✞ ዘመነ ጽጌ ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል አስራ አራት [፲፬]
ድንግል ማርያም ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ዮሴፍ እና ሰሎሜ ከግብፅ ወደ ኢየሩሳሌም መመለሳቸው
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍ እና ሰሎሜ በስደት የኖሩት ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ነው፡፡ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ከተፈጸመ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ሲጥር የነበረው የገሊላው ንጉሥ ሄሮድስ ሞተ፡፡
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ግብፅ ሄደና የሄሮድስን ሞት ለእነ ዮሴፍ ነገራቸው፡፡ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለው፡፡ ማቴ፪፥፲፱-፳፪
ከዚህ በኋላ ከግብፅ ወደ እስራኤል አገር ለመሄድ ተነሡ፡፡ እመቤታችን በግብፅ የቆየችባቸውን አገሮች ተራራዎችን፣ ኮረብታዎችን፣ ጫካዎችን እና ሜዳዎችን ባረከቻቸው፡፡
ተራራዎችም ጫካዎችም ዕፀዋቱም ለእመቤታችን ሰገዱላት፡፡ በሰላም ወደ አገርሽ ግቢ እንደማለት ነው፡፡ እመቤታችን እነሱን በመባረክ እነሱም ለእመቤታችን በመስገድ ተስናበቱ፡፡
እነ ዮሴፍ ከደብረ ቁስቋም ወጥተው ሞሳር ወደተባለ አገር ደረሱ፡፡ ከዚያም መአልቃ ከሚባል ቦታ ደረሱና በጫካ ውስጥ አደሩ፡፡
ከዚህ በኋላ ከሞሳር ወጥተው በስደት እያሉ ጌታ ውሃ ወደ አፈለቀባት መጠርያ ወደተባለች አገር ደረሱና ጌታ ባፈለቀው ውሃ ታጠቡ፡፡ ውሃይቱም የተባረከችና የተቀደሰች ውሃ ሆነች፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ እስራኤል አገር እየቀረቡ ሲሄዱ የሄሮድስ ልጅ አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ፈንታ በይሁዳ እንደ ነገሠ ሰሙ፡፡ ዮሴፍ ይህን ዜና በሰማ ጊዜ እርሱም እንደአባቱ እኛን ለመግደል ይፈልግ ይሆናል ብሎ ፈራ፡፡
መልአኩ መጥቶ በሕልሙ ወደ አገርህ ወደ ገሊላ ግባ አትፍራ አለው፡፡ዮሴፍ ሕፃኑንና እናቱን ፣ሰሎሜንንም ይዞ ገሊላ ገባ፡፡ናዝሬት በምትባለው ከተማም ኖሩ።ማቴ፪፥፲፱-፳፪
ክፍል አስራ አምስት (የመጨረሻው) ይቀጥላል...
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem