Posts filter


🔰 አዲሱ Android 15  Preview : ምን አዲስ ነገር ይዟል?

× Google ሁለተኛውን Android 15 ቅድመ እይታ ለዴቨሎፐሮች  እና ለቴክኖሎጂ አድናቂዎች ይፋ አድርጓል።

× ዛሬ Android 15 ሊኖሩ የሚችሉ አዳዲስ ዋና ዋና ባህሪያት እና ማሻሻያዎችን ዝርዝር በአጭሩ ለማየት እንሞክራለን:

🔒 Lockscreen Enhancements:
በተቆለፈ ስክሪን ላይ ላለው 'Enter Pin' ጥያቄ ጽሑፍ በትልቁ እንዲሆን ተሻሽሏል።

📦 App Archiving፡
ስልካችን ስፔስ ቢሞላ እና ተጨማሪ አፕ መጫን ብንፈልግ ክላውድ ላይ መጫን የሚያስችል  feature ተካቶለታል።

📸 Pixel Phones as Webcams፡ አዲሱን የHD አማራጭ በመጠቀም የተሻሻለ የቪዲዮ ጥራት ያለው የፒክስል ስልክ እንደ Webcam መጠቀም ያስችላል ፤ ይሄ feature ፒሲያቸው ጥራት የሌለው ካሜራ ላላቸው እና Video Call በአብዛኛው ለሚጠቀሙ ሰዎች ጠቃሚ ነው።

⌨️ Keyboard Shortcut፡
ኪይቦርዱን በአስቸኳይ መክፈት ብንፈልግ በቀላሉ app drawer በመንካት መክፈት እንችላለን።

🔊 Bluetooth LE Auracast Improvements፡
ለኤርፎን እና ስፒከሮች ጨምሮ  በርካታ የብሉቱዝ መሳሪያዎች እንዲገናኙ እና የጋራ የድምጽ ይዘትን እንዲያስተላልፋ የሚያስችል Feature ተካቶለታል።

📧 Satellite Messaging፡
መልእክቶችን ለመላክ Network ኖረ አልኖረ የሳተላይት ቴክኖሎጂን በመጠቀም መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተካቶለታል።

🐞 Bug Fixes፡
አንድሮይድ 15  ፕሌይ ስቶር ጋር የተያያዙ ብልሽቶችን፣ package manager፣ የጣት አሻራ ሁኔታ እና የአንድሮይድ ሲስተም ኢንተለጀንስን ጨምሮ የተለያዩ bug fix  እንደሚያደርግ ይጠበቃል።


📣 Join| @yidnek_tech
📣 Join| @yidnek_tech_group
📣 Subscribe| https://linktw.in/MEKnrg

©Tech በአማርኛ ™




#Congratulation! 🎉
#እንኳን_ደስ_አላችሁ!

Chat-GPT በኢትዮጵያ Location መስራት ጀመረ።
ተማሪዎች ለሪሰርች፣ ለአሳይመንት፣ ለፕሮጀክት እንዲሁም ለሌሎች ነገሮች እንደሚጠቀሙበት የሚታወቀው Chat-GPT አሁን ስልክ ቁጥርዎን ብቻ በማስገባት VPN ሳያስፈልግዎት መጠቀም ይችላሉ።

https://chat.openai.com/


Join : @yidnek_tech
Join : @yidnek_tech_group
Subscribe : https://linktw.in/MEKnrg


#Tech_News
#ዜና_ቴክ

× ኢትዮጵያ ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚያስከፍሉ ሀገራት በቀዳሚነት ተቀመጠች።

× መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገ 'ፕራይስ ኮምፓሪዝን' የተሰኘ የምርምር ተቋም አደረግኩት ባለው አዲስ ጥናት በዓለማችን ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚጠይቁ 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን በአንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

× ጥናቱ በኢትዮጵያ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በወር በ307.84 ዩሮ ገደማ እንደሆነ በመግለጽ ይህ ዋጋ ኢትዮጵያን በዓለም ላይ ከሚገኙት ሀገራት ከፍተኛ ዋጋ የሚጠየቅባት ሀገር ያደርጋታል ብሏል።

× ይህም ለወርሃዊ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ሽያጭ በአማካኝ 30.99 ዩሮ ከምትጠይቀዉ ዩናይትድ ኪንግደም ጋር በንፅፅር ሲቀመጥ የኢትዮጵያ ዋጋ ወደ አስር እጥፍ እንደሚጠጋ ተጠቁሟል።

× ውድ የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ካለባቸዉ ሀገራት መካከል ለብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በወር 236.09 ዩሮ የምታስከፍለዉ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

× በተቃራኒው በጥናቱ በአለም ላይ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በርካሽ ዋጋ ከሚገኝባቸው ሀገራት ተርታ መካከል ዩክሬን የአንደኝነት ደረጃን የያዘች ሲሆን ለአገልግሎቱ የሚከፈለዉ ወርሃዊ ክፍያ በአማካኝ 4.42 ፓውንድ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


#Tech_News
#ዜና_ቴክ

× ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል።

× የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ የሆነው ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት ለመጀመር በሙከራ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

× ይህ ሥርዓትም ቢያንስ ከ1000 በላይ ተከታይ ባላቸው ቻናሎች ላይ እንደሚጀመር ነው የገለጸው።

× ከዚህ ቀደም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት የሌለው ቴሌግራም አሁን ላይ ተጠቃሚዎች ቻናላቸውንና ቡታቸውን በክፍያ እንዲያስተዋውቁ የሚያስችላቸውን አሰራር መዘርጋቱን ነው ይፋ ያደረገው።

× የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ እንደጠቀሰው በሙከራ ላይ የሚገኘው የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓቱ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን የግል መረጃን አይጠቀምም ብሏል።

× ከዚሁ ጋር ተያይዞ ማስታወቂያዎቹ በግል እና በቡድን መልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳዎች ላይ የማይታዩ መሆናቸውንና በክፍያ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች በቻናሎች ላይ ብቻ እንደሚቀርቡ ገልጿል።

× ማስታወቂያ ማስነገር የሚፈልጉ አስተዋዋቂዎች ቻናላቸውን ወይም ቡታቸውን ከ160 ባልበለጡ ፊደላት ገለጻ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በቋንቋ፣ በይዘት እንዲሁም በልዩነት ማስታወቂያው እንዲተላለፍላቸው የሚፈልጉትን ቻናል መርጠው ማስተዋወቅ ይችላሉ ተብሏል።

× ቴሌግራም ከቻናል ባለቤቶች ጋር የትርፍ ክፍፍል የማድረግ እቅድ እንዳለውም ያስታወቀ ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን መሰረታዊ ወጪዎቹን ከሸፈነ በኋላ እንደሆነ ገልጿል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


#Tech_News
#ዜና_ቴክ

× YouTube የDislike Buttonኑን ከPublic እይታ ወደ Private ሊቀይር ነው።

× ይህም ማለት YouTube ላይ የሚለቀቁትን ማንኛውንም Video ተመልካቹ ወይም ግለሰብ Dislike ቢያደርግ ያን Dislike ሌሎች ሰዎች ማየት አይችሉም።

× ለChannelሉ ባለቤት ብቻ ይታያል ማለት ነው።

× YouTube ይሄንን ያደረገበት ምክንያት Dislike Attackን ለመከላከል ነው።

× Dislike Attack ማለት አንዳንድ ሰዎች በግልም ሆነ በቡድን በመሆን ሆን ብለው አንዳንድ የYouTube Channelሎችን ኢላማ   በማድረግ እዛ Channle ላይ የሚለቀቁትን Video Dislike ያደርጋሉ።

× ይሄ ደግሞ የChannel Creatorች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ በመሆኑ ነው።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


#5_እጅግ_ፈጣን_የስልክ_ፕሮሰሰሮች_ደረጃ_በ2021
#5_Faster_Smartphone_Processors_Rank_In_2021


፩. A15 Bionic

× ይሄ Processor እስካሁን ከተሰሩ Processorች ሁሉ በጣም ፈጣንና አንደኛ ሲሆን Design የሚደረገው በApple Company ነው።

× A15 Bionic Processor በፈረንጆቹ September 14, 2021 የወጣ ሲሆን በiPhone13 በiPhone13 Pro በiPhone13 Pro Max ና Mini የመሳሰሉት ላይ እናገኘዋለን።

× ከiPhone ውጪ ይሄን Processor የሚጠቀም ስልክ የለም።

× 15.8 Trillion Operations በ ደቂቃ የሚሰራ ሲሆን 15 Billion Transistor አለው።

- CPU Performance 99/ከ100

- Gaming Performance 96/ከ100


፪. A14 Bionic

× በሁለተኛ ደረጃ የምናገኘው አሁንም የApple ምርት የሆነውን A14 Bionic Processor ነዉ።

× Launched የተደረገው September 15, 2020 ነዉ።

× A15 Bionic ቀጥሎ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው Processor ሲሆን በiPhone12 በiPhone12 Pro  Mini ና iPadAir Tablet ላይ ስናገኘው 11.8 Billion Transistor ይዟል።

× በተጨማሪም 11 Trillion Operation በSecond መስራት ይችላል።

- CPU Performance 98/ከ100

- Gaming Performance 84/ከ100

× A15 ከA14 Bionic ጋር ሲነፃፀር በ43% ፈጣን Performance አለው።


፫. Qualcomm Snapdragon 888 Plus+

× ይሄ Processor Released የተደረገው በፈረንጆች
June 28, 2021 ሲሆን ከ Appleሉ A14 Bionic ቀጥሎ ምርጥ ፍጥነት ያለው Processor ነው።

× America San Diego ውስጥ የሚመረተው ይሄ Processor 32 Trillion Operations በSecond መስራት ይችላል

- CPU Performance 89/ከ100

- Gaming Performance 95/ከ100

- የAsus፣ የMotorola፣ የXiaomi እና የVivo Companyዎች አዲሱን Qualcomm Snapdragon 888 Plus+ Chipsetን አዲስ በሚያወጡት ስልኮች ላይ እንደሚያካትቱ አስታውቀዋል።


፬. Qualcomm Snapdragon 888

× ይሄ Processor 11.8 Billon Transistor የተገጠመለት ሲሆን 26 Trillion Operations
በSecond ይሰራልናል።

- CPU Performance 88/ከ100

- Gaming Performance 93/ከ100

× Samsung Galaxy S21, OnePlus 9, Galaxy Z Fold 3, Xiaomi Mi 11 Ultra እና የመሳሰሉት ስልኮች
Qualcomm Snapdragon 888 Processorን ተጠቃሚ ናቸው።

× Qualcomm Snapdragon 888 Plus+ ከQualcomm Snapdragon 888 ጋር ስናነጻጽረው
በ20% ይበልጠዋል።


፭. Samsung Exyon 2100

× በአምስትተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው Samsung Exyon 2100 ሲሆን በSamsung Electronic Manufacture የሚመረተው ሲሆን 26 Trillion Operations በSecond ያከናውናል ስንት Transistor እንዳለው Officially እስካሁን አልተገለፀም።

- CPU Performance 83/ከ100

- Gaming Performance 82/ከ100

× Exyon 2100 ከQualcomm Snapdragon 888 Processor ጋር ሲነፃፀር (slightly) ይበለጣል።

× Samsung Galaxy S21 Ultra, Samsung Galaxy S21, Samsung Exyon 2100 processorን የሚጠቀሙ ስልኮች ናቸው።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


#SD_(Secure Digital)_Card
#ሜሞሪ_ካርድ

× ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድና የተከበራችሁ የ 'Yidnek Tube' የቴሌግራም ቻነል ቤተሰቦች!

× የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መካከል ስለ ሜሞሪ ካርድ ወይም SD (Secure Digital) CARD በጥቂቱ እነግራችኃለሁ አብራችሁኝ ቆዩ!

× ይህች SD (Secure Digital) Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡

× ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮምፒዩተሮች፣ በታብሌቶች፣ በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

× የሜሞሪ ካርድ በመጀመሪያ ወደ ዓለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡

× እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሜሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሜሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

× በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሜሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በኢንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡

× አብዛሃኞቹ ሜሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

× ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሜሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ፡፡

× በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡

× ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

× በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሜሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡

× Compact Flash የተባለው የሜሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡

× እነዚህ የሜሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

× እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሜሞሪ ስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር፡፡

× በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ SD CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

× አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm (mili meter) ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1TB (Tera Byte) ወይም 1000GB (Giga Byte) መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡

× ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሜሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB (Mega Byte) ነበር፡፡

× ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡

× ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-

- 16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
- 7500 ሙዚቃዎችን
- 3200 ፎቶዎችን
- ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


• ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድና የተከበራችሁ የ'Yidnek Tube' የቴሌግራም ቻነል ቤቴሰቦች! •

× ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት አምስት ነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ዌብሳይቶችን እጠቁማችኋለሁ፤ እብራችሁኝ ቆዩ!


፩ኛ. MIT Open እና Courseware

- የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው የድረ-ገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች፣ ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች የኦንላይን ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው።

- ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።

- ሊንክ፦ https://alison.com/certificate-courses?utm_source=google&utm_medium=cpc&utm_campaign=PPC>Tier-3>Product>Courses-(Broad)&gclid=Cj0KCQiAh4j-BRCsARIsAGeV12CcIrBDHwNbJVmkObIuPKFRh2NpNq03_SzlOZILG8xkijzKN9gYBIMaAlQJEALw_wcB


፪ኛ. GitHub.com

- GitHub በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድረ-ገጽ ነው።

- እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድረ-ገጽ ዓይነት ነው።

- ሊንክ፦ https://github.com/


፫ኛ. W3 Schools

- ይህ ድረ-ገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፣ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ ፕሮግራሚን ቋንቋዎች የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት ይሰጣል።

- በተጨማሪም በድረ-ገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።

- ሊንክ፦ https://www.w3schools.com/


፬ኛ. Codecademy

- አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድረ-ገጽ ነው።

- በተለይ ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።

- ሊንክ፦ https://www.codecademy.com/


፭ኛ. Stanford Engineering Everywhere (SEE)

- ይህ ድረ-ገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው።

- ድረ-ገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም፦ በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።

ሊንክ፦ https://see.stanford.edu/


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


#አምስት ነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ዌብሳይቶች!
.
.
.


.
.
.

🌍 በዓለማችን ላይ ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው ፲ (አስር) አስገራሚ ድረ-ገጾች! 🔍

× በአሁኑ ወቅት መጠኑ ይለያይ እንጂ አንዳንዶቻችን በየቀኑ የኢንተርኔት መረቦችን መቃኘታችን የተለመደ ተግባር ሆኗል።

× የምንቃኛቸው ድረ-ገጾችም ብዙ ጊዜ የምናውቃቸውን አልያም በጣም ታዋቂዎቹን ነው።

× አንዳንድ ጊዜም በፌስቡክ ወይንም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ያገኘናቸው መረጃዎች አዳዲስ ድረ-ገጾችን ያስተዋውቁናል።

× እነዚህን አዳዲስ ድረ-ገጾችም ጠቃሚ ሆነው ስናገኛቸው ለሌላ ጊዜ እንድንጠቀማቸው ቡክማርክ አድረገን እናስቀምጣቸዋለን።

× ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 10 ድረ-ገጾች ግን ምናልባትም አይተናቸው የማናውቃቸው እና የተለየ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።


፩. 10Minutemail.com

× ይህ ድረ-ገጽ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የኢ-ሜይል አድራሻ ለመክፈት ያስችላል።

× ድረ-ገጹ የተላላክናቸውን መልዕክቶች እና የኢ-ሜይል አድራሻውን ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል።

× 10Minutemail.com እንደከፈትነው ምንም ምዝገባ ሳያስፈልገን ራሱ የኢ-ሜይል አድራሻ ይሰጠናል።

× በተጨማሪም Tempmail ለዚህ ይጠቅመናል።

× አጠራጣሪ ድረ-ገጾች ስንከፍት ኢ-ሜይል ሲጠይቁን በዚህ መጠቀም እንችላለን።


፪. Fake Name Generator

× በጣም ዓይናፋር የሆኑ ፣ የግል ጉዳያቸው የሚያስጨንቃቸው እና ትክክለኛ ስማቸውን ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ ሰዎች በዚህ ድረ-ገጽ አማካኝነት የሀሰት ስም እና ዝርዝር መረጃዎችን መፍጠር ይችላሉ።


፫. Down for Everyone or Just Me

× አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተርዎ የተወሰኑ ድረ-ገጾችን አልከፍት ሊልዎት ይችላል።

× እናም በዚህ ድረ-ገጽ አማካኝነት እውን ይህ ድረ-ገጽ አልከፍት ያለዎት ስለማይሰራ ነውን? አልያስ ሆን ተብሎ እንዳይከፍቱት ስለተደረገ ነውን? የሚለውን ማረጋገጥ ይችላሉ።


፬. Date and Time

× በዚህ ድረ-ገጽ ደግሞ በቀናት እና በዓመታት መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለማስላት ይጠቅማል።

× ለአብነትም ዕድሜያችን በቀናት ለማስላት የተወለድንበትን ቀን ፣ ወር እና ዓመት እና የዕለቱን ቀን ፣ ወር እና ዓመት በማስገባት በምድር ላይ ለስንት ቀናት ቆይታ እንዳደረግን ማስላት እንችላለን።

× የምናሰላው ቀን በዓላትን እና የሳምንቱን ቀናት ማለትም ቅዳሜ እና እሁድን አካቶ አልያም ሳያካትት ስንት እንደሆነም ማወቅ ያስችላል።


፭.. Web Capture

× የተለያዩ ድረ-ገጾችን የፊት ገፅታ ምስል ለማስቀረት እና ወደ JPG ወይምJPEG ፣ PNG አልያም PDF ፎርማት ለመቀየር ይህን ድረ-ገጽ ይጠቀሙ።


፮. Google NCR

× የጉግል ድረ-ገጽን ወይም google.comን ስንከፍት ጉግል ወደ ያለንበት ሀገር ዶሜይን ያስገባናል።

× ለምሳሌ ጉግልን በኢትዮጵያ ስንከፍት google.com.et ወደሚለው ያሸጋግረናል።

× ይህም የሚሆነው ጉግል እንደየሀገራቱ የሚከለክለው እና የሚፈቅደው ህግ ስላለው ነው።

× እናም ጉግልን ያለምንም የሀገራት ገደብ ለመክፈት google.com/ncr ብለን መፈለግ በቂ ነው።


፯. Virustotal

× ከጓደኞቻችን አልያም ከማናውቀው ግለሰብ የሚያጠራጥር ፋይል ከተላከልን እና ከኢንተርኔት በቀጥታ ያወረድነውን ፋይል በዚህ ድረ-ገጽ አማካኝነት የተላከልን ፋይል ወይም ዳውንሎድ ያደርግነው ፋይል ቫይረስ መያዙን እና አለመያዙን ማወቅ እንችላለን።

× ቫይረስቶታል ነፃ የኢንተርኔት የቫይረስ መመርመሪያ (ስካነር) ነው።


፰. IPviking

× በዓለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የመረጃ ምንተፋዎች ፣ የአይፒ አድራሻዎች ፣ የመረጃ ዘራፊዎቹን (የሃከሮቹን) አድራሻ እና የመሳሰሉ መረጃዎችን http://map.norsecorp.com/#/ በተባለው ድረ-ገፅ ላይ መመልከት ይቻላል።


፱. Hackertyper

× ይህን ድረ-ገፅ ከፍተን የተለያዩ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ስንጫን መረጃ ዘራፊዎች ወይም ሃከሮች የሚጠቀሙበትን ዓይነት ገጽ ይከፍትልናል።

× በዚህም ጓደኞቻችን እና ወዳጆቻችን የተለያዩ ድርጅቶችን መረጃዎችን እየሰረቅን ለማስመሰልና ለመሸወድ እንችላለን። (ግን ሀላፊነቱን እኔ አልወስድም ፤ ተጠንቀቁ!)


፲. Password Generator

× ጠንካራ እና በቀላሉ ብሬክ የማይደረግ ማለትም የማይሰበር የይለፍ ቃል ለፌስቡክ ፣ ለኢ-ሜይል እናም ለሌሎች ፓስዎርድ ለሚጠይቁ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሙሉ ጠንካራ የይለፍ ቃል ወይም ፓስዎርድ ለመመስረት ይረዳናል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


🌎 Top 10 Amazing Websites! | ምርጥ ፲ (አስር) አስገራሚ ድረ-ገጾች! 🔍
.
.
.


.
.
.

፩. የሃርድዌር (Hardware) መቃረን

- ለዊንዶውስ (Windows) ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የሃርድዌር መቃረን ነው።

- እያንዳንዱ ሃርድዌር ክፍሎች ለመግባባት IRQ (Interrupt Request
Channel) ያስፈልጋቸዋል።

- እነዚህ IRQ ለየሃርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው።

- ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1 ነው ያለው።

- እያንዳንዱ ሃርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል።

- ግን ብዙ የሃርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሃርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሃርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ።

- በዚህም ሰዓት ሁለት የሃርድዌር
ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል።


፪. የተበላሸ ራም (RAM)

- ራም (Ram ወይም Random-Access Memory) ችግሮች ዋናው የብሉ ስክሪን ኦፍ ዴዝ (Blue
Screen of Death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልዕክት
'ፋታል ኤክሰፕሽን ኢረር' (Fatal Exception Error) የሚል ነው።

- 'ፋታል ኤክሰፕሽን ኢረር' የሚነግረን አሳሳቢ የሃርድዌር ችግር አለ ማለት ነው።

- አንዳንዴ የሃርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል።

- በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ጊዜ ራሙ ከኮምፒውተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው።

- ይህም ማለት ኮምፒውተሩ ከራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር፤ የራሱ
ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ ዓይነት ራም በአንድ ኮምፒዩተር ውስጥ ስንጠቀም ነው።

- ለምሳሌ 70ns ላይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል።

- ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ጊዜ Windows ክራሽ ያደርጋል።


፫. ባዮስ ሴቲንግ (BIOS Settings)

- እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል።

- እነዚህን ሴቲንጎች ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2
ወይም F10 እንጫናለን። (እንደ
ኮምፒውተሩ ይለያያል።)

- ኮምፒውተሩን ስንከፍት ከጥቂት ሰከንዶች
በኋላ F2ን ወይንም F10ን በመጫን ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል።

- ነገር ግን አንዴ ባዮስ ውስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።

- ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ማንሳት ወይንም ወረቀት ላይ ሴቲንጎቹን ማኖር፤ አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ ለመቀየር ያስችለናል።

- ብዙውን ጊዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው።

- የድሮ ኮምፒውተሮች ላይ ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ጊዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው።

- ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒውተሩ ክራሽ ያደርጋል
ወይም ፍሪዝ ይሆናል።


፬. ቫይረስ (Virus)

- ቫይረሶች የኮምፒውተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት
ወይም የኮምፒውተር ፋይሎች
ላይ በመጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ።

- ቫይረሶች የትዕዛዞች ስብስብ ሆነው እራሳቸውን በሌላ የኮምፒውተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ። (ብዙ ጊዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)

- ኮምፒውተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ኃይል ስላለው ኮምፒውተሩን
ክራሽ ወይም ፍሪዝ ሊያደርግ ይችላል።


፭. የሲፒዩ (CPU) መጋል

- በኮምፒውተራችን ውስጥ ካሉ ሃርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ (CPU ወይም Central Processing Unit) ነው።

- ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል።

- ሲፒዩ ብዙጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር፤ ከኮምፒውተራችን ጋር አንድ ላይ
ይመጣል።

- እነዚህ ቬንትሌተሮች ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒውተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል።

- ይህ ደግሞ በኮምፒውተራችን ላይ የ'ከርኔል ኢረር' (Kernel Error) ያስከትላል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


💻 ኮምፒውተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ (Crash) የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች!
.
.
.


• ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድና የተከበራችሁ የ'Yidnek Tube' የቴሌግራም ቻነል ቤቴሰቦች! •

× ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት አብዛኞቻችን ስማርት ስልክ (Smarphone) አለን፤ ነገርግን የት ሀገር ምርት (Product) እንደሆነ ብዙም ዕውቀቱ የለንም።

× ያንን በማስመልከት ዛሬ ከ20 በላይ ስማርት ስልኮች (Smartphones) የት ሀገር እንደሚመረቱ እናያለን፤ አብራችሁኝ ቆዩ!


፩. iPhone (አይፎን) - የአሜሪካ ምርት 🇺🇸

፪. Google Pixel (ጉግል ፒክስል) - የአሜሪካ ምርት 🇺🇸

፫. Motorola (ሞቶሮላ) - የአሜሪካ ምርት 🇺🇸

፬. Microsoft (ማይክሮሶፍት) - የአሜሪካ ምርት 🇺🇸

፭. Samsung (ሳምሰንግ) - የደቡብ ኮሪያ ምርት 🇰🇷

፮. LG (ኤልጂ) - የደቡብ ኮሪያ ምርት 🇰🇷

፯. Huawei (ሁዋዌ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፰. Lenovo (ሌኖቮ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፱. Vivo (ቪቮ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲. Oppo (ኦፖ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲፩. Xiaomi (ሺያዎሚ (ሻሚ) ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲፪. One Plus (ዋን ፕላስ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲፫. Infinix (ኢንፊኒክስ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲፬. Realme (ሪያልሚ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲፭. Redme (ሬድሚ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲፮. Tecno (ቴክኖ) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲፯. iTel (አይቴል) - የቻይና ምርት 🇨🇳

፲፰. Asus (አሱስ) - የታይዋን ምርት 🇹🇼

፲፱. HTC (ኤችቲሲ) - የታይዋን ምርት 🇹🇼

፳. Lava (ላቫ) - የህንድ ምርት 🇳🇪

፳፩. Sony (ሶኒ) - የጃፓን ምርት 🇯🇵

፳፪. Nokia (ኖኪያ) - የፊንላድ ምርት 🇫🇮


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


#ዜና_ቴክ
#Tech_News

× እንኳን ደስ አላችሁ ዩቲዩበሮች!
× Congra Youtubers!

× ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው የዩቲዩብ ቻነል ኖሮን በዩቲዩብ Community ለማስከፈት 1000 Subscribers ይጠይቅ ነበር።

× ነገር ግን አሁን ዩቲዩብ አሻሽሎት 1000 Subscribers የነበረውን ወደ 500 Subscribers ዝቅ አድርጓል።

× ይሄ ደግሞ ለጀማሪ ዩቲዩበሮች በጣም ምርጥ የሆነ ነገር ነው።

× ስለዚህ በዩቲዩብ Community ከቀጣይ ጥቅምት ወር ጀምሮ ማለትም ከOctober 12, 2021 ጀምሮ 500 Subscribers እና ከዛ በላይ ያላችሁ ዩቲዩበሮች መጠቀም ትችላላችሁ።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


ለስኳር ታማሚዎች ቆሽትን ተክቶ የሚሰራ ቴክኖሎጂ ሊቀርብ ነው!

× የዓይነት 1 የስኳር በሽታን መቆጣጠር የሚያስችል ሰው ሰራሽ የቴክኖሎጂ ሙከራ ላይ አስደናቂ ውጤት መገኘቱ ተሰማ፡፡

× ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው ይህ መሳሪያ በሰውነት ቆዳ ውስጥ በሚቀበሩ ሴንሰሮች አማካኝነት ቆሽታቸው ኢንሱሊን ማምረት ያቆመ የስኳር ታማሚዎችን (የዓይነት 1 የስኳር ሕመም ተጠቂዎችን) የስኳር መጠን ባለማቋረጥ የሚከታተል ይሆናል ነው የተባለው፡፡

× አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በቆሽት አማካኝነት አስፈላጊው የኢንሱሊን መጠን በደም ስሮች እንዲሰራጭ ትዕዛዝ ይሰጣል ተብሏል፡፡

× መሳሪያውን ታማሚዎቹ የደም ስኳር መጠናቸውን ለመለካት ፣ ለመቆጣጠር የሚወስዱትን ጊዜ ፣ በአጋጣሚ የስኳር መጠናቸው ዝቅ ብሎ ለሕይወታቸው አስጊ ሆኖ ቢገኝ ወደ ሕክምና እንኪደርሱ የሚደረሰውን ጉዳት ያስቀራልም ነው የተባለው፡፡

× እስካሁን ድረስም የዓይነት 1 የስኳር ሕመም ያለባቸው 1ሺህ ሰዎች ተለይተው የመቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂው እየተገጠመላቸው መሆኑን ዴይሊ ሜይል አመላክቷል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


#ስለ_Google_አስር_የሚያስደንቁ_ነገሮች
#10_Amazing_Facts_About_Google

× ስለጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች እነሆ!

፩. ስያሜው

- ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል

-ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።

- በእንግሊዝኛው "googol" ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።

- እናም ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው ፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።

፪. የጀርባ ማሻ

- የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው "Backrub" ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።

- ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ ፤ ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።

፫. የተንጋደደ

- ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።

- እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።

፬. ፍየሎች

- ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል ፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው።

- አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ ፤ ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።

፭. እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'

- ጂሜይል ፣ ጉግል ማፕ ፣ ጉግል ድራይቭ ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

- ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ ፤ አንድሮይድ ፣ ዩትዩብ ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።
ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።

፮. ዱድል

- "ዱድል" የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።

- ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።

- አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።

፯. ለሌሎች ያመለጠ ዕድል

-በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።

-ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።

- አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል ፤ ሚሊዮን አላልንም ፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።

፰. መሪ ቃላት

- "ከይሲ አትሁን" ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።

- "ምን አገባው" የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።

፱. ምግብማ ግድ ነው

- ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።

- የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።

፲. የጉግል ባልንጀራ

- የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።

- ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube


#ስለ_Google_አስር_የሚያስደንቁ_ነገሮች
#10_Amazing_Facts_About_Google



20 last posts shown.

46

subscribers
Channel statistics