👉አል-áŠĸáˆģáˆĢ👈


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


☞ሸáˆĒዓዊ áŒĨቆማዎá‰Ŋ የሚáˆĩተናገዱበá‰ĩ á‰ģነል!

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: ☀ሁá‹ŗ መልቲሚዲá‹Ģ |HUDA MULTIMEDIA
💡የህá‹ŗሴው ግá‹ĩá‰Ĩና የáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ሙáˆĩሊሞá‰Ŋ!

⚡ī¸á‹á‹ĩ የ ☀ī¸áˆá‹ŗ መልቲሚዲá‹Ģ ቤተሰá‰Ļá‰Ŋ
đŸ•¯ áˆĩለ አá‰Ŗይ ግá‹ĩá‰Ĩ የተወሰኑ ሙáˆĩሊሞá‰Ŋን ለማናገር ሞክáˆŦ ነበር! ምላáˆģቸውን አጠናቅáˆŦ በዚህ á‰Ēዲዮ አá‹Ģይዤዋለሁ!

đŸ“Ŗሁላá‰Ŋሁም ተመልክá‰ŗá‰Ŋሁ ለሌሎá‰Ŋም á‹Ģጋሩ ዘንá‹ĩ አደáˆĢ áŠĨላለሁ!!!

https://youtu.be/ubv2Hnao0qs


Forward from: ዲን መመáŠĢከር ነው
â–Ēī¸á‹¨á‰´áˆŒáŒáˆĢም ሊንኮá‰Ŋ áˆĩá‰Ĩáˆĩá‰Ĩ

đŸ”ģሙሐደáˆĢዎá‰Ŋ áŖ ተከá‰ŗá‰ŗይ ደርáˆļá‰Ŋ áŖ ፅሑፎá‰Ŋ áŠĨና ጠቃሚ á‹ĩምጾá‰Ŋ የሚለቀቁá‰Ŗቸውን የቴሌግáˆĢም á‰ģናሎá‰Ŋ ለመቀላቀል ከá‰ŗá‰Ŋ á‹Ģሉá‰ĩን ሊንኮá‰Ŋ ይáŒĢኑ .. ለሌሎá‰Ŋም á‹Ģáˆĩተላልፉ .. በአሏህ ፍቃá‹ĩ ተጠቃሚ ይሆናሉ
👇👇


➖ بØŗŲ… اŲ„Ų„Ų‡ اŲ„ØąØ­Ų…Ų† اŲ„ØąØ­ŲŠŲ… 🖊 ➖
☘ የሐቅ ጎá‹ŗናን áˆĩም ለሚá‹Ģጠፉ ☘
â€ĸ┈┈â€ĸâœŋ❁âœŋâ€ĸ┈┈â€ĸ
🍀 âļ ከáˆŊá‰Ĩር ጋር በተá‹Ģá‹Ģዘ 🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

⭕ī¸ áŠĨነሆ áˆŊá‰Ĩርተኝነá‰ĩና áŠĨáˆĩልምና ሆá‹ĩና ጀርá‰Ŗ የሆኑ ጠላá‰ļá‰Ŋ ናቸው❗ī¸ የቁርአን áŠĨና የሐዲáˆĩ ማáˆĩረጃዎá‰Ŋም áˆŊá‰Ĩርተኝነá‰ĩን የሚá‹Ģወግዙ መሆናቸው በá‰Ĩዙ መልኩ ይንፀá‰Ŗረቃልáĸ

አላህ በቁርአን ውáˆĩáŒĨ በአላህ ጎá‹ŗና ላይ በሚደረግ á‰ĩግል á‹ĩንበር áŠĨንá‹ŗናልፍ ይገáˆĩፀናልáĻ
ŲˆŲŽŲ‚ŲŽØ§ØĒŲŲ„ŲŲˆØ§ ŲŲŲŠ ØŗŲŽØ¨ŲŲŠŲ„Ų اŲ„Ų„Ų‘ŲŽŲ‡Ų اŲ„Ų‘ŲŽØ°ŲŲŠŲ†ŲŽ ŲŠŲŲ‚ŲŽØ§ØĒŲŲ„ŲŲˆŲ†ŲŽŲƒŲŲ…Ų’ ŲˆŲŽŲ„ŲŽØ§ ØĒŲŽØšŲ’ØĒŲŽØ¯ŲŲˆØ§ ۚ ØĨŲŲ†Ų‘ŲŽ اŲ„Ų„Ų‘ŲŽŲ‡ŲŽ Ų„ŲŽØ§ ŲŠŲØ­ŲØ¨Ų‘Ų اŲ„Ų’Ų…ŲØšŲ’ØĒŲŽØ¯ŲŲŠŲ†ŲŽ
በአላህ መንገá‹ĩ ላይ áŠĨነዚá‹Ģ የሚጋደሏá‰Ŋሁን ተጋደሉ ፤ á‹ĩንበርም áŠĨንá‹ŗá‰ŗልፉ፡፡ áŠĨነሆ አላህ á‹ĩንበር አላፊዎá‰Ŋን አይወá‹ĩም!
(ምዕáˆĢፍ 2 ፤ አንቀፅ 190)

⭕ī¸ ከዚህ አንቀፅና ከሌሎá‰Ŋም መሰል የቁርአን áŠĨና ሐዲáˆĩ መረጃዎá‰Ŋ áŠĨንደምንማረው ሙáˆĩሊሞá‰Ŋ áˆĩነáˆĩርአቱን የጠበቀ ፍልሚá‹Ģ የሚá‹ĢáŠĢሂዱ á‰ĸሆንም á‹ĩንበር ከማለፍ áŠĨንዲቆጠቡ á‰ŗዘዋል፡፡ የáˆŊá‰Ĩር áŒĨቃá‰ĩ ደግሞ á‹ĩንበር ከማለፍ ተግá‰ŖáˆĢá‰ĩ ውáˆĩáŒĨ ይመደá‰Ŗልና የተወገዘ መሆኑን ከዚህ áŠĨንረá‹ŗለን፡፡ áŠĨáˆĩልምና áŠĨና áˆŊá‰Ĩርተኝነá‰ĩ ጠላá‰ĩ መሆናቸውንም በዚህ áŠĨንገነዘá‰Ŗለን፡፡

⭕ī¸ áŠĨáˆĩልምናን ከáˆŊá‰Ĩር ጋር ለማá‹Ģá‹Ģዝ የሚሞክሩ ሰዎá‰Ŋ ቁርአን áŠĨና ሐዲáˆĩ ከዚህ አይነá‰ĩ አáˆĩተምህሮ የፀዱ መሆናቸውን ይወቁ❗ī¸

ዙል ቀዕá‹ŗህ 7 - 1441

አል - áŠĸáˆģáˆĢ á‰ģናል


➖ بØŗŲ… اŲ„Ų„Ų‡ اŲ„ØąØ­Ų…Ų† اŲ„ØąØ­ŲŠŲ… 🖊 ➖
☘☘ ሙáˆĩሊሞá‰Ŋ ሆይ! ☘☘
âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸
ኮሮና ከደረሰá‰Ŗá‰Ŋሁ አá‰ĨáˆŊሊ!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 ውዱ ነá‰ĸá‹Ģá‰Ŋን īˇē ከሙáˆĩሊሞá‰Ŋ መáŠĢከል ህመም የገጠመውን ሰው ሊጠይቁ ሲሄዱ áŠĨንዲህ ይሉ ነበር
âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸
‹á‰Ŋግር የለም!â€ē አላህ ከáˆģ የጠáˆĢህ á‰ĩሆናለህ!â€ē

🔘 ነá‰Ĩá‹Ģá‰Ŋን īˇē በዚህ መልኩ የá‰ŗመሙ ሙáˆĩሊሞá‰Ŋን á‹Ģፅናኑ áŠĨንደነበር áŠĸማም ቡáŠģáˆĒ በሐዲáˆĩ መዝገá‰Ŗቸው ላይ ዘግበውá‰ŗልáĸ

➡ī¸ 'የጠáˆĢህ á‰ĩሆናለህ' ሲሉ 'ከምን?' ከተá‰Ŗለ ---Âģ ከወንጀሎá‰Ŋ ነዋ!
🍀 አዎን! በአላህ መáˆēአ በáˆŊá‰ŗዎá‰Ŋ ከወንጀል ቆáˆģáˆģዎá‰Ŋ á‹ĢጠáˆĢሉ!
âŦ‡ī¸
🔘 á‰ŗዲá‹Ģ ምናልá‰Ŗá‰ĩም በኮሮና ወረርáˆēኝ መነáŠĢቱ ላጋጠማቸው ሙáˆĩሊሞá‰Ŋ የምናáˆĩተላልፈው መልáŠĨክá‰ĩ የነá‰Ĩá‹Ģá‰Ŋን ማፅናኛ ምáˆŗሌ ይሆናል
âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸
''‹á‰Ŋግር የለም!â€ē - አላህ ከáˆģው የጠáˆĢá‰Ŋሁ á‰ĩሆናላá‰Ŋሁ!''
Ų„ا بØŖØŗ ØˇŲ‡ŲˆØą ØĨŲ†Ø´Ø§ØĄ اŲ„Ų„Ų‡!
(Ø¨ØŽØ§ØąŲŠ)
🔘 á‰Ĩá‰ģ ግን áŠĸማናá‰Ŋሁን ጠá‰Ĩቁ❗ī¸
➡ī¸ ልá‰Ĩ አይá‰ŗመም áŠĨንጂ በáˆŊá‰ŗ á‹Ģለ ነው ዘመዴ!

🔘 ወረርáˆēኝም ሆነ በáŒĨቅሉ ማንኛውም በáˆŊá‰ŗ አማኞá‰Ŋ ወንጀል áŠĨንዲሰረዝላቸው ማá‹ĩረጉ የአላህን áŠĨዝነá‰ĩ á‹Ģáˆĩገነዝበናል፡፡ ወንጀሎá‰Ŋን ለማበáˆĩ ሁሌም ፍላጎá‰ĩ áŠĨንá‹ŗለውና መሃáˆĒ áŠĨንደሆነ á‹Ģáˆĩá‰ŗውሰናልáĸ

➡ī¸ ሰበá‰Ĩ áŠĨየፈለገ ወንጀሎá‰Ŋን የሚምር ጌá‰ŗ መሆኑ አá‰Ĩዝá‰ļ á‹Ģáˆĩመሰግነዋልáĸ
اŲ„Ø­Ų…د Ų„Ų„Ų‡ ØąØ¨ اŲ„ؚاŲ„Ų…ŲŠŲ†!
🔘 ወላሂ ፍጡሮቹ በመሆናá‰Ŋን á‰ŗá‹ĩለናል!

🌴 áˆĩለዚህ ሙáˆĩሊሞá‰Ŋ ሆይ!
âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸
ኮሮና áˆŗይመáŒŖ በፊá‰ĩ መጠንቀቁ á‰ĸá‹Ģáˆģም áŠĨንáŠŗ ምናልá‰Ŗá‰ĩ ከመáŒŖ ➡ī¸áŠ á‰ĨáˆŊሊ! ወንጀልን á‹Ģá‰Ĩáˆŗል áŠĸንáˆģአላህ! ☘ የተá‹Ģዙá‰Ĩንን አላህ ዓፊá‹Ģ á‹Ģá‹ĩርግልን፡፡

አል áŠĸáˆģáˆĢ


➖ بØŗŲ… اŲ„Ų„Ų‡ اŲ„ØąØ­Ų…Ų† اŲ„ØąØ­ŲŠŲ… 🖊 ➖
☘☘ áŠĸáˆģáˆĢ (áŒĨቆማ) ☘☘
â€ĸ┈┈â€ĸâœŋ❁âœŋâ€ĸ┈┈â€ĸ
🍀 ከá‰Ŗá‹ĩ ነገር ነው የገጠመን! 🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 የኮá‰Ēá‹ĩ ወረርáˆēኝ ከተከሰተ በኋላ ምናልá‰Ŗá‰ĩም የመáˆĩጊá‹ĩ áŠģዲሞá‰Ŋና ከነሱ ጋር የሚቀáˆĢረቡ አንá‹ŗንá‹ļá‰Ŋ áŠĢልሆኑ በቀር የተቀረው ሰው ከመáˆĩጊá‹ļá‰Ŋ ከáˆĢቀ ሰንበá‰ĩበá‰ĩ á‰Ĩሏልáĸ

🔘 በáˆŗምንá‰ŗዊው ዒá‹ŗá‰Ŋን ጁሙዓህ áŠĨንáŠŗ ወደ መáˆĩጊá‹ĩ መá‰ĩመማá‰Ŋን ቀርá‰ļá‰Ĩናልáĸ ቀላል ጉá‹ŗይ አይደለም ወገን! ፤ ከá‰Ŗá‹ĩ ነገር ነው የገጠመን!

➡ī¸ áŠĨንደው አላህ ይá‹ĩረáˆĩልንና ከá‹ĩሮውም የተáˆģልን ሰጋጆá‰Ŋ አá‹ĩርጎ ወደመáˆĩጊá‹ĩ ይመልሰንáĸ

አል áŠĸáˆģáˆĢ


★★★★★★★★★★★★

💎 ረሱል īˇē "ማንኛውም ሙáˆĩሊም ተክልን ተክሎ ወይም አዝርዕá‰ĩን ዘርá‰ļ ሲá‹Ģበቃ፤አህዋፍáŖሰዎá‰Ŋ ወይም áŠĨንáˆĩáˆŗá‰ĩ á‰ĸበሉለá‰ĩ ሰደቃ የሆኖ ይቆጠርለá‰ŗልáĸ "á‰Ĩለዋልáĸ


➖ بØŗŲ… اŲ„Ų„Ų‡ اŲ„ØąØ­Ų…Ų† اŲ„ØąØ­ŲŠŲ… 🖊 ➖
☘☘ áŠĸáˆģáˆĢ (áŒĨቆማ) ☘☘
â€ĸ┈┈â€ĸâœŋ❁âœŋâ€ĸ┈┈â€ĸ
🍀🍀 áŠĨንመለáˆŗለን! 🍀🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 የሰው ልጅ ሁሉ በሰáˆĢው áˆĩáˆĢ ፍርá‹ĩ ሊá‹Ģገኝ ወደ ጌá‰ŗው የሚመለáˆĩ መሆኑ ከá‰ŗላላቅ áŠĨውነá‰ŗዎá‰Ŋ መáŠĢከል ይመደá‰Ŗል፡፡ ይህ ጉá‹ŗይ áŠĨጅግ አንገá‰Ĩጋá‰ĸ ነውና በቁርአን áŠĨና ሐዲáˆĩ ላይ በá‰Ĩዙ መልኩ ተá‰ĨáˆĢርቷል
➡ī¸ አንዱን áŠĨናውáˆŗ
âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸
🔘 አላህ ØŗبحاŲ†Ų‡ ŲˆØĒؚاŲ„Ų‰ ሱረቱል á‹Ģሲንን በቋጨበá‰ĩ 83ኛው አንቀፅ ላይ áŠĨንዲህ ይለናል âŦ‡ī¸
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✴ī¸ŲŲŽØŗŲØ¨Ų’Ø­ŲŽØ§Ų†ŲŽ اŲ„Ų‘ŲŽØ°ŲŲŠ بŲŲŠŲŽØ¯ŲŲ‡Ų Ų…ŲŽŲ„ŲŽŲƒŲŲˆØĒŲ ŲƒŲŲ„Ų‘Ų Ø´ŲŽŲŠŲ’ØĄŲ ŲˆŲŽØĨŲŲ„ŲŽŲŠŲ’Ų‡Ų ØĒŲØąŲ’ØŦŲŽØšŲŲˆŲ†ŲŽ
✴ī¸ á‹Ģ የሁሉ ነገር áˆĩልáŒŖን በáŠĨጁ የሆነው ጌá‰ŗ áŒĨáˆĢá‰ĩ ይገá‰Ŗው ፤ ወደርሱም á‰ĩመለáˆŗላá‰Ŋሁ!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 አላህ ተመላáˆŊ መሆናá‰Ŋንን በዚህ መልኩ አáˆĩገንዝá‰Ļ ምዕáˆĢፉን ቋጭá‰ļá‰ŗል፡፡
➡ī¸ áŠĨጅግ á‹ĩንቅ አጨáˆĢረáˆĩ!
âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸
ግና áŠĢáˆĩá‰ŗወáˆĩን ነዋ!

አል áŠĸáˆģáˆĢ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
۞ Ų‚ŲŽØ§Ų„ŲŽØĒŲ اŲ„Ų’ØŖŲŽØšŲ’ØąŲŽØ§Ø¨Ų ØĸŲ…ŲŽŲ†Ų‘ŲŽØ§ ۖ Ų‚ŲŲ„ Ų„Ų‘ŲŽŲ…Ų’ ØĒŲØ¤Ų’Ų…ŲŲ†ŲŲˆØ§ ŲˆŲŽŲ„ŲŽŲ°ŲƒŲŲ† Ų‚ŲŲˆŲ„ŲŲˆØ§
ØŖŲŽØŗŲ’Ų„ŲŽŲ…Ų’Ų†ŲŽØ§ ŲˆŲŽŲ„ŲŽŲ…Ų‘ŲŽØ§ ŲŠŲŽØ¯Ų’ØŽŲŲ„Ų اŲ„Ų’ØĨŲŲŠŲ…ŲŽØ§Ų†Ų ŲŲŲŠ Ų‚ŲŲ„ŲŲˆØ¨ŲŲƒŲŲ…Ų’ ۖ ŲˆŲŽØĨŲŲ† ØĒŲØˇŲŲŠØšŲŲˆØ§ اŲ„Ų„Ų‘ŲŽŲ‡ŲŽ ŲˆŲŽØąŲŽØŗŲŲˆŲ„ŲŽŲ‡Ų Ų„ŲŽØ§ ŲŠŲŽŲ„ŲØĒŲ’ŲƒŲŲ… Ų…Ų‘ŲŲ†Ų’ ØŖŲŽØšŲ’Ų…ŲŽØ§Ų„ŲŲƒŲŲ…Ų’ Ø´ŲŽŲŠŲ’ØĻŲ‹Ø§ ۚ ØĨŲŲ†Ų‘ŲŽ اŲ„Ų„Ų‘ŲŽŲ‡ŲŽ ØēŲŽŲŲŲˆØąŲŒ ØąŲ‘ŲŽØ­ŲŲŠŲ…ŲŒ

════ ¤❁âœŋ❁¤ ════

✨ የዐረá‰Ĩ ዘላኖá‰Ŋ ÂĢአምነናልÂģ አሉ፡፡ ÂĢአላመናá‰Ŋሁም፤ ግን ሰልመናል በሉ፡፡ ÂĢáŠĨምነቱም በልá‰Ļá‰ģá‰Ŋሁ ውáˆĩáŒĨ ገና (ጠልቆ) አልገá‰Ŗም፡፡ አላህንና መልክተኛውንም á‰Ĩá‰ĩá‰ŗዘዙ ከáˆĨáˆĢዎá‰ģá‰Ŋሁ ምንንም አá‹Ģጎá‹ĩልá‰Ŗá‰Ŋሁም፡፡ አላህ መሓáˆĒ አዛኝ ነውናÂģ በላቸው፡፡

http://t.me/MewedaChannel


➖ بØŗŲ… اŲ„Ų„Ų‡ اŲ„ØąØ­Ų…Ų† اŲ„ØąØ­ŲŠŲ… 🖊 ➖
☘ áŠĸáˆĩላማዊው የሂጅáˆĢ áŠĢላንደር ☘
â€ĸ┈┈â€ĸâœŋ❁âœŋâ€ĸ┈┈â€ĸ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 የሂጅáˆĢ áŠĢላንደር የነá‰Ĩá‹Ģá‰Ŋንን īˇē ከመáŠĢ ወደ መዲና የተደረገ áˆĩደá‰ĩ መሰረá‰ĩ á‹Ģደረገ ሲሆን 12 ወáˆĢá‰ĩን ይይዛል፡፡

🔘 ይህ የነá‰Ĩá‹Ģá‰Ŋን īˇē ከመáŠĢ ወደ መዲና የተደረገ áˆĩደá‰ĩ የተፈፀመው áŠĨንደ ጎርጎሮáˆŗውá‹Ģን የዘመን አቆáŒŖጠር በ 622 ዓ.ል ሲሆን ይህ ክáˆĩተá‰ĩ ለሂጅáˆĢ የዘመን አቆáŒŖጠር áŠĨንደ መነáˆģ ተደርጎ ይወሰá‹ŗል፡፡

🔘 ሂጅáˆĢ የሚለው ቃል 'áˆĩደá‰ĩ' የሚል á‰ĩርጓሜን የሚሰáŒĨ ሲሆን በዚህ áŠĢላንደር áˆĩá‹Ģሜ ላይ á‹Ģረፈበá‰ĩ አገá‰Ŗá‰Ĩ ይህንኑ áˆĩደá‰ĩ á‹Ģመላክá‰ŗል፡፡

🔘 የሂጅáˆĢ አቆáŒŖጠር የወáˆĢá‰ĩ ቅደም ተከተል የሚከተለውን ይመáˆĩላል
âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸âŦ‡ī¸
âļ ሙሐረም
❷ ሰፈር
❸ ረá‰ĸዓል አወል
❚ ረá‰ĸዓ áˆŖኒ
âē ጁማደል አወል
âģ ጁማደ áˆŖኒ
âŧ ረጀá‰Ĩ
âŊ ሸዕá‰Ŗን
❞ ረመá‹ŗን
âŋ ሸዋል
â“Ģ ዙል ቂዕá‹ŗህ
â“Ŧ ዙል ሒጃህ

አል áŠĸáˆģáˆĢ


➖ بØŗŲ… اŲ„Ų„Ų‡ اŲ„ØąØ­Ų…Ų† اŲ„ØąØ­ŲŠŲ… 🖊 ➖
🍀🍀🍀
áŠĨáˆĩልምናን በገንዘá‰Ĩ ማáˆĩቆም አይá‰ģልም
â€ĸ┈┈â€ĸâœŋ❁âœŋâ€ĸ┈┈â€ĸ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 በገንዘá‰Ĩና በቁáˆŗቁáˆĩ áŠĨርá‹ŗá‰ŗ በኩል አá‹ĩርገው áŠĨáˆĩልምናን ለማáŒĨፋá‰ĩ የሚሞክሩ ሰዎá‰Ŋ በአንá‹ĩ በኩል ሙáˆĩሊሞá‰Ŋን ከዲናቸው ለመጎተá‰ĩ ሲáŒŖáŒŖሊ ይáˆĩተዋላሉáĸ በሌላ በኩል ደግሞ ለክህደá‰ĩ áŠĨንቅáˆĩቃሴዎá‰Ŋ የገንዘá‰Ĩ áŠĨርá‹ŗá‰ŗ በማá‹ĩረግ ክህደá‰ĩ ከáŠĨáˆĩልምና በላይ áŠĨንዲá‹ĢንሰáˆĢáˆĢ ለማá‹ĩረግ ይንቀáˆŗቀáˆŗሉ፡፡

🔘 ይህ የáŒĨፋá‰ĩ áŠĨንቅáˆĩቃሴ በነበሩበá‰ĩ የáŒĨፋá‰ĩ ጎá‹ŗና ላይ á‹ĩርá‰Ĩ áŒĨፋá‰ĩ ሆኖ ጉá‹ŗá‰ĩ የሚጨምርá‰Ŗቸው መሆኑን á‰ĸገነዘቡ መልáŠĢም ነበርáĸ ግና ለዚህ አልá‰ŗደሉምና ገንዘá‰Ŗቸውን በማፍሰáˆĩ áŠĨáˆĩልምናን የማá‹ŗከም ሙከáˆĢን á‹Ģደርጋሉ፡፡ አላህ ሂá‹ŗá‹Ģ ይáˆĩáŒŖቸው!

🔘 ይህን ተግá‰ŖáˆĢቸውን አáˆĩመልክá‰ļ አላህ በቁርአኑ በሱረቱል አንፋል 36ኛው አንቀፅ ላይ áŠĨንዲህ ይለናልáĻ

🔆 ØĨŲŲ†Ų‘ŲŽ اŲ„Ų‘ŲŽØ°ŲŲŠŲ†ŲŽ ŲƒŲŽŲŲŽØąŲŲˆØ§ ŲŠŲŲ†ŲŲŲ‚ŲŲˆŲ†ŲŽ ØŖŲŽŲ…Ų’ŲˆŲŽØ§Ų„ŲŽŲ‡ŲŲ…Ų’ Ų„ŲŲŠŲŽØĩŲØ¯Ų‘ŲŲˆØ§ ØšŲŽŲ† ØŗŲŽØ¨ŲŲŠŲ„Ų اŲ„Ų„Ų‘ŲŽŲ‡Ų ۚ ŲŲŽØŗŲŽŲŠŲŲ†ŲŲŲ‚ŲŲˆŲ†ŲŽŲ‡ŲŽØ§ ØĢŲŲ…Ų‘ŲŽ ØĒŲŽŲƒŲŲˆŲ†Ų ØšŲŽŲ„ŲŽŲŠŲ’Ų‡ŲŲ…Ų’ Ø­ŲŽØŗŲ’ØąŲŽØŠŲ‹ ØĢŲŲ…Ų‘ŲŽ ŲŠŲØēŲ’Ų„ŲŽØ¨ŲŲˆŲ†ŲŽ
🔆 áŠĨነዚá‹Ģ የáŠĢዱá‰ĩ ከአላህ መንገá‹ĩ ሊከለክሉ ገንዘá‰Ŗቸውን á‹ĢወáŒŖሉáĸ በáŠĨርግáŒĨም á‹Ģወጧá‰ŗል áŖ ከዚá‹Ģም በáŠĨነሱ ላይ ፀፀá‰ĩ á‰ĩሆንá‰Ŗቸዋለá‰Ŋ! áŖ ከዚá‹Ģም ይሸነፋሉ!

🔘 ከዚህ አንቀፅ áŠĨንደምንረá‹ŗው የአላህን ዲን ለማá‹ŗከም ገንዘá‰Ĩ ማውáŒŖá‰ŗቸው ፀፀá‰ĩ ላይ á‹Ģደርáˆŗቸዋል፡፡

🔘 ፀፀá‰ŗቸው በá‰Ĩዙ መገለáŒĢዎá‰Ŋ áŠĨውን የሚሆን ሲሆን ከነዚህ መáŠĢከል áŠĨንá‹ŗሃáˆŗá‰Ŗቸውና áŠĨንደምኞá‰ŗቸው áŠĨáˆĩልምናን ማáˆĩቆም á‰Ŗለመá‰ģላቸው የሚደርáˆĩá‰Ŗቸው የቁጭá‰ĩ ፀፀá‰ĩ ይገኝበá‰ŗልáĸ

🔘 áŠĨáˆĩልምና የአላህ á‰Ĩርሃን áŠĨንደመሆኑ መጠን ሊá‹Ģáˆĩቆሙá‰ĩ የሚá‰ģላቸው አይደለምና ሁሌም áŠĨንደበáˆĢ ይቀáŒĨላል❗ī¸

🔘 ዋናው ፀፀá‰ŗቸው የሚሆነው ግን ምናልá‰Ŗá‰ĩም ወደ áŠĨáˆĩልምና የመግá‰Ŗá‰ĩ áŠĨá‹ĩሉን áˆŗá‹Ģገኙ ሞá‰ĩን የቀመሱ áŠĨንደሆን በገንዘá‰Ŗቸው ይሰሩá‰ĩ የነበረው áˆĩáˆĢ በቂá‹Ģም ቀን ከፊá‰ĩ ለፊá‰ŗቸው በሚቀርá‰Ĩበá‰ĩ ጊዜ ይሆናልáĸ áŠĨንዲህ á‹Ģለ የክህደá‰ĩ á‹ĩርጊá‰ĩ ደግሞ áŠĨáˆŗá‰ĩ ውáˆĩáŒĨ መኖርን የሚá‹Ģáˆĩከá‰ĩል መሆኑ በá‰Ĩዙ ማáˆĩረጃዎá‰Ŋ ተá‰ĨáˆĢርá‰ļልናል፡፡ ይህንን አáˆĩመልክá‰ļ ከላይ የጠቀáˆĩነው አንቀፅ መጨረáˆģ ላይ አላህ áŠĨንዲህ ይላል áĻ

🔆 ŲˆŲŽØ§Ų„Ų‘ŲŽØ°ŲŲŠŲ†ŲŽ ŲƒŲŽŲŲŽØąŲŲˆØ§ ØĨŲŲ„ŲŽŲ‰Ų° ØŦŲŽŲ‡ŲŽŲ†Ų‘ŲŽŲ…ŲŽ ŲŠŲØ­Ų’Ø´ŲŽØąŲŲˆŲ†ŲŽ
🔆 áŠĨነዚá‹Ģም የáŠĢዱá‰ĩ ወደ ገሀነም ይሰበሰá‰Ŗሉ!

🔘 ይህ አንቀፅ በዚህ መልኩ የተጠናቀቀው ከáŠĨáˆĩልምና መንገá‹ĩ ሰዎá‰Ŋን ለማዘናጋá‰ĩ ገንዘá‰Ĩ የሚá‹Ģወጡá‰ĩ ሰዎá‰Ŋ ከመጠቀáˆŗቸው ቀáŒĨሎ መሆኑ ይህን መሰል ተግá‰Ŗር ላይ ለሚáˆŗተፉ በሙሉ ማáˆĩፈáˆĢáˆĒá‹Ģና ዛá‰ģ á‹Ģዘለ áŠĨንዲሆን á‹Ģደርገዋል፡፡ በዚሁ የክህደá‰ĩ áŠĨንቅáˆĩቃሴ ላይ ለሚቀáŒĨሉና የአላህን መሃáˆĒነá‰ĩ ለማይá‰ŗደሉ ሁሉ የፍፃሜá‹Ģቸው á‰ĩምá‰ĸá‰ĩ ሆኖ በቁርአን ላይ ሰፍሮ ይቆá‹Ģል፡፡

➡ī¸ ማን ከሰረ á‰ŗዲá‹Ģ⁉ī¸

አል-áŠĸáˆģáˆĢ


Forward from: መወá‹ŗ á‰ģናል(MEWEDA CHANNEL)
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
#ቀለበá‰ŗዊ የፀሐይ ግርá‹ļáˆŊ ሲከሰá‰ĩ ❗ī¸

★★★★★★★★★★★★

✨ ይህ አይነá‰ĩ ክáˆĩተá‰ĩ ሲከሰá‰ĩ አላህ á‰Ŗሮቹን የሚá‹ĢሰፈáˆĢáˆĢበá‰ĩ ነውና በá‹ĩንጋጤ ወደ ሰላá‰ĩáŖዱዓ ወደ ማá‹ĩረግና ሰደቃ ወደ መáˆĩጠá‰ĩ ...ተá‰ģኮሉ ነበር የተá‰Ŗልነው !!!

⚡ī¸áˆáŠ•áŠ› á‹Ģማረ áŠĨምነá‰ĩ 👉áŠĸáˆĩላም
★★★★★★★★★★★★

✨ አይገርምም ክáˆĩተቱን áŠĨንደመዝናኛ ቆáŒĨሎ áŖየፕሌን ከፍሎáŖ #ላሊበላ á‹ĩረáˆĩ መሄá‹ĩ!!!

☀ī¸áŠ áˆ‹áˆ… አቅላá‰Ŋንን አይገልá‰ĨáŒĨá‰Ĩን

ይቀላቀሉን 👇👇👇
Http://t.me/MewedaChannel


➖ بØŗŲ… اŲ„Ų„Ų‡ اŲ„ØąØ­Ų…Ų† اŲ„ØąØ­ŲŠŲ… 🖊 ➖
☘☘ አል-áŠĸáˆģáˆĢ (áŒĨቆማ) ☘☘
â€ĸ┈┈â€ĸâœŋ❁âœŋâ€ĸ┈┈â€ĸ
🍀🍀 በግርá‹ļáˆŊ ጊዜ 🍀🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 ቁተይá‰Ŗህ áŠĸá‰Ĩኑ ሰዒá‹ĩ (ØąØļŲŠ اŲ„Ų„Ų‡ ØšŲ†Ų‡) በዘገቡá‰ĩ ሐዲáˆĩ á‹ĩንቁ ነá‰Ĩá‹Ģá‰Ŋን ነá‰Ĩዩ መሐመá‹ĩ īˇē áŠĨንዲህ ማለá‰ŗቸውን ተናግረዋልáĻ
đŸ’Ŧ "ØĨŲŲ†Ų‘ŲŽ اŲ„Ø´Ų‘ŲŽŲ…Ų’ØŗŲŽ ŲˆŲŽØ§Ų„Ų’Ų‚ŲŽŲ…ŲŽØąŲŽ ØĸŲŠŲŽØĒŲŽØ§Ų†Ų Ų…ŲŲ†Ų’ ØĸŲŠŲŽØ§ØĒŲ اŲ„Ų„Ų‡ŲØŒ ŲˆŲŽØĨŲŲ†Ų‘ŲŽŲ‡ŲŲ…ŲŽØ§ Ų„ŲŽØ§ ŲŠŲŽŲ†Ų’ØŽŲŽØŗŲŲŲŽØ§Ų†Ų Ų„ŲŲ…ŲŽŲˆŲ’ØĒŲ ØŖŲŽØ­ŲŽØ¯ŲØŒ ŲˆŲŽŲ„ŲŽØ§ Ų„ŲØ­ŲŽŲŠŲŽØ§ØĒŲŲ‡ŲØŒ ŲŲŽØĨŲØ°ŲŽØ§ ØąŲŽØŖŲŽŲŠŲ’ØĒŲŲ…ŲŲˆŲ‡ŲŲ…ŲŽØ§ ŲŲŽŲƒŲŽØ¨Ų‘ŲØąŲŲˆØ§ØŒ ŲˆŲŽØ§Ø¯Ų’ØšŲŲˆØ§ اŲ„Ų„Ų‡ŲŽ ŲˆŲŽØĩŲŽŲ„Ų‘ŲŲˆØ§ ŲˆŲŽØĒŲŽØĩŲŽØ¯Ų‘ŲŽŲ‚ŲŲˆØ§..."

đŸ’Ŧ "በርግáŒĨም ፀሀይና ጨረቃ ከአላህ ምልክá‰ļá‰Ŋ ናቸው፡፡ áŠĨነሱም ለአንá‹ĩ ሰው ሞá‰ĩ ወይንም ህይወá‰ĩ ሲá‰Ŗል አይጋረዱም፡፡ á‰Ŗá‹Ģá‰Ŋኋቸው ጊዜ ተክá‰ĸáˆĢ አá‹ĩርጉ (አላሁ አክበር በሉ) áŖ አላህንም ለምኑ áŖ áˆĩገዱም áŖ ምፅዋá‰ĩንም áˆĩጡ..."

አል-áŠĸáˆģáˆĢ á‰ģናል
@yenebiyatwrs


☀ī¸áŠĨናá‰ŗá‰Ŋን አዒáˆģ (አላህ áˆĩáˆĢዋን ይውደá‹ĩ) ዘንá‹ĩ የተወሰኑ ሴá‰ļá‰Ŋ áˆĩáˆĩ ልá‰Ĩáˆĩ ለá‰Ĩሰው ገቡáĸ

✨áŠĨንዲህ አለá‰ģቸው áĻ "አማኝ ሴá‰ļá‰Ŋ ከሆናቹህ ይህ የለበáˆŗá‰Ŋሁá‰ĩ ልá‰Ĩáˆĩ የአማኝ ሴá‰ļá‰Ŋ አይደለምáĸ"


ØĒŲØŗŲŠØą اŲ„Ų‚ØąØˇØ¨ŲŠ ŲĄŲ¤| ŲĸŲ¤Ų¤ 📂


@yenebiyatwrs

አል—áŠĸáˆģáˆĢ á‰ģናል ይቀላቀሉን!!!!


☀ī¸ አላህ (ሱ·ወ) áŠĨáˆĩልምናን ለኛ áŠĨኛንም ለáŠĨáˆĩልምና በመምረጡ ፤ áŠĨሹ ዘንá‹ĩ á‰Ĩቸኛው áŠĨና ተቀá‰Ŗይነá‰ĩ á‹Ģለው ዲን በማá‹ĩረጉ ምáˆĩጋና ይገá‰Ŗው áĸ

☀ī¸ áŠĨáˆĩልምናን ለአለም በማá‹ĩረáˆĩ ለተላኩá‰ĩ áŠĨና የነá‰ĸá‹Ģá‰ļá‰Ŋ መደምደሚá‹Ģ በሆኑá‰ĩ በÂĢሙሀመá‹ĩÂģ ላይም የአላህ ሰላም ይáˆĩፈን áĸ

☀ī¸ የሰው ልጆá‰Ŋ ከተፈጠሩበá‰ĩ áŠĨለá‰ĩ አንáˆĩá‰ļ ዓለም áŠĨáˆĩከምá‰ĩጠፋበá‰ĩ ቀን á‹ĩረáˆĩ ሰዎá‰Ŋ áŠĨንዲጓዙበá‰ĩ ከፈáŒŖáˆĒá‹Ģቸው የá‰ŗዘዙበá‰ĩ áŠĨምነá‰ĩ * áŠĸáˆĩላም * ነው áĸ

☀ī¸ ይህ áˆĩርዓá‰ĩ ዱንá‹Ģ ላይ ለሰዎá‰Ŋ አáˆĩፈላጊ የሆኑ ነገሮá‰Ŋን በሙሉ ጠቅልሎ የá‹Ģዘ ከመሆኑም በተጨማáˆĒ፤ በቀáŒŖዩም ዓለም ( በአáŠēáˆĢ) በምንም ሊተመን የማይá‰Ŋል áˆŊልማá‰ĩና ደáˆĩá‰ŗ የሚá‹Ģáˆĩገኝ ነው áĸ

☀ī¸ በተቃáˆĢኒው ይህንን áˆĩርዓá‰ĩ á‰Ŗልተቀበለና á‰Ŗልተከተለ ላይ ደግሞ ማá‰Ĩቂá‹Ģም ሆነ áŠĨረፍá‰ĩ በሌለው አáˆŗማሚ ቅáŒŖá‰ĩ ይáˆĩተናገá‹ŗል áĸ

☀ī¸á‰ áˆŒáˆ‹ አá‰Ŗá‰Ŗል በሁለመናቸው ሙáˆĩሊም ለሆኑ ‘ ጀነá‰ĩ’ áŠĸáˆĩላምን ላልተቀበሉ ደግሞ ‘ ጀሀነም ’ የተá‰Ŗለ ሀገርን á‹Ģዘጋጀ áˆĩርዓá‰ĩ ነው áĸ

☀ī¸ ማንኛውም ሰው "ሙáˆĩሊም " ነኝ በማለቱ á‰Ĩá‰ģ ወይም ደግሞ የሙáˆĩሊም áˆĩም በመጠቀሙ á‰Ĩá‰ģ ‘ጀነá‰ĩን’ á‹Ģገኛል ማለá‰ĩ አይደለም!!!

☀ī¸ በመሆኑም የዱንá‹Ģንም ሆነ የአáŠŧáˆĢን áˆĩáŠŦá‰ĩ ለመቀá‹ŗጀá‰ĩ áŠĸáˆĩላም á‹Ģዘዘውን መá‰ŗዘዝ áŖ የከለከለውን መከልከል የግá‹ĩ ይላል áĸ

☀ī¸ አላህ (ሹ¡ ወ) ለሰው ልጆá‰Ŋ በየጊዜው #መፅሀፍá‰ĩን በማውረá‹ĩ áŖ ነá‰ĸá‹Ģá‰ĩን በመላክáŖ áŠĨነዚህንም ነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ á‰ĩዕዛዛá‰ĩንና ክልከላዎá‰Ŋን áŠĨንዲá‹Ģáˆĩተምሩ በማá‹ĩረግ በአጠቃላይ የሚá‹ĩኑበá‰ĩን መንገá‹ĩ á‹Ģáˆŗá‹Ģቸዋል áĸ

☀ī¸áˆˆá‹šáˆ… ኡመá‰ĩ ( ህዝá‰Ĩ) ደግሞ የቀደሙá‰ĩን መፅሀፍá‰ļá‰Ŋ የሚáˆŊር ÂĢ ቁርአንÂģ ፤ የነá‰ĸá‹Ģá‰ļá‰Ŋ መቋáŒĢ አá‹ĩርጎ ÂĢሙሀመá‹ĩንÂģ አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ልኮልናል áĸ

☀ī¸ አልሀምዱሊላህ â€ŧ ይህም ማለá‰ĩ የáŠĨáˆĩልምና ምንጮá‰Ŋ ÂĢ ቁርአንÂģ áŠĨና ÂĢ የá‰ŗላቁ ነá‰ĸይ "ሱና"Âģ á‰Ĩá‰ģ ናቸው ማለá‰ĩ ነው áĸ

☀ī¸ ከነዚህ ሁለቱ ምንጮá‰Ŋ áŠĨንደተገኘው áŠĨáˆĩልምና ከአምáˆĩá‰ĩ [ 5] ነገáˆĢá‰ļá‰Ŋ የተገነá‰Ŗ ነው áĸ

áŠĨነርሱም áĻ
① ከአላህ በቀር በáŠĨውነá‰ĩ የሚገዙá‰ĩ አምላክ áŠĨንደሌለ ሙሀመá‹ĩም ( አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ) የአላህ á‰Ŗርá‹Ģ( ፍጡር): áŠĨና መልዕክተኛው መሆናቸውን መመáˆĩከር áŖ

② “ሰላá‰ĩን ” በተከá‰ŗá‰ŗይነá‰ĩ መáˆĩገá‹ĩ áŖ

â‘ĸ "ዘáŠĢን" መáˆĩጠá‰ĩ áŖ

â‘Ŗ " ረመዷንን ” መፆም áŠĨና

⑤ ለá‰ģለ ሰው “ሀጅን” ማá‹ĩረግ ናቸው áĸ

@yenebiyatwrs


â€ĸđŸ’Ĩ"በኔ ላይ አንá‹ĩ ሰለዋá‰ĩ á‹Ģወረደ አላህ በáŠĨርሹ ላይ አáˆĩር ጊዜ ሰለዋá‰ĩ á‹Ģወርá‹ĩበá‰ŗልáĸ"
ረሱል īˇē

ÂĢ اŲ„Ų„Ų‘ŲŽŲ‡ŲŲ…Ų‘ŲŽ ØĩŲŽŲ„ŲŲ‘ ŲˆŲŽØŗŲŽŲ„ŲŲ… ØšŲŽŲ„ŲŽŲ‰ Ų†ŲŽØ¨ŲŲŠŲ†ŲŽØ§ Ų…ŲØ­ŲŽŲ…Ų‘ŲŽØ¯
Ų’ īˇē Âģ.
★★★★★★★★★★

ÂĢ اŲ„Ų„Ų‡Ų… ØĩŲ„ ŲˆØŗŲ„Ų… ŲˆØ¨Ø§ØąŲƒ ØšŲ„Ų‰ Ų†Ø¨ŲŠŲ†Ø§ Ų…Ø­Ų…د īˇēÂģ

📖✏ī¸đŸ“œ
.
â€ĸ┈┈â€ĸ ❀ 🍃🌸🍃 ❀ â€ĸ┈┈â€ĸ


🔹የቁርአን ግá‰Ĩá‹Ŗ 🔹

🎙 khalifah At-Tonaeijy

💎 ሱረቱል ሒጅር

@MewedaChannel


ለአንá‹ĩ ወር የሚቆይ ልዩ የሸáˆĒዓ ኮርáˆĩ በነሲሓ ቲá‰Ē ከዛáˆŦ ሰኔ 9/2012 ከ10: 00 ጀምሮ

💎 ነሲሓ ቁርáŠŖን ቤá‰ĩ 💎

📚ቃዒደቱ ኑáˆĢኒá‹Ģህ

đŸ“ē በኡáˆĩá‰ŗዝ ሑሴን ሙንደá‰ŗ

📚 የቁርáŠŖን ሀልቃ

đŸ“ē በኡáˆĩá‰ŗዝ ሚፍá‰ŗህ ኑáˆĒ

💎 የነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ ውርáˆĩ 💎

📚 áŠĒá‰ŗቡ ተውሒá‹ĩ

đŸ“ē በሸይáŠŊ áŠģሊá‹ĩ ዐá‰ĨዱለáŒĸፍ

📚 áŠĒá‰ŗቡ ሰላá‰ĩ

đŸ“ē በሸይáŠŊ ኸሊል ሐሚá‹ĩ ኸሊል

📚 መንዙመቱል ፊቅህá‹Ģ

đŸ“ē በሸይáŠŊ áŠĸልá‹Ģáˆĩ አሕመá‹ĩ

💎 ነሲሓ መሰረá‰ŗዊ 💎

📚 የዓቂá‹ŗ á‰ĩምህርá‰ĩ

đŸ“ē በኡáˆĩá‰ŗዝ ሙሐመá‹ĩ ሐሰን ማሜ

📚 ቀዋዒዱል አርበዓ

đŸ“ē በኡáˆĩá‰ŗዝ ሱልáŒŖን ኸá‹ĩር

📚 አዱሩሱል ሙሒማህ

đŸ“ē በá‹ļ/ር ዐá‰Ĩዱ ኸይáˆŦ

💎 ነሲሓ ለáŠĨህá‰ļá‰Ŋ 💎

📚 የተፈáŒĨሎ ደም áŠĨና ሸáˆĒዓዊ ህግጋá‰ļቹ

đŸ“ē በኡáˆĩá‰ŗዝ ሙሐመá‹ĩ ሐሰን ማሜ

📚 የጋá‰Ĩá‰ģ áŠĨና ፍá‰ē ህግጋá‰ĩ

đŸ“ē በኡáˆĩá‰ŗዝ ሙሐመá‹ĩ ሐሰን ማሜ

@yenebiyatwrs


⚡ī¸áŠá‰Ĩዩ īˇē አንá‹ĩ ሰው ለቤተሰቡ አáˆĩá‰Ļ የሚá‹ĢወáŒŖው ወáŒĒ áŠĨንደ ሰደቃ ይቆጠርለá‰ŗልáĸ

Http://t.me/yenebiyatwrs


💎የአደá‰Ŗá‰Ŗይ áŒĨáˆĒ ነá‰Ĩá‹Ģዊ á‰ĩውፊá‰ĩ!💎


☞ነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ አውነተኛ ወደ ሆነው ቅናá‰ģ á‹ĩምፃቸውን ከፍ አርገው በየገበá‹ĢውáŖ በየአደá‰Ŗá‰Ŗዩና ሰው በተሰበሰበበá‰ĩ áˆĩፍáˆĢ ሁሉ áŒĨáˆĒá‹Ģቸው አጉልተው á‹Ģሰሙ ነበርáĸ ይህን የተቀደሰ áŒĨáˆĒ ከፊሉ ሲቀበል ከፊሉ ይáˆŗለቅበá‰ŗልáĸ ከፊሉ áŒĨáˆĒውን ላለመáˆĩማá‰ĩ በልá‰Ĩáˆļቹ ይከናነá‰Ŗልáĸ ከፊሉ ይዘልፋቸዋል ይá‰Ĩáˆĩ á‰Ĩሎም ይገፈá‰ĩáˆĢቸዋልáĸ

☞ይህ ሁሉ የሚደርáˆĩá‰Ŗቸው áŠĨኔና አንተን የመሰሉ áŒĢማá‰Ŋን ተረገጠ á‰Ĩለው "ዘáˆĢፍ!" የሚሉ á‰ĩንንáˆŊ áˆĩá‰ĨáŠĨናዎá‰Ŋ አይደሉምáĸ áŠĨጅግ የተከበሩ የአለማቱ ጌá‰ŗን መá‹ĩህን ለአደም ልጅ ለማደረáˆĩ መርጧቸው ቃሉን በልáˆŗናቸው ላይ á‹Ģኖረ ክቡáˆĢን ነá‰Ĩá‹Ģá‰ļá‰Ŋ ናቸውáĸ

☞የአደá‰Ŗá‰Ŗይ ሰበáŠĢ áŒĨንá‰ŗዊ የነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ ፋና የቅኖá‰Ŋ ልማá‹ĩ ነበርáĸ መለኮá‰ŗዊ áŠĨዝነá‰ĩን ለፍጡር á‹Ģነገበው áŒĨáˆĒá‹Ģቸው ዘልቆ ጆሮáŠŖቸው ደርáˆļ ልá‰Ļናቸው ይመሩ ዘንá‹ĩ á‹ĩምፃቸው áŠĨረፍá‰ĩ የለውምáĸ ይሰማልáĸ

☞ከገበá‹Ģው መሀል ሰው ከተሰበሰበበá‰ĩ ሁሉ ሰተá‰ĩ á‰Ĩሎ ይዘልቃልáĸ "ህዝá‰Ļá‰ŧ ሆይ! ጌá‰ŗቹህ አሏህ ነው ከሱ ሌላ áŠĨውነተኛ አምላክ የላá‰Ŋሁም!" የምá‰ĩለው የተውሒá‹ĩ ቃል ከአንደበá‰ŗቸው ጎልá‰ŗ á‰ĩሰማለá‰Ŋáĸ

☞ይህá‰ēን ቃል ሸምá‰ļ የመáŒŖ የáŠĨውነá‰ĩ ከንግዱ á‹Ģተረፈ áˆĩáŠŦá‰ŗማ ሸማá‰Ŋ አልá‹Ģም ነጋዴ ነውáĸ áŠĨነዛ በነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ áŒĨáˆĒ የተሞሉ ገበá‹Ģዎá‰Ŋና አደá‰Ŗá‰Ŗዮá‰Ŋ ዛáˆŦ á‰ŗáˆĒክ áŠĨንጂ ህዋáˆĩ አይደርáˆĩá‰Ŗቸውምáĸ የá‹ĩምፆቹ አáˆģáˆĢ በህሊናá‰Ŋን á‰ĸኖርምáŖ ፈለጋቸው á‰ĸá‰ŗየንም ከጆሮáŠŖá‰Ŋን ግን ርቋልáĸ ንግá‹ŗቸውም ከáˆĩሟልáĸ ለዘልáŠŖለም á‹Ģተረፉá‰ĩ የነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ áŒĨáˆĒዎá‰Ŋን በቅን ልá‰Ļናና በáˆĩል ምልከá‰ŗ የተቀበሉ á‰ĩጉኃን á‰Ĩá‰ģ ናቸውáĸ

☞ከá‹ŗንáŠĒáˆĢና ዘፈን ከማáˆĩá‰ŗወቂና ክህደá‰ĩ ጩኸá‰ĩ የነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ áŒĨáˆĒ የረበሸው ከንቱ á‰ĩውልá‹ĩ ላይ ነህና áŠĨንá‹ŗá‹Ģሰናክሉህ!! á‹ĩምፅህን የናፈቁ የተዘጉ ልá‰Ļá‰Ŋ አሉና በአላህ ፈቃá‹ĩ á‰ĩከፍá‰ŗቸዋለህáĸ

☞የነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ áŒĨáˆĒ ከቧልá‰ĩና ዛዛá‰ŗ ይልቅ ከሰዎá‰Ŋ ልá‰Ĩ ሰርፃ á‰ĩገá‰Ŗለá‰Ŋáĸ ፍáˆŦን á‰ŗፈáˆĢለá‰Ŋáĸ á‹Ģኔ ጆሮን የሚá‹Ģውኩ ሰይáŒŖናዊ á‹ĩምፆá‰Ŋ ይተናሉáĸ ምን አልá‰Ŗá‰ĩ ላይመለሱ ይሸáˆģሉáĸ ግና ይህ የነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ የáˆĩá‰Ĩከá‰ĩ áˆĩልá‰ĩ በግዜ ሂደá‰ĩ በሚገáŒĨሙá‰ĩ áŠĨክሎá‰Ŋና á‹ĩክመá‰ļá‰Ŋ áŠĨየተመናመነ ሊጠፋ áŒĢፍ ደርሷልáĸ አንá‹ŗንá‹ĩ áŒĨቂá‰ĩ ወንá‹ĩሞá‰Ŋ ፋና ወጊ ሆነው á‰ĸጀምሩá‰ĩም ቅሉ ጠላá‰ĩን አፍርቷልáĸ ይህ ነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ የሚገáŒĨማቸው ፈተና ነውና ፅናቱን ተላበሱáĸ ህዝቤም ይመáˆĢልና! ከጨለማው á‰Ĩርሃን የናፈቀው የሰይáŒŖን ሲáˆŗይ á‰ŗገኘዋለህና በርá‰ŗáĸ


☞የኑሕ ምዕáˆĢፍ የነá‰Ĩá‹Ģá‰ĩ áŒĨáˆĒ á‰ŗላቁ ማáˆŗá‹Ģ የተከበረው ቁርአን ምዕáˆĢፍ 71!

71) ኑሕáŖ (የኑሕ ምዕáˆĢፍ)
┈┈â€ĸâ€ĸâ€ĸâœŋ❒🌹❒âœŋâ€ĸâ€ĸâ€ĸ┈┈

71:1 - áŠĨኛ ኑሕን ÂĢሕዝá‰Ļá‰Ŋህን አáˆŗማሚ ቅáŒŖá‰ĩ áˆŗይመáŒŖá‰Ŗቸው በፊá‰ĩ አáˆĩጠንቅቅ በማለá‰ĩ ወደ ሕዝá‰Ļቹ ላክነው፡፡Âģīŋŧ

71:2 - (áŠĨርሱም) አለ ÂĢሕዝá‰Ļá‰ŧ ሆይ! áŠĨኔ ለáŠĨናንተ ገላጭ የኾንኩ አáˆĩጠንቃቂ ነኝ፡፡īŋŧ

71:3 - ÂĢአላህን ተገዙá‰ĩáŖ ፍሩá‰ĩምáŖ á‰ŗዘዙኝም በማለá‰ĩ፤ (አáˆĩጠንቃቂ ነኝ)፡፡īŋŧ

71:4 - ÂĢለáŠĨናንተ ከኀáŒĸáŠŖá‰ļá‰ģá‰Ŋሁ ይምáˆĢልና፡፡ ወደተወሰነው ጊዜም á‹Ģቆá‹Ģá‰Ŋኋል፡፡ የአላህ (የወሰነው) ጊዜ በመáŒŖ ወቅá‰ĩ አይቆይም፡፡ የምá‰ŗውቁá‰ĩ á‰Ĩá‰ĩኾኑ ኖሮ (በá‰ŗዘዛá‰Ŋሁ ነበር)፡፡Âģīŋŧ

71:5 - (áˆĩለ ተቃወሙá‰ĩም) ÂĢአለ ጌá‰ŗá‹Ŧ ሆይ! áŠĨኔ ሌሊá‰ĩም ቀንም ሕዝá‰Ļá‰ŧን ጠáˆĢሁ፡፡īŋŧ

71:6 - ÂĢáŒĨáˆĒየም መሸáˆŊን áŠĨንጅ ሌላ አልጨመረላቸውም፡፡īŋŧ

71:7 - ÂĢáŠĨኔም ለáŠĨነርሱ á‰ĩምር ዘንá‹ĩ (ወደ áŠĨምነá‰ĩ) በጠáˆĢኋቸው ቁáŒĨር áŒŖá‰ļá‰ģቸውን በጆሮዎá‰ģቸው ውáˆĩáŒĨ አደረጉ፡፡ ልá‰Ĩáˆļá‰ģቸውንም ተከናነቡ፡፡ (በመáŒĨፎ áˆĨáˆĢቸው ላይ) ዘወተሩም፡፡ (á‹Ģለ ልክ) መኩáˆĢá‰ĩንም ኮሩ፡፡īŋŧ

71:8 - ÂĢከዚá‹Ģም áŠĨኔ በጩኸá‰ĩ ጠáˆĢኋቸው፡፡īŋŧ

71:9 - ÂĢከዚá‹Ģም áŠĨኔ ለáŠĨነርሱ ገለáŒŊኩ፡፡ ለáŠĨነርሱም መመáˆĩጠርን መሰጠርኩīŋŧ

71:10 - ÂĢአልáŠŗቸውም፡- ጌá‰ŗá‰Ŋሁን ምሕረá‰ĩን ለምኑá‰ĩ፡፡ áŠĨርሹ በáŒŖም መሐáˆĒ ነውና፡፡īŋŧ

71:11 - ÂĢበáŠĨናንተ ላይ ዝናምን ተከá‰ŗá‰ŗይ አá‹ĩርጎ ይልáŠĢል፡፡īŋŧ

71:12 - ÂĢበገንዘá‰Ļá‰Ŋና በልጆá‰Ŋም ይለግሰላá‰Ŋኋል፡፡ ለáŠĨናንተም አá‰ĩክልá‰ļá‰Ŋን á‹Ģደርግላá‰Ŋኋል፡፡ ለáŠĨናንተም ወንዞá‰Ŋን á‹Ģደርግላá‰Ŋኋል፡፡Âģīŋŧ

71:13 - ለአላህ ልቅናን የማá‰ĩሚá‰ĩ ለáŠĨናንተ ምን አላá‰Ŋሁ?īŋŧ

71:14 - በልዩ ልዩ ኹኔá‰ŗዎá‰Ŋ በáŠĨርግáŒĨ የፈጠáˆĢá‰Ŋሁ ሲኾን፡፡īŋŧ

71:15 - አላህ ሰá‰Ŗá‰ĩን ሰማá‹Ģá‰ĩ አንዱ áŠĢንዱ በላይ ሲኾን áŠĨንዴá‰ĩ áŠĨንደፈጠረ አá‰ŗዩምን?īŋŧ

71:16 - በውáˆĩáŒŖቸውም ጨረቃን አá‰ĨáˆĒ አደረገ፡፡ ፀሐይንም á‰Ĩርሃን አደረገ፡፡īŋŧ

71:17 - አላህም ከምá‹ĩር ማá‰Ĩቀልን አበቀላá‰Ŋሁ፡፡īŋŧ

71:18 - ከዚá‹Ģም በውáˆĩጧ ይመልáˆŗá‰Ŋኋል፡፡ ማውáŒŖá‰ĩንም á‹ĢወáŒŖá‰Ŋኋል፡፡īŋŧ

71:19 - አላህም ምá‹ĩርን ለáŠĨናንተ ምንáŒŖፍ አደረጋá‰ĩ፡፡īŋŧ

71:20 - ከáŠĨርሡ ሰፋፊዎá‰Ŋን መንገá‹ļá‰Ŋ á‰ĩገቡ ዘንá‹ĩ፡፡īŋŧ

71:21 - ኑሕ አለ፡- ÂĢጌá‰ŗá‹Ŧ ሆይ! áŠĨነሱ አምመጹá‰Ĩኝ፡፡ ገንዘቡና ልጁም ከáŒĨፋá‰ĩ በáˆĩተቀር á‹Ģልጨመረለá‰ĩን ሰው ተከተሉ፡፡īŋŧ

71:22 - ÂĢá‰ŗላቅንም ተንኮል የመከሩá‰ĩን ሰዎá‰ŊÂģ (ተከተሉ)፡፡īŋŧ

71:23 - አሉም ÂĢአምላኮá‰ģá‰Ŋሁን አá‰ĩተዉ፡፡ ወá‹ĩንምáŖ ሱዋዕንምáŖ የጉáˆĨንምáŖ የዑቅንም ነáˆĩርንም አá‰ĩተው፡፡īŋŧ

71:24 - ÂĢበáŠĨርግáŒĨም á‰Ĩዙዎá‰Ŋን አáˆŗáˆŗቱ፡፡ ከሓዲዎá‰Ŋንም áŒĨመá‰ĩን áŠĨንጅ ሌላን አá‰ĩጨምርላቸውÂģ (አለ)፡፡īŋŧ

71:25 - በኀáŒĸáŠŖá‰ļá‰ģቸው ምክንá‹Ģá‰ĩ ተሰጠሙ፡፡ áŠĨáˆŗá‰ĩንም áŠĨንዲገቡ ተደረጉ፡፡ ለáŠĨነርሱም ከአላህ ሌላ የኾኑ ረá‹ŗá‰ļá‰Ŋን አላገኙም፡፡īŋŧ

71:26 - ኑሕም አለ ÂĢጌá‰ŗá‹Ŧ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምá‹ĩር ላይ አንá‹ĩንም አá‰ĩተው፡፡īŋŧ

71:27 - ÂĢአንተ á‰Ĩá‰ĩተዋቸው á‰Ŗሎá‰Ŋህን á‹Ģáˆŗáˆĩá‰ŗሉና፡፡ ኀáŒĸáŠŖተኛ ከሓዲንም áŠĨንጅ ሌላን አይወልዱም፡፡īŋŧ

71:28 - ÂĢጌá‰ŗá‹Ŧ ሆይ! ለáŠĨኔም ለወላጆá‰ŧም ምáŠĨመን ኾኖ በቤቴ ለገá‰Ŗም ሰው ሁሉ ለምáŠĨመናንና ለምáŠĨምናá‰ĩም ምሕረá‰ĩ አá‹ĩርግ፡፡ ከሓዲዎá‰Ŋንም ከáŒĨፋá‰ĩ በቀር አá‰ĩጨምርላቸው፤Âģ (አለ)፡፡īŋŧ

- ተፈፀመ-


✍ዐá‰Ĩዱረዛቅ አል-ሐበáˆēይ


https://t.me/joinchat/AAAAAEq8AN90dYXSHRVgZA


➖ بØŗŲ… اŲ„Ų„Ų‡ اŲ„ØąØ­Ų…Ų† اŲ„ØąØ­ŲŠŲ… 🖊 ➖
☘☘ ከግáŒĨም ማህደር ☘☘
â€ĸ┈┈â€ĸâœŋ❁âœŋâ€ĸ┈┈â€ĸ
🍀🍀 áŠĨውነተኛ ጀግና 🍀🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

áŠĨውነተኛ ጀግና - ምá‹ĩር ላይ ነበረ
ለጌá‰ŗው ሲዋደቅ - በá‰ĩጋá‰ĩ የኖረ
ከወንጀል ማዕበል - ነፍሱን áŠĨየገá‰ŗ
ህይወቱን ሲገፋá‰ĩ- ከፅኑዎá‰Ŋ ተርá‰ŗ
ነፍሲá‹Ģው አረፈá‰Ŋ- መበርá‰ŗቱን አይá‰ŗ
ማሸነፍ ሲáˆŗናá‰ĩ - ወá‰ĩውá‰ŗ ወá‰ĩውá‰ŗ

áŠĨውነተኛ á‰ŗጋይ - ምá‹ĩር ላይ ነበረ
ሸይáŒŖን áŠĨንá‹ŗይáŒĨለው - ሲá‰ŗገል የኖረ
ከáŒĨፋá‰ĩ ለመሸáˆŊ - መፍá‰ĩሄውን አውቆ
ህይወቱን ሲገፋá‰ĩ - áŠĨጅግ ተጠንቅቆ
ሸይáŒŖን ተሸነፈ - á‰ŗጋዩን ሰልá‰Ŋá‰ļ
አልáˆŗáŠĢ ሲለው - ጎá‰ĩጉá‰ļ ጎá‰ĩጉá‰ļ

áŠĨውነተኛ ጠá‰ĸá‰Ĩ - ምá‹ĩር ላይ ነበረ
በማáˆĩረጃ áŒĨበá‰Ĩ - ህይወቱን የኖረ
በምáˆĢá‰ģ ጉዞ - በርá‰ĩá‰ļ ሲተጋ
ህይወቱን ሲገፋá‰ĩ - ጀሊልን ፍለጋ
ተደሰተ ጌá‰ŗው - በዚህ ጠá‰ĸá‰Ĩ ኑሮ
áˆĩáŠŦá‰ĩን ለገሰው - ጨምሮ ጨማምሮ

የሱው ተቃáˆĢኒ - áŠĨንዲህ á‹Ģልበረá‰ŗ
በነፍሲá‹Ģ áŒĨáˆĒ - ልቡ ተወá‰ĩውá‰ŗ
ተጎá‰ĩá‰ļ ቀርá‰ļ - በሸይáŒŖኑ ገመá‹ĩ
ተይዞ á‰ŗሰረ - ተገኝá‰ļ ከወáŒĨመá‹ĩ
ከዚህ መጠበቂá‹Ģው - መበርá‰ŗá‰ĩ ነውና
áˆĢሕማኑ á‹Ģá‹ĩርገን - áŠĨውነተኛ ጀግና

🖌 áŠĸá‰Ĩኑ ሱልáŒŖን አልáŠĸá‰ĩዮá‰ĸ

áŠĨርማá‰ĩና ማáˆĩተáŠĢከá‹Ģ
➡ī¸ī¸ ዓá‰Ĩዱረዛቅ አልሐበáˆē

ግምገማ
➡ī¸ áŠĸáˆģáˆĢ የáˆŗንሱርና አáˆĩተá‹Ģየá‰ĩ ክፍል
ሸዋል 22 - 1441

t.me/isharaChannel2

20 last posts shown.

2 789

subscribers
Channel statistics