ነዳጅ ማደያዎች 24 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ!
በአዲስ አበባ ከተማ ከ130 በላይ ነዳጅ ማደያዎች ቢኖሩም 24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ 35 ብቻ መሆናቸው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡ከ130 በላይ ነዳጅ ማደያዎች ያሉ ሲሆን አብዛኞቹ ምሽት ላይ አገልግሎት እንደማይሰጡ እና በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጣቸው ላይ ማሻሻያ እንደሚደረግ የተናገሩት የከተማዋ ንግድ ቢሮ የገበያ መረጃ ጥናት እና ማስታወቂያ ዳይሬክተር አቶ ሙሰማ ጀማል ናቸው።
"በተሰራው የክትትል ሥራ ላይ የነዳጅ ማደያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክፍተት መኖሩን እና አብዛኞቹ 24 ሰዓት አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውን ተመልክተናል" ነው ዳይሬክተሩ ያሉት፡፡በከተማዋ አገልግሎት የሚሰጡ ነዳጅ ማደያዎች 24 ሰዓት አገልግሎት እዲሰጡ ሊደረግ መሆኑን አንስተው፤ "በአስገዳጅነት የአገልግሎት የሰዓት ለውጥ ከመደረጉ አስቀድሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ይሰራል" ብለዋል፡፡
ሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት መፍታት የሚያስችል አዋጅ ለሕዝብ ተወካዎች ቀርቦ መጽደቁንም ተናግረዋል፡፡በመሆኑም በቀጣይ በሕገ-ወጥ ድርጊት ላይ የተገኙ ነዳጅ ማደያዎች ላይ፤ ከ700 ሺሕ ብር ጀምሮ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እንደሚጣልባቸው አስታውቀዋል፡፡አክለውም ነዳጅ ማደያዎች በቢሮ ፍቃድ እና እውቅና ከተሰጣቸው ውጪ ነዳጅ መሸጥ እንደሌለባቸው አሳስበዋል፡፡
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa