"የትርክት ኃይል"
ተፃፈ በ Gemechu Merera Fana
-
እዚህ ሰፈር ስንቱን አጤሪራ እያዘጋጀን በማስጠናት ሙድ ያሳየሁት Game of Thrones የተሰኘ ተከታታይ ፊልም ነበር። ( ጉራ intended)! የማይታመኑ ሱፐር ናቹራል ገቢሮች (የሞተ የሚነሳበትን፣ ድራጎን የሚበርበትን ወዘተ) የማይመቹኝን ሰውዬ ሰኞ ጠዋት 11:00 ላይ 'ፓይሬት ሳይቶች' ላይ ጠብቄ አዳዲስ ኢፒሶዶች እንዳይ ያደረገኝ ውስጡ የታጨቀው ገራሚ የቃላት ምልልስ ነው።
ሁለተኛው ሲዝን ላይ ሎርድ ቫርይስ እና ሎርድ ቲሪዮን ቁጭ ብለው ወይን እየጠጡ ይወያያሉ . . .
*
VARYS: Power is a curious thing, my lord. Are you fond of riddles?
TYRION: Why, am I about to hear one?
VARYS: Three great men sit in a room. A king, a priest and a rich man. Between them stands a common sellsword. Each great man bids the sellsword kill the other two. Who lives, who dies?
TYRION: Depends on the sellsword.
VARYS: Does it? He has neither crown nor gold nor favor with the gods.
TYRION: He has a sword, the power of life and death.
VARYS: But if it's swordsmen who rule, why do we pretend kings hold all the power? When Ned Stark lost his head, who was truly responsible? Joffrey? The executioner? Or something else?
TYRION: I've decided I don't like riddles.
VARYS: Power resides where men believe it resides. It's a trick, a shadow on the wall. And a very small man can cast a very large shadow.
*
አራት ሰዎች አሉ። ንጉሥ፣ ካህን፣ ባለሀብት እና ቅጥር ነፍሰገዳይ። የመጀመሪያዎቹ ሦስቱ ነፍሰገዳዩን ተመሳሳይ ነገር ነው የሚያዝዙት። ወደሁለቱ ጠቁመው "ግደላቸው" ነው የሚሉት። ከሦስቱ ኃይለኛው ማናቸው ናቸው፣ ነፍሰገዳዩሰሰ የማንን ትዕዛዝ ይፈፅማል? ነው ጥያቄው። በቫርይስ ዕንቆቅልሽ/ተረት ውስጥ ነፍሰገዳዩ ሕዝብን ነው የወከለው።
ነፍሰገዳዩ ኃይማኖተኛ ከሆነ ንጉሡንና ባለሀብቱን ይገላል። መንግሥትን ማገልገልና መታዘዝ አለብኝ ካለ ካህኑንና ባለሀብቱን ይገላል። የሚሻለኝ ሀብት ነው ካለ ደግሞ ንጉሡንና ካህኑን ይገድላል። ከሦስቱ ሰዎች በobjective መለኪያ ኃይል ማናቸውም ጋር ቢኖር ዋጋ የለውም፣ ነፍሰገዳዩ ኃይል አለው ብሎ የሚያምንበት ሰው ብቻ ነው ከሞት የሚተርፈው። ኃይል subjective ነው። የሚመጣው ደግሞ በትርክትና በድርጊት ነው።
በቫርይስ እንቆቅልሽ/ተረት ነፍሰገዳዩ ሕዝብን ነው የሚወክለው። ሕዝቡ የሚያምንበትን ራሱ ይመርጣል። ሕዝብ ኃይል አለው ብሎ የሚያምንበት አካል ኃይል ይኖረዋል። የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተለያዩ ገዢ dominant ትርክቶች አሉ። ለአንዳንዱ የድል፣ ለሌላው የዕስር ትርክቶች (and the vice versa) ናቸው። በየአካባቢው ትርክቶቹን የሚጠቀሙባቸው እንዳሉ ሁሉ፣ የትርክቱ ታጋቾች (hostages of that narrative) አሉ። ለዚህ ነው ሁሉንም ወደመሀል የሚያመጣ ትርክት የሚያሻው። 'What's history but a fable [we] agreed upon እንዲሉ!
"Power resides where men believe it resides."
* * *
ከጥቂት ዓመታት በፊት ነው። ከሀገራችን ከተሞች ውስጥ በአንዷ ባርና ሬስቶራንት ያላት አንድ ጓደኛዬ ቤት የተፈጠረ ነው። ሁለት ሰራተኞቿ ተጣልተው ካለችበት ተደውሎ ተጠራች። ዘበኛውና ወጥ ቤቷ ናቸው የተጣሉትና ቤቱን ቀውጢ ያደረጉት።
ወጥ ቤቷ ታለቅሳለች። "በቃ አሰናብቺኝ!" ብላ ኡኡ ትላለች። ምክንያቷን በብዙ ልመና ተጠይቃ ተናገረች። ዘበኛው ሰድቧት ነው። ዘበኛውና ወጥ ቤቷ የሁለት የተለያዩ ብሔር አባላት ናቸው። (አልጠቅስም)። እና ዘበኛው "እናንተማ ጠገባችሁ! ልክ አስገባሻለሁ አንቺ ጥምብ *ብሔር*" ብሏታል። አበደች። እና ለጓደኛዬ እያለቀሰች ብሶቷን፣ ስድቧን ስትናገር እንዲህ አለቻት
"እኔን "ጥምብ *ብሔር*"ይለኛል እንዴ?! እሱ የትኛውን ትግሬ/አማራ/ኦሮሞ ሆኖ ነው?!"
*
"Power resides where men believe it resides." Varys