሣሪያው የተለያየ ነው፡፡ አእምሮ ያለውን ሰው አእምሮ የሌለው እንስሳ ያደርገዋል፡፡
ይህ አይነት ቅጣት በጣም የሚታበዩ ሰዎች የሚቀጡበት ነው፡፡ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በትዕቢቱ ምክንያት ወደ አውሬነት ተለውጦ ቤተመንግስቱን ለቅቆ ከአራዊት ጋር ሣር እየበላ ሰባት ዓመት ኖሯል። ዳን፬፥፳፰-፴፪
የእመቤታችን ለቅሶ በወንዝ ማዶ
እመቤታችን ከዮሴፍ እና ከሰሎሜ ተለይታ ልጅዋን ይዛ ወንዝ ተሻግራ ብቻዋን ተቀመጠች፡፡ ከመከራዋ ብዛት የተነሣ በጣም አለቀሰች እንዲህም አለች፡፡ ሞሳር እና ግብፅ ማደርያዬ ሆነዋል፡፡ ይሁዳን እና ቤተልሔምን የት አገኛቸዋለሁ፡፡ እኔ በተወለድኩበት አገር በደብረ ሊባኖስ የሚኖሩ ሰዎች ብፁአን ናቸው፡፡ በኪስባር የሚኖሩ ሰዎች ሰውነቴን አስጨነቋት የንፍታሌም እና የዛብሎን ልጆች ባካችሁ ስለ ደረሰብኝ መከራ አልቅሱልኝ ተንቄአለሁና የገሊላ እና የቁስጥንጥንያ ልጆች ልታዩኝ አይገባም፡፡
ዕንባዋን እንደ ጎርፍ እያፈሰሰች አለቀሰች ልቧ በኀዘን ተቃጠለ። ዮሴፍ ከሩቅ ሆኖ ይመለከታት ነበር፡፡ ሊያረጋጋት በሄደ ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ወደ እኔ አትምጣ አለችው፡፡ በድንጋይ የተቀጠቀጠችውን እና በጅራፍ የተገረፈችውን ግርፋት ስታስብ መረጋጋት አልሆንልሽ አላት፡፡
በኀዘን ላይ ኀዘን በለቅሶ ላይ ለቅሶ ጨመረች፡፡ ዮሴፍም እጅግ ተበሳጨ ከእመቤታችን ጋር ከሚቀበለው መከራ በላይ የእመቤታችን አለመረጋጋት በብስጭቱ ላይ ብስጭት ጨመረበት በመከራው ላይ ሌላ መከራ ሆነበት፡፡ ትዕግሥቱን ጨረሰና መከራውን በሞት ለመገላገል አሰበ፡፡ ታንቆ ይሞት ዘንድ ገመድ ወስዶ በዕንጨት ላይ አሠረና አንገቱን አስገባ፡፡ መልአክ ወርዶ ከዮሴፍ አንገት የገባውን ገመድ ቆረጠው፡፡ ዮሴፍንም እንዲህ አለው፡፡የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ ለምን ትበሳጫለህ የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ ጌታን የታቀፈች እመቤታችን ከዓይኖቿ ዕንባን ስታፈስ አታያትምን ? ታንቀህ በመሞት ይህን ዓለም እና የወዲያኛውን ዓለም እንዳታጣ ታገሥ፡፡ መልአኩ ዮሴፍን ካረጋጋ በኋላ ወደ እመቤታችን ሄዶ ሰገደላትና ሰላምታ ካቀረበላት በኋላ እንዲህ አላት የዳዊት ልጅ ማርያም ሆይ ይህን ያህል ኀዘን ለምን ታዝኛለሽ ይህ ሁሉ ድካምሽና ኀዘንሽ ይረሳል፡፡ ዮሴፍ ስለ አንቺ እና ስለ ልጅሽ ቤቱን፣ ንብረቱን፣ ዘመዶቹን ትቶ በበረሃ እየተንከራተተ ነው ለምን አልረጋጋም ትይዋለሽ፡፡ መልአኩ እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜን አገናኝቷቸው ሄደ ፡፡
ሰ. ቤተ ትዕማን ፦
በግብፅ ትዕማን የምትባል ባዕለጸጋ ሴት ነበረች ከእርስዋ ቤት ደረሱ፡፡ ትዕማን በምድራዊ ሀብት እጅግ የከበረች ሴት ነበረች፡፡ እመቤታችን ልጅዋን መሬት ላይ አስቀመጠችውና በሀብት የከበረችውን ሴት እንዲህ አለቻት፡፡ ልጄን በጣም ስለራበው ወተት ካለሽ ወተት ስጪኝ ወተት ከሌለሽ በቤትሽ ካለው ምግብ ስጭኝ ? ሴትዮዋ ግን ርኅራኄ የሌላት ጨካኝ ስለሆነች በእመቤታችን ሳቀችባት እንዲህም አለቻት፡፡ መልክሽ ቆንጆ ነው፡፡ ልብሽ ግን ጠማማ ነው በጣም ሰነፍ ሴት ነሽ፡፡ ይህን የልመና ቃልሽን ሁለተኛ እንዳልሰማው፡፡ እመቤታችን የክፉዋን ሴት ቃል ከሰማች በኋላ እውነት ተናግረሻል ይህ ሁሉ መከራ ያገኘኝ በኃጢአቴ ነው ብላ ዕንባዋን አፈሰሰች፡፡ የተራቡት በልተው የሚጠግቡበት የተጠሙት ጠጥተው የሚረኩበት የአባትዋን እና የእናትዋን ቤት አሰበች፡፡ ዮሴፍ በሀብት የከበረችውን ሴት እንዲህ አላት ምግብ ቢኖር ለእንግዳ መስጠት ይገባል፡፡ ባይኖር ደግሞ ካለው ያድርስህ ተብሎ በሰላም ይሸኛል እንጂ ልብን እንደ ጦር የሚወጋ ነገረ ለምን ትናገርያለሽ፡፡ ክፉዋ ሴትም ዮሴፍን ከእግሩ እስከ ራሱ ተመለከተችውና አንተ ፍየል ጠባቂ እኔን ታስተምረኛለህን ? አለችው፡፡ እንደ አለት የጠነከረው ልቧ ከጭካኔ ወደ ርኅራኄ አልተመለሰም በወይን ጠጅ እንደሰከረ ሰው በእነዮሴፍ ላይ መሳቋን አላቋረጠችም፡፡ የትዕማን የቤት ሠራተኛዋ ኮቲባ ትባላለች፡፡ ከካም ዘር ስትሆን እንደ ቁራ የጠቆረች ነበረች፡፡ እየሮጠች መጥታ ሕፃኑን ኢየሱስ ክርሰቶስን አንስታ ወደ መሬት ጣለችው፡፡ እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ እየሮጡ ሄደው አነሱት፡፡ ወደ ትዕማን ዞር ባሉ ጊዜ ግን ትዕማን ከቆመችበት ቦታ አልነበረችም፡፡ እንደ አቤሮን እና እንደዳታን መሬት ተከፍታ ዋጠቻት
ዘኁ ፲፮፥፩-፴፭ የቤት ሠራተኞችም ግማሽ አካሏ ጥቁር ሲሆን ግማሽ አካሏ ነጭ ሆነ፡፡ የትእማን ዘመዶች፣ ቤተሰቦች፣ ባሏም ጦጣና ዝንጀሮ እየሆኑ ወደ ጫካ ሄዱ ፡፡
ከዚህ በኋላ እመቤታችን ዮሴፍ እና ሶሎሜ ከትዕማን ቤት ገብተው ተቀመጡ፡፡ እስከ ስድስት ወርም ከዚያው ኖሩ፡፡ ከስድስት ወር በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በመንፈቀ ሌሊት መጣና በዚህ ቤት ይብቃችሁ ከዚህ ቤት ለስድስት ወር ያህል ደስ ብሏችሁ ተቀምጣችኋል፡፡
ሸ. ምድረ ንሒሳ ፦
ከዚህ በኋላ እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ከዚህ አገር ወጥተው ሄዱና ወደ ንሒሳ አገር ገቡ፡፡ብዙ ሕዝብ ወደ እመቤታችን መጥተው ወልደ እግዚአብሔር ከአንቺ እንደሚወለድ ነቢያት የተናገሩትን ሰምተናል እያሉ ሰገዱላት፡፡ እመቤታችንም ብዙ ሕዝብ እየመጡ ይመሰክራሉ ብሎ እየመጡ የተናገረላችሁ እናንተ ናችሁ አለቻቸው፡፡ ብዙ ሰዎች እየመጡ ለእመቤታችን ሰላምታ አቀረቡላት፡፡ እመቤታችንም በንሒሳ ሦስት ቀን ከቆየች በኋላ በአገራችሁ በሽተኞች የሉምን ? ብላ ጠየቀቻቸው፡፡ እነሱም ብዙ በሸተኞች አሉ ብለው መለሱ፡፡ እመቤታችንም ሁሉንም በሽተኞች ነገ ወደ እኔ አምጡአቸው አለቻቸው፡፡ በማግስቱ በተለያየ በሽታ ተይዘው የሚማቅቁትን በሽተኞች ሰብስበው አመጡላት ሁሉንም ፈወሰቻቸው፡፡ ከአገራቸው መካከል ከደረቅ መሬት ላይ ውሃ አፈለቀችላቸው፡፡ የፈለቀው ውሃም በሽተኞችን የሚፈውስ ማየ ሕይወት ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ ደመና መጣና እመቤታችንን ዮሴፍን እና ሰሎሜን አቅፎ ወሰዳቸው፡፡ በእግር ሰላሳ ስምንት ቀን የሚወስድ ሩቅ ቦታ ላይ አስቀመጣቸው፡፡ በዚያ ቦታ ያለኀዘን ያለለቅሶ ያለመከራ ጥቂት ጊዜ ተቀምጠዋል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው የእመቤታችን ታሪክ ነገረ ማርያም ከተባለው መጽሐፍ የተወሰደ ነው፡፡
ቀ.ምድረ ኢትዮጵያ ፦
ክፍል አስራ ሦስት ይቀጥላል...
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem