የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወርሃዊ ደሞዛቸው 20ሺህ ብር መሆኑን አመለከቱ
👉🏼 ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ከአምስት አመታት ገደማ> ማለታቸዉን ተከትሎ የከንቲባዋ እና የጠ/ሚኒስትሩ ደሞዝ ተቀራራቢ ሆኗል
የአዲስአበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን ያመለከቱት ዛሬ < ጽዱ ኢትዮጵያ > ለተሰኘው የገንዘብ መዋጮ < ሙሉ ደሞዛቸውን > ማበርከታቸውን በገለፁበት ወቅት ነው።
አዳነች በተረጋገጠ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰራጩት ፅሁፍ ንቅናቄን ተቀላቅያለሁ >> ሲሉ ማስፈራቸዉን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል። ከንቲባዋ ወርሃዊ ደሞዛቸው 20ሺህ ብር መሆኑን መግለፃቸውን ተክትሎ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወርሃዊ ደሞዝ ጋር ተቀራራቢ ስለመሆኑ አሻም ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከአምስት ዓመታት በፊት በአንድ መድረክ ባደረጉት ንግግር ወርሃዊ ደሞዛቸው 400 የአሜሪካ ዶላር ገደማ መሆኑን መግለፃቸው ይታወሳል።
ጠ/ሚ ዐብይ በወቅቱ ለተነሱላቸው በርካታ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ > ብለው ነበር።
በዚሁ ንግግራቸው የተነሱ ጥያቄዎች የሰፈሩበትን ማስታወሻ ወረቀት ወደላይ ከፍ አድርጎ በማሳየት አክለው እንደተናገሩት > ብለው ነበር።
ጠ/ሚ ዐብይ ደሞዛቸውን በይፋ ከገለፁ በኋላ በከፍተኛ የመንግስት ተሿሚነት በግልጽ ደሞዛቸውን የተናገሩት ከንቲባዋ መሆናቸውን አሻም ለዚህ ዘገባ ባደረገችው መጠነኛ ማጣራት ለማወቅ ችላለች።
ይህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከዓመታት በፊት የገለፁት የደሞዝ መጠን [ ጭማሪ ካልተደረገበትና በወቅቱ የዶላር ምንዛሬ መሠረት ] ከከንቲባ አዳነች ጋር ተቀራራቢ ይሆናል ስትል አሻም መዘገቧን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።
ምንም እንኳን ዐብይ በዛሬው ዕለት ይህን ንቅናቄ ተከትሎ ድጋፍ ላደረጉት ምስጋና ቢቸሩም፣ ያልተሳተፉትም ሚናቸውን እንዲወጡ ቢጠይቁም፤ በእርሳቸው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንደሌሎቹ ባለስልጣናት ወደባንክ ያስገቡት ገንዘብ ስለመኖሩ በገፃቸው ላይ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተቀመጠ ማስረጃ የለም።
#ዳጉ_ጆርናል