እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን !
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ_የመስቀሉ_ሥር_ድንቅ_ሐዋርያ
[ ፬ ]
#ዮሐንስ ማለት ‹‹ #የእግዚአንሔር_ጸጋ ነዉ››፤ደስታ ማለት ነዉ ፡፡ አባቱ ዘብዴዮስ ፤ እናቱ ማርያም ባዉፍልያ ትባላለች ፡፡ ቁጥሩ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የሆነ ያዕቆብ የተባለ ወንድም ነበረው ፡፡ ማቴ 4፡21 ፤ ማር 1፡20 ፤ማቴ 20፡20 ቅዱስ ዮሐንስ አስቀድሞ የዮሐንስ መጥምቅም ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ዮሐ 1፡ 35 ቅዱስ ዮሐንስ ከአባቱና ከወንድሙ ጋር ዓሣ በሚያጠምድበት በገሊላ ባሕር ላይ መረቡን ሲያበጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያነት ጠራው ፡፡ እርሱም አባቱን ሌሎቹንና ታንኳን ትቶ ከወንድሙ ያዕቆብ ጋር ጌታን ተከተለው ።
#የዮሐንስ_ስሞች
ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ
ዮሐንስ ታኦሎጎስ
ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
ዮሐንስ ወንጌላዊ
ዮሐንስ ዘንሥር
1. ቅዱስ ዮሐንስ ወንድሙ ያዕቆብ የሰማርያ ሰዎች በእሳት እንዲጠፋ ተመኝተው ነበር ፡፡ በዚህ ዓይነት የችኩልነት ስሜታቸዉ የተነሣ ጌታ ‹‹‹ቦአኔርጌስ››‹‹‹‹የነጎድጓድ ልጆች›››››ብሏቸዋል፡፡ማር 3፡17 ሉቃ 9፡54 በምሥጢር ደቂቀ ምሥጢር ደቂቀ መለኮት ሲል ነው ፡፡ ማር 3፡17
2. ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ) ቀዳሚው ነው ፡፡ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግሥትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር ፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቅሩብ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደው የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡
3. ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ኾኖ ኖሯል፡፡
4. ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አምልቶና አስፍቶ በመጻፉ (ታኦጎሎስ) ተብሏል ፡፡ ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡
5. ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነውን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል ፡፡ትጉሙም #የራእይ አባት ማለት ነዉ፡፡
6. ቅዱስ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌልን በመጻፉ ወንጌላዊ ተብሏል፡፡
7. በሥላሴ ሥዕል ላይ ካሉት ከዐራቱ እንስሳ አንዱ ንሥር ነዉ፡፡ንሥር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል ፡፡ ንሥር በእግሩ እንደመሽከርከሩ ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡ ንሥር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላውያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏል ፡፡ ንሥር ዐይኑ ንጹሕ ነው ሽቅብ ወጥቶ ቁልቁል ሲመለከት ቅንጣት የምታክል ሥጋ አታመልጠውም ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌል ሲጀምር እጅግ ርቆና መጥቆ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የአካላዊ ቃልን (የእግዚአብሔር ወልድን)በቅድምና መኖር ተናግሯል፡፡በዚኽም ዮሐንስ ዘንሥር ተብሏል፡፡
ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በሕይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነው ፡፡ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹‹‹ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶኽ ??›››ዮሐ 21፡20 ይኽም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነው ፡፡በማቴ 16፡18 ላይ ‹‹እዉነት……ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ›››››ያለው ቃል ለቅዱስ ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ሕያው ቃል ነው ።
የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጕድጓ ፡ ፍቁረ እግዚእ ፡ አቡ ቀለምሲስ ፡ ነባቤ መለኵት የመስቀሉ ሥር ድንቅ ሐዋርያ በረከቱ ፣ ረድኤቱ ፣ ምልጃና ፍጹም ጸሎቱ አይለየን ይጠብቀንም ።
እንኳንም ከዚኽ ዐለም ድካም ለተሠወረበት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ በሠላም አደረሰን አደረሳችኹ ።