በአዲስ አበባ በስድስት ክፍለ ከተሞች የሥምና ንብረት ዝውውር ታገደ!
በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በስድስት ክፍለ ከተሞች እና በተመረጡ ወረዳዎች የሥምና ንብረት ዝውውር መታገዱን የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ አስታውቋል።ኤጄንሲው ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት በመዲናዋ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን አመልክቷል፡፡
አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ መሰራቱን ገልጿል።በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም አመላክቷል።በዚህ መሠረትም የይዞታ ማረጋገጥ ሥራው በተመረጡ ስድስት ክፍለ ከተሞች በቀጣይ አምስት ወራት ውስጥ እንደሚከናወን ተጠቅሷል።
ክፍለ ከተሞችም የካ፣ ለሚ ኩራ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ መሆናቸው ተገልጿል።ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክ/ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር ድረስ የሥምና ንብረት ዝውውር መታገዱ ተገልጿል።ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡም ጥሪ ቀርቧል።
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa