➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
🍀🍀🍀
እስልምናን በገንዘብ ማስቆም አይቻልም
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔘 በገንዘብና በቁሳቁስ እርዳታ በኩል አድርገው እስልምናን ለማጥፋት የሚሞክሩ ሰዎች በአንድ በኩል ሙስሊሞችን ከዲናቸው ለመጎተት ሲጣጣሩ ይስተዋላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ለክህደት እንቅስቃሴዎች የገንዘብ እርዳታ በማድረግ ክህደት ከእስልምና በላይ እንዲያንሰራራ ለማድረግ ይንቀሳቀሳሉ፡፡
🔘 ይህ የጥፋት እንቅስቃሴ በነበሩበት የጥፋት ጎዳና ላይ ድርብ ጥፋት ሆኖ ጉዳት የሚጨምርባቸው መሆኑን ቢገነዘቡ መልካም ነበር። ግና ለዚህ አልታደሉምና ገንዘባቸውን በማፍሰስ እስልምናን የማዳከም ሙከራን ያደርጋሉ፡፡ አላህ ሂዳያ ይስጣቸው!
🔘 ይህን ተግባራቸውን አስመልክቶ አላህ በቁርአኑ በሱረቱል አንፋል 36ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ይለናል፦
🔆 إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ لِيَصُدُّوا عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ فَسَيُنفِقُونَهَا ثُمَّ تَكُونُ عَلَيْهِمْ حَسْرَةً ثُمَّ يُغْلَبُونَ
🔆 እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘባቸውን ያወጣሉ። በእርግጥም ያወጧታል ፣ ከዚያም በእነሱ ላይ ፀፀት ትሆንባቸዋለች! ፣ ከዚያም ይሸነፋሉ!
🔘 ከዚህ አንቀፅ እንደምንረዳው የአላህን ዲን ለማዳከም ገንዘብ ማውጣታቸው ፀፀት ላይ ያደርሳቸዋል፡፡
🔘 ፀፀታቸው በብዙ መገለጫዎች እውን የሚሆን ሲሆን ከነዚህ መካከል እንዳሃሳባቸውና እንደምኞታቸው እስልምናን ማስቆም ባለመቻላቸው የሚደርስባቸው የቁጭት ፀፀት ይገኝበታል።
🔘 እስልምና የአላህ ብርሃን እንደመሆኑ መጠን ሊያስቆሙት የሚቻላቸው አይደለምና ሁሌም እንደበራ ይቀጥላል❗️
🔘 ዋናው ፀፀታቸው የሚሆነው ግን ምናልባትም ወደ እስልምና የመግባት እድሉን ሳያገኙ ሞትን የቀመሱ እንደሆን በገንዘባቸው ይሰሩት የነበረው ስራ በቂያም ቀን ከፊት ለፊታቸው በሚቀርብበት ጊዜ ይሆናል። እንዲህ ያለ የክህደት ድርጊት ደግሞ እሳት ውስጥ መኖርን የሚያስከትል መሆኑ በብዙ ማስረጃዎች ተብራርቶልናል፡፡ ይህንን አስመልክቶ ከላይ የጠቀስነው አንቀፅ መጨረሻ ላይ አላህ እንዲህ ይላል ፦
🔆 وَالَّذِينَ كَفَرُوا إِلَىٰ جَهَنَّمَ يُحْشَرُونَ
🔆 እነዚያም የካዱት ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ!
🔘 ይህ አንቀፅ በዚህ መልኩ የተጠናቀቀው ከእስልምና መንገድ ሰዎችን ለማዘናጋት ገንዘብ የሚያወጡት ሰዎች ከመጠቀሳቸው ቀጥሎ መሆኑ ይህን መሰል ተግባር ላይ ለሚሳተፉ በሙሉ ማስፈራሪያና ዛቻ ያዘለ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በዚሁ የክህደት እንቅስቃሴ ላይ ለሚቀጥሉና የአላህን መሃሪነት ለማይታደሉ ሁሉ የፍፃሜያቸው ትምቢት ሆኖ በቁርአን ላይ ሰፍሮ ይቆያል፡፡
➡️ ማን ከሰረ ታዲያ⁉️
አል-ኢሻራ