በመተሓራ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 6.0 የተመዘገበ!
-የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ፤ ከፍተኛ ጉዳት መደረሱ አልተገለጸም
በኦሮሚያ ክልል መተሓራ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 6.0 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ትናንት አርብ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:28 ላይ መከሰቱን ቮልካኖ ዲስከቨሪ አስታውቋል።የመሬት መንቀጥቀጡ ማዕከል ከከተማዋ 6.5 ኪ.ሜ. ርቀት አካባቢ ላይ እንደነበር እንዲሁም ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ሪፖርቱ አመላክቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በአካባቢው ባሉ ከተሞች መሰማቱ ተገልጿል።
በአፋር፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ምክንያት 90,000 ሰዎች ላይ ተጽዕኖ መፈጠሩንና ሁለት ሰዎችም መጎዳታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።ባለሥልጣናት በአፋር ክልል ከ55 ሺህ በላይ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ከ20ሺህ በላይ በአጠቃላይ ከ75 ሺህ በላይ ሰዎችን ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች አስወጥተዋል።
ከመስከረም ወር ጀምሮ የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ 261 የሚሆኑ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን መዝግቧል። የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎቹ በዋናነት የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ አካል በሆነው ፋንታሌ አካባቢ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ይህም በርካታ ቤቶች እንዲፈርሱ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa