በመርካቶ ሸማ ተራና አካባቢው ያጋጠመው የእሳት አደጋ መንስኤ ከኤሌክትሪክ ጋር በተያያዘ ችግር እንደሆነ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው የደረሰው የእሳት አደጋ በኤሌክትሪክ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አማካኝነት ያጋጠመ መሆኑን በፎረንሲክ ምርመራ ማጣራቱንና ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
ኮሚሽኑ ባለፉት 6 ወራት በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የደረሱ 103 የእሳት አደጋ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡በዚህ የማጣራት ሂደትም በኤሌክትሪክ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የደረሰ ቃጠሎ ብዛት 50፣ በመካኒካል ችግር ምክንያት የደረሰ 11 ቃጠሎ፣ ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሰ 10 ቃጠሎ፣ በቸልተኝነት የደረሰ 17 እና በሌሎች ምክንያቶች የደረሰ 15 ቃጠሎ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 96 እና በክልሎች ደግሞ ሰባት በአጠቃላይ እንደ ሀገር 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ደርሰው የአደጋ መንስኤዎችን ማጣራቱን ጨምሮ ገልጿል፡፡በግማሽ ዓመቱ በ582 መኖሪያ ቤቶች፣ በ12 ተሽከርካሪዎች፣ በ1ሺ 965 ንግድ ቤቶች፣ በስድስት ፋብሪካዎችና የተለያዩ ድርጅቶች በቃጠሎ ምክንያት ጉዳት ስለመድረሱ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የስድስት ወራት ሪፖርት ተብራርቷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa