"... ብራሶል አስቀድሞ በእርዳታ ድርጅቶች እጅ ኢትዮጵያን ሲሰልል ነበር። ስለላ ማለት ለግል ጥቅሙ እንጂ ፣ ለሀገሩ ሩሲያ ጥቅም አይደለም። ብራሶል የሚያቀርበው የጠብመንጃ ሽያጭ ሲሆን ፣ እስካሁን በዞረበት ሀገር ሁሉ ለግሉ የሚሰልለው ማዕድናትን ነው። አንድ ሀገር የእርሱ ዓይን ያርፍባት ዘንድ ብዙ ማዕድናት እንዳላት ማወቅ አለበት። የብራሶል አመለካከት እንዲህ ነው። ዓለም ውስጥ ያሉ መንግሥታት በሙሉ ማሳያዎች ናቸው። በህዝብ የተመረጡ ወይም በህዝብ ሳይመረጡ የወጡ ህጋዊ ማፍያዎች። እኛ ከዚህ የምንለየው ህጋዊ አለመሆናችን ብቻ ነው። ፖለቲካ በሚሉት የውሸት አብዮት ፣ ህዝቡን ስለማናታልል ነው።" ይላል ሁልጊዜም።
~ከመጽሀፉ የተወሰደ
🌟 ዛምራ የተሰኘው መፀሀፌን ምን ያክሎቻችሁ አንብባችሁታል?
@yismakeworku
~ከመጽሀፉ የተወሰደ
🌟 ዛምራ የተሰኘው መፀሀፌን ምን ያክሎቻችሁ አንብባችሁታል?
@yismakeworku