ቅዳሜ'ለት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ ኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ እንዲደረግላትና ይህም በቀጣይ ሳምንታት መፍትሄ ሊያገኝ እንደሚገባ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ማክሮን፣ ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረጓ፣ አበዳሪዎች የአገሪቱን የሦስት ቢሊዮን ዩሮ ብድር የማሸጋሸግ ሂደት "በቀጣይ ሳምንታት" ውስጥ የማጠናቀቅ ሃሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ጋር እያካሄደች ያለችውን ንግግር ፈረንሳይ እንደምትደግፍም ፕሬዝዳንት ማክሮን አስታውቀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa