አገልግሎቱ ካሉት 41 ባቡሮች እየሠሩ ያሉት 16ቱ ብቻ እንደሆኑ አስታወቀ!
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ካሉት 41 ባቡሮች እየሠሩ ያሉት 16ቱ ብቻ እንደሆኑ አስታውቋል፡፡የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ብርሀን አበባው ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ወደ ስራ ሲገባ 41 ባቡሮች የነበሩት ቢሆንም አሁን አገልግሎት እየተሰጡ ያሉት ባቡሮች ቁጥር 16 ብቻ ነው፡፡
ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባቡሮች አገልግሎት የማይሰጡት በብልሽት ምክንያት መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።ባቡሮቹ ብልሽት በሚያጋጥማቸው ጊዜ የጥገና ዕቃዎች ገበያ ላይ የሉም ያሉት ኃላፊው፤ ችግሩን ለመፍታት ከአንዱ ባቡር እየተነቀለ ወደ ሌላኛው ሲገጠም መቆየቱ ተናግረዋል።
የባቡሮቹን ሶፍትዌር ለመጠቀም ፍቃድ አለመኖሩም ለባቡሮቹ መቆም ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተበላሽተው የቆሙ ባቡሮችን ወደ ስራ ለማስገባት፣ የተሻለ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና ዘርፉ አሁን ካለበት የውጤት መቀዛቀዝ ለማውጣት የሪፎርም ስራዎች መጀመራቸውን አብራርተዋል፡፡
በሪፎርሙ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮችም ዋነኛው የቆሙ ባቡሮችን ወደ ስራ ማስገባት መሆኑን ጠቅሰው፤ እስከ መጪው ሰኔ ድረስ አምሥት ባቡሮች ወደሥስራ እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የሁለት ባቡሮች የጥገና ስራ መጠናቀቁን ጠቁመው፤ እነኝህ ባቡሮች በቀጣይ ሶስት ቀናት ወደ ስራ እንደሚገቡ አብራርተዋል።
(ኢፕድ)
@YeneTube @FikerAssefa