ኢትዮጵያ እና ቱርክ “የአንካራ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይ በሚካሄደው የቴክኒክ ድርድር ዙሪያ” መምከራቸው ተገለጸ!
የኢትዮጵያ እና የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአንካራ በተደረሰው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ዙሪያ መምከራቸው ተገለጸ።ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በቱርክዬ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡርሃንቲን ዱራን የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን “የአንካራ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይ በሚካሄደው የቴክኒክ ድርድር ዙሪያ” ከቱርኩ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡርሃንቲን ዱራን ጋር ሀሳብ መለዋወጣቸውም ተጠቁሟል።ኢትዮጵያ ለአንካራ ስምምነት ሙሉ ተፈጻሚነት ቁርጠኛ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
በውይይቱ ወቅት ዶ/ር ጌዲዮን ቱርክዬ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የአንካራ ስምምነትን እንዲፈርሙ ላደረገችው አስተዋጽኦ ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በኢትዮጵያን እና ሶማሊያ መካከል የተፈረመውን የአንካራን ስምምነት ተከትሎ በጎርጎሮሳውያኒ 2025 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ ሁለቱን ሀገራት የመጎብኘት እቅድ እንዳላቸው መገለጹን መዘገባችን ይታወሳል።
ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ በመካከላቸው የተፈጠረውን አልመግባባት ለመፍታት ያስችላል የተባለ ስምምነት በቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም መፈራረማቸው ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa