በተሸከርካሪ አደጋ በ 27 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ
የካፋ ዞን ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ዳዊት ደሳለኝ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት መነሻውን ቴፒ በማድረግ ወደአዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ሀበሻ ዘመናዊ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ኮድ 3-98954 ኢት ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከማለዳው 12፡30 በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ የብጦ ቀበሌ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰ አስታውቀዋል፡፡
በአደጋው በ16 መንገደኞች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 13ቱ ሴቶች ሲሆኑ በ11 ተሳፋሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ኢንስፔክተር ዳዊት ተጎጂዎች ቦንጋ ገብረፃዲቅ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡
አደጋው የደረሰው መንገዱ ጠመዝማዛ መሆኑን አመልክተው የአደጋውን ምስኤ የትራፊክ ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አመልክተው ተጎጂዎችን በማንሳት ወደ ህክምና በመውሰድ የተባበሩ የቀበሌው ነዋሪዎችን እና የጊምቦ ወረዳ ፖሊሶችን አመስግነው አሽርካሪዎች ፍጥነታቸውን ቀንሰው እንዲያሽረክሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡ ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሽ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽ ዘግቧል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል