... ዝምታው ውስጥ የሚሰማው የኔ ድምፅ ብቻ ነው... ንግግሩ እንኳን ከፀትታ ያንሳል... ከእጁ ጋር ባለፊልም ካሜራ አብሮ ተፈጥሯል... በዙሪያው እንደ መዓት ቢራቢሮ ነኝ... ሊይዘኝ ሲጥር አላውቅም... ምናልባት ለዚህ ነው ደህንነት ሚሰማኝ... ላርፍበት እቋምጣለው... መሆኔን ሁሉ እንደ አዘቦት በዝምታ ያልፋል... ከ እራፊ መልሶቹ እጫወታለው...
(ምናልባት ፍቅር ይዞኛል... ከትንንሽ ሳቆቿ ጋር... ከትንንሽ ገላዋ ጋር ... ከትንንሽ ጠረኗ ጋር... እንዳልለምዳ ፈርቼ ነው በትንሹ የቀረብኳት... ከጣቶቿ መርጬ ማርያም ጣቷን ከሳቋ መርጬ ፈገግታዋን ከአይኗ መርጬ ትንሽ መሽኮርመሟን... ከገላዋ ልዝብ እቅፏን...
... በሙሉ አይኔ ሳላያት)
... እርሱ ፎቶ ለማንሳት ይቁነጠነጣል... እኔ ያየውን ላይ እቅበጠበጣለው... ነፍሱን የሳበውን ላውቅ... አብረን ሆነን ካነሳው ላይ መርጦ አጥቦ ያመጣልኛል... እዚህ ሆኜ ግርግዳዬን የሞላው ... ጤዛ ያረጠበው ሳር ምድር እንደ መርገፍ ያለች እፉዬ ገላ የደረቀ ቅጠል... ትንንሽ አበቦች... የዝናብ ጠፈጠፎች ... ንፋስ የገፋቸው አፀዶች... ከነዚህ ሁሉ ላይ የሚፈልቁ ትንንሽ የፀሃይ ልጆች... ናቸው
(ከካሜራዬ ድምፅ ጋር አዲስ ትዝታ ይፃፋል... የጤዛው መልክ ጠረኗን ይጠራብኛል... የረገፉ እፉዬ ገላዎች ጋር ስልምልም አካሏን አስባለው... የካፍያው መልክ አንገቴ ስር የሰማሁትን የትንፋሽዋን ሙቀት ያስናፍቀኛል... ከትናንሽ ትዝታዎቿ ጋር ትናንሽ ፀሃዮች እለቅማለው)
... ወረቴ ሲያልቅ ይታወቀኛል... ቢራቢሮዎቼ አበቦቹን ለካክፈው ጨርሰዋል... ደብቆ ያኖረው አፀድ የለም... ቸልታው ውስጥ ስለተጋረዱ መንገዶቹ አላውቅም... ፀትታውን ተሰናበትኩት... ስሄድ የተከተለኝ የካሜራው ድምፅ እና ዝምታው ነው...
(... ልጅነቴን ከበላሁ ቡሃላ... "መጥለቅ" ያልኩትን ፎቶ አተኩሬ አየሁት... በድንግዝግዝ ብርሃን ውስጥ ከኔ ርቃ የምትበር ቢራቢሮ... ፀሃይ አይደለችም... በመሃከላችን የተጋደመ አድማስ አይታይም... ግን በርምጃዋ ልክ የሚጨልም ቀን እኔ ጋር ነበር...)
|ዘካሪያስ|
°•.• @yenie_kal •.•°
@yenie_kal
○○○○○○○