በአውሮፓ ውስጥ በቱጃሩ ሰው የፖለቲካ አመለካከት የተነሳ የቴስላ ተሽከርካሪ ሽያጭ 28.2 በመቶ ቀንሷል ተባለ
በአውሮፓ ውስጥ አዲስ የመኪና ሽያጭ ከአንድ አመት በፊት በመጋቢት ወር ከነበረው 28.2 በመቶ ቀንሷል ፣ ምንም እንኳን አጠቃላይ የባትሪ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሽያጭ በወር ውስጥ 23.6 በመቶ እንደጨመረ የአውሮፓ አውቶሞቢል አምራቾች ማህበር (ኤሲኤኤ) መረጃ አሳይቷል። በአውሮፓ ውስጥ አጠቃላይ አዲስ የመኪና ሽያጭ በወር ውስጥ 2.8% ከፍ ብሏል ፣ በብሪታንያ እና በስፔን ባለሁለት አሃዝ ዝላይ ጭማሪ አሳይቷል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ትርፍ መጨመር የነዳጅ እና የናፍታ መኪናዎች ውድቀትን እንደሚያካክስ መረጃው አመላክቷል።
በአውሮፓ የቴስላ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የሽያጭ ማሽቆልቆል ከቻይና ጋር ያለው ፉክክር እየበረታ እና አንዳንዶች በፖለቲካዊ አመለካከቱ ላይ ተቃውሞ በማሳየታቸው አሽከርካሪዎች የኤሎን ማስክን የኤሌክትሪክ መኪና ከመግዛት እየተቆጠቡ ይገኛል። አውሮፓውያን መኪና ሰሪዎችም ከቻይና ጋር ያለውም ፉክክር እየታገሉ ሲሆን በሀገር ውስጥ ገበያ ከፍተኛ ወጪን ቢኖርም ዋሃውን ለማውረድ እየተዋጉ ይገኜል። አሁን ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአውቶሞቢሎች ላይ የጣሉት የ25 በመቶ ታሪፍ ጋር በመታገል ለኢንዱስትሪው ያለውን ፈተና ይበልጥ አስከፊ አድርጎታል።
በአውሮፓ ህብረት ፣ በብሪታንያ እና በአውሮፓ ነፃ ንግድ ማህበር የመጋቢት ወር ሽያጮች ለሁለት ወራት ከነበረበት መቀዛቀዝ በኋላ ወደ 1.42 ሚሊዮን መኪናዎች ከፍ ብሏል ሲል የአውሮፓ አውቶሞቢል አምራቾች ማህበር (ኤሲኤኤ) መረጃ አሳይቷል በቮልስዋገን እና ሬኖ የተመዘገቡት የተሽከርካሪ ሽያጭ በ10.3 በመቶ እና 13 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በአውሮፓ የቴስላ ሽያጭ ለሶስት ተከታታይ ወር ቀንሷል። ከዓመት በፊት ከነበረበት 28.2 በመቶ ሲቀንስ የጠቅላላ ገበያ ድርሻው ከአንድ አመት በፊት ከነበረበት 2.9 በመቶ ወደ 2 በመቶ ቀንሷል።
ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa