የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ባጸደቀው ብድር ዙሪያ ሁለተኛ ዙር ግምገማ አፀደቀ
የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ለኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ባጸደቀው የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ዙሪያ ሁለተኛውን ዙር ግምገማ ትናንት ማፅደቁን አስታውቋል።
የብድር ግምገማው መጽደቁን ተከትሎ፣ ድርጅቱ የ250 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱ የውጭ ዕዳ አስተማማኝ እንዲኾን ጥረቱን መቀጠሉንና በቡድን 20 አገራት ማዕቀፍ ሥር የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ ለመድረስ ከአበዳሪዎች ጋር የሚያደርገው ድርድር አበረታች መሆኑን ጠቅሷል።
የመንግሥትን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ይፈጠራል ተብሎ የተሠጋው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አልተከሰተም ያለው ድርጅቱ፣ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችትም "በፍጥነት" እያደገ መኾኑን ገልጿል።
@Yenetube @FikerAssefa