New Single Song
ተሻገርኩበት
ወ/ም ሹሜ ኤልያስ
ዘንድሮን እንኳን አልሻገርም
በህያዋን ምድር በቃ አልኖርም
ብዬ ተስፋዬን በቆረጥኩበት
ምህረትህ በዝቶ ተሻገርኩበት
ለኔ ድልድይ መሸጋገርያ
በፍርሀት ቀኔ ለኔ መመኪያ
ኢየሱስ ሁሌ የልቤ ሙላት
ምተማመንህ የኔ ውድ አባት
አፌ ያቀርባል ምስጋና
አድርገኸኛልና ቀና ቀና
ክብር እልልታ ቤትህን ይሙላ
አሻግረኸኛል ሆነኸኝ ጥላ
በጥማት መሬት በምድረበዳ
በጠላት ቀስቶች ነፍሴ ተሰዳ
ረዳት የለዉም ህዝብ ሁሉ ሲለኝ
ከሰማይ ነበር እኔን ሚረደኝ
ልቤ በፍርሀት በሀዘን ተሞልቶ
የሚይዘውን ስያጣ ተስፍ ተሟጦ
ለካስ ሚረዳኝ ችግረን ሁሉ
መቶ አፅናኝ ኢየሱስ በቃሉ
ምስጋናን እንጂ ምን እከፍላለዉ
ያለኝን ይዤ ፊትህ እቀርባለዉ
የደስታን መዝሙር ልቤ አፍልቆ
ያመሰግንሀል ወጥመድ ተሰብሮ
@zemeru
@zemeru
በማስተዋል ዘምሩ Telegram Chennel JOIN US for more Updates!