ታላቁ የበድር ዘመቻ
ክፍል 2
☆የጦርነቱ ታሪክ
ኢብኑ ኢስሃቅ እንዳለው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የተወሰኑ የረመዷን ወር ቀናት ካለፉ ነበር ለዚህ ተልእኮ የወጡት። ሰኞ ቀን ስምንት የረመዷን ወር ቀናት ካለፉ በኋላ ነበር። ዐብዱላህ ኢብኑ ኡም መክቱምን በመዲና ሰላት ላይ አቡ ሉባባን ደግሞ የመዲናን ሁኔታ እንዲቆጣጠርን እንዲያስተዳደር ሀላፊነት ሰጥተው ወጡ።
በወቅቱ የሙስሊሞች ቁጥር ሦስት መቶ አሥራ ሦስት ሰዎች ነበር። መቶ አርባ ምናምን የሚሆኑ ሰዎች ከአንሷር /የመዲና ሰዎች/ ነበሩ፤ የተቀረው ቁጥር ከሙሃጅሮች /ከመካ ወደ መዲና የተሠደዱ ሰዎች/ ነበር። ሙስሊሞቹ ሁለት ፈረስ እና ሰባ ግመሎች ነበሯቸው። የባንዲራቸው ተሸካሚ የነበረው ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር ሲሆን የበድር ጦርነት የዋለው ጁሙዓ ጠዋት ረመዷን አሥራ ሰባተኛው ቀን ነበር።
አቡ ሱፍያን የሙስሊሞችን መውጣት አወቀ
አቡሱፍያን እጅግ ንቁ እና ጠንቃቃ ሰው ነው። ነገሮች ይዘው የሚመጡትን መጨረሻ ይገምታል። ቁረይሾች በሙስሊሞች ላይ የሠሩትን ግፍ ጠንቅቆ ያውቃል። እያደገ ያለውን የሙስሊሞች ሀይል ሁኔታም በቅርብ ይከታተላል። ከሻም ግዛት ወጥቶ ሂጃዝ ዋናው የዐረቢያ ምድር አካባቢ እንደደረሠ የመዲና ሙስሊሞችን ሁኔታ መሠለል ያዘ። ለንግድ ቅፍለቱም ፈርቶ በነሱ አካባቢ የሚያልፈውን መንገደኛ ሁሉ የአካባቢውን ሁኔታ ያጠያይቅ ነበር። በመጨረሻም የተወሰኑ መንገደኞች ሙሀመድ እና ባልደረቦቹ የንግድ ቅፍለት የሆነችውን የመካን ግመሎች ለመከታተል የወጡ ስለመሆናቸው ወሬ ደረሠው። በዚህን ጊዜ የጥንቃቄ እርምጃ ወሠደ። መንገድ ከመቀየሩም ባሻገር በመካ ላሉ ቁረይሾችም የድረሱልኝ መልእክት ላከ።
የቁረይሾች መውጣት
አቡ ሱፍያን ወሬውን እንዲነግርለት ደምደም ኢብኑ ዐምር አል-ጊፋሪን ቀጠረ። እሱም አፍንጫው በተቆረጠ ግመል ላይ ሆኖኮርቻውን አዙሮ ቀሚሱን ቀዳዶ እንዲህ በማለት እየጮሀ መካ ደረሠ “እናንተ ቁረይሾች ሆይ! እናንተ ቁረይሾች ሆይ! ከአቡሱፍያን ጋር ያለ ሀብት ንብረታችሁን ሙሀመድ እና ባልደረቦቹ ሊዘርፉ ወጥተዋል። ልትደርሱለት ግድ ነው። ድረሱላቸው! ድረሱላቸው!።” ቁረይሾች ይህን ባወቁ ጊዜ ለንግዳቸው ፈሩ። በፍጥነትም ተሰባሰቡና ቅፍለታቸውን ለማዳን ወጡ። ከነሱ ጋርም ዋና አለቆቻቸውና መሪዎቻቸው ነበሩ። ቀንደኛ የኢስላም ጠላት ከነበረው ከአቡ ለሀብ ኢብኑ ዐብዱልሙጦሊብ /የነቢዩ አጎት/ በስተቀር ማንም የቀረ አልነበረም። እሱም ቢሆን በምትኩ አል-ዓስ ኢብኑ ሂሻም ኢብኑ አል-ሙጊራህን ልኮ ነበር። በዚሁ ቁረይሾች ለመውጣት ከስምምነት ደረሱ። ሙስሊሞችን እንደሚያዋርዱና በደሞቻቸው እንደሚጫወቱ በማሰብ ደስ እያላቸውና እየፎከሩ ወጡ። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ
وَإِذْ زَيَّنَ لَهُمُ الشَّيْطَانُ أَعْمَالَهُمْ وَقَالَ لَا غَالِبَ لَكُمُ الْيَوْمَ مِنَ النَّاسِ وَإِنِّي جَارٌ لَّكُمْ
“ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና ‘ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ’ ባለ ጊዜም (አስታውስ)፡፡” (አል-አንፋል 8፤48)
☆የቁረይሾች የንግድ ቅፍለት ማምለጥ
አቡ ሱፍያን በበኩሉ ተከላካይ የቁረይሽ ጦር ከመካ እስኪመጣለት ድረስ በቦታው ላይ ቆይቶ አልጠበቀም። በራሱ በኩል የቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ ማምለጫ ዘዴዎችን አፈላለገ። በደረሰበት ሁሉ የሙስሊሞችን ሁኔታ ይጠይቃል፤ ወሬዎችን ያነፈንፋል፤ ይተነትናልም። መጅዲ ኢብኑ ዐምር የተባለ ሰው ባገኘ ጊዜ በዚህ ሰሞን “አዲስ ያስተዋልከው ነገር አለን?” በማለት ጠየቀው። እሱም “የማስታውሰው ብዙም ነገር የለኝም። ነገርግን ሁለት መንገደኞች መጡና ግመሎቻቸውን እዚህ በማሰር ከያዙት ስልቻ ውስጥም ውሃ በመጠጣት ከዚያም ተመልሰው ሄዱ።” አለው
አቡሱፍያንም ግመሎቻቸውን አስረው ወደነበረበት በመምጣት ከእንሠሦቹ የቀረውን በጠጥ በማንሣት ሲበትን እውሰጡ ደረቅ ፍሬ አገኘ። ከዚያም “ወላሂ ይሄ የየስሪብ መኖ ነው።” አለ። ሁለቱ ሰዎችም የሙሀመድ ወገኖች መሆናቸውን ገመተ። የሙስሊሙ ጦርም እዚህ አካባቢ መሆን አለበት ሲልም አሠበ።
ወደ ግመሎቹ ቅፍለትም በመመለስ ወደ ኋላ እንዲመለሱ ካደረገ በኋላ መንገድ በማስቀየር በድርን በግራ በኩል በመተው የባህር ሰርጡን ተከትሎ በመጓዘ ቅፍለቱን ይዞ አመለጠ።
የሙሽሪኮች ትእቢት እና በጦርነት አቋም ስለመፅናታቸው
የሙሽሪኮች ጦር በሰፊው በረሃ ላይ እንዲሁም በመካና መዲና መንገድ በሚገኙ ተበታትነው በሠፈሩ ጎሣዎች መካከል እየፎከረና እያቅራራ የጦር ሀይሉንም እያሞጋገሠ አቡሱፍያንን ከሙስሊሞች እጅ ለማስጣል በማሰብ ወደፊት ገሠገሠ። የአቡሱፍያን ቅፍለት ግን ጥቃት ሣያገኛት አመለጠች። አቡሱፍያን ሰላማዊ ሜዳ ላይ መውጣቱንና ከሙስሊሞች ከበባ ማምለጡን በተረዳ ጊዜ ወታደሮቿን አሰባስባ እርሱን ለማዳን እየመጣች ላለችው የቁረይሽ ጦር መልእክት ላከ። “አምልጠናልና ተመለሱ።” በማለት። የአቡሱፍያን መልእክተኛም የሙሽሪኮችን ጦር መንገድ ላይ አገኛቸው። የንግድ ቅፍለቶቹ በሰላም ያመለጡ መሆኑንም ነገራቸው። ነገርግን አቡ ጀህል በትእቢት እና በጉራ እንዲህ አለ “ወላሂ በድር ሣንደርስና ሦስት ቀን እዚያ ሳንቆይ አንመለስም። ግመሎቻችንን እናርዳለን። ምግብ እናበላለን። መጠጥ እንጠጣለን። እውቅ ሴቶችም ይዘፍኑልናል። ዐረቦች ሁሉ ስለኛ መሄድና መሰብሰብ መስማት አለባቸው። ይህንንም በመስማት እስከመጨረሻው ይፈሩናል።” ቁረይሾች የአቡጀህልን ሀሣብ በመቀበል ተጓዙ። የጎሣዎች አለቆችም ሰዎች “ፈሪዎችና ቦቅቧቆች” ይሉናል ብለው በመፍራት ተከተሏቸው። መሹረት አል-አክነስ ኢብኑ ሸሪቅን የተከተሉ የበኑ ዙህራ ሰዎች ሲቀሩ ሌላ ማንም አልተመለሠም ነበር። እሱም በነሱ ውስጥ ተሰሚነት ያለው አለቃ ነበርና ተመለሱ ባላቸው ጊዜ ተመለሱ።
☆የበድር ጦርነት ክስተቶች
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የወጡት የቁረይሽን የንግድ ግመሎች ለማግኘት ነበር። ወደርሣቸው መንቀሣቀስ ላይ ስለነበረው የቁረይሽ ጦር ግን ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም። ከመዲና ውጭ ለጦር ዝግጅት ካምፕ ጣሉ። አማኙን የሙስሊም ጦርም አሰባሰቡ። ለመዋጋት አቅማቸው ያልደረሰውንም መለሱ።
☆የሁለቱ ወገኖች ሀይል
የሙስሊሞች ሀይል
በነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የተመራው የሙስሊሙ ጦር ቁጥር ሦስት መቶ አሥራ ሦስት ሰው ነበር። ከነኚህም መካከል ሁለት ፈረሰኞች የዙበይር ኢብኑ አል-ዐዋም እና የሚቅዳድ ኢብኑ ዐምር ፈረሦች ሲሆኑ ሰባ ግመልም ተራ በተራ ይፈናጠጡ ነበር።
https://t.me/youthmission
https://t.me/youthmission
በአላህ ፍቃድ ክፍል 3 ይቀጥላል!!!