(... ሴት እርግ ነች... ኮረዳነቷ ያስታውቃል... ከላባዋ ስር የፋፋ ሙቅ ገላ እንዳለ ያስታውቃል... ካለሁበት በግምት አስር ሜትር ርቀት ላይ ለኔ የማይታየኝን ነገር ትለቅማለች...)
... ቀበጥ ገላ አላት ... ልቧ ለሚያንቋልጥላት የሚሞት... ገና የጡቶቿን ማደግ እንዳስተዋለች ኮረዳ ምትሽኮረመም... ቃል ከላንቃ ሲነቃ ... ልቧ ፍርስ የሚልላት... ልጅነቷን ከንጋት ያሻገረች ናት... ከእኔ ጋር...
(... የደረቷ ላይ ላባ እንደንጋት ሰማይ ያለ ነው... የገደል ማሚቱ ብምታስተጋባው የምሽትት ፀሃይ ብርሃን አያታለው... ከግቢው አጥር ማዶ ወንዙን ተሻግሮ ካለ እድሜዬን ሙሉ ከማውቀው የዋንዛ ዛፍ ላይ መሰሎቿ አሉ...)
... በደከመ ልብ አያታለው... ልማዳዊ ቃሎቼ ፈቃዴን ሳይጠብቁ ይመልሱላታል... ምን አጣውባት እላለው... በፍቅር የሚያዩአት አይኖቼ ህፀፅዋን ያስሳሉ... ምናልባት ብቻዋን ነው ምታምረው...
(... ሌላ ሴት ርግብ ከዛፉ ላይ ወረደች ... የአንድ እግሯ ሁልርት ጣቶች ተቆርጠዋል... ምናልባት ቆርቆሮ አጥር ይሆናል... ስትራመድ ታነክሳለች... እንደዛችኛዋ የ እርግብ ነፍስ ያለባት አትመስልም... )
... መንፈሴ ሞቷል... በድኔን ሰብስቤ ልጠፋ አስባለው... ከሳቋ ጋር ሚነቃ ነፍስ አልተረፈኝም... ለልቧ ሃገር ባዳ ነኝ...
(ቀስ ብቀስ በዛ ያሉ ርግቦች እፊቴ ያለውን ረባዳ ሞሉት... ዝምታ ሆነ... በጥሬ ለቀማ ቦታው በሚነሳ የድንብር ግጭት... ባሌን አማለልሽብኝ በሚል ከሚገለማመጡ ሴት ርግቦች... የወንዙ ድምፅ ... የዛፉ ቀጠል... ሁሉም ድምፃቸው ዝምታ ነው... የተቐመጥኩበት ድንጋይ ሳይቀር መኖሬን ረስቷል...)
... ላንቺ የቀረ መውደድ የለኝም... በልቤ አልኩ... እውነትነቱ አስፈራኝ... ይአፈራሁት እውነት መሆኑን ይሁን ውሸታም መሆኔን እርግጠኛ አይደለሁም...
("... አንተ አቢ ና ተቀበለኝ እቃ ይዣለው..." እናቴናት... የከፈተችውን የውጭውን በር በቁሟ ለቀቀችው... የግቢው ሰላም ከመቅፅበት ጠፋ... እርግቦቹ ክንፌ አውጪኝ ተበታተኑ... )
... ካንገቷ ስር የሚወጣው ጠረን አዲስነቱ ጠፍቷል... የአካሏ መለስለስ ደሜን ማሞቅ ትቷል... ስታቅፈኝ አይኗን ጨፍና ነው... ሳቅፋት መልኳን እያየሁ ነበር... የምታነበንበውን ስትጨርስ ... በሃሳቤ አንካሳውን እርግብ እያየሁ "እኔም" ...
|ዘካሪያስ|
°•.• @yenie_kal •.•°
@yenie_kal
○○○○○○○