በአዲስ አበባ የትራፊክ መብራት ላይ ምጽዋት የሰጡና ግዡ የፈፀሙ 300 ደንብ ተላላፊዎች መቀጣታቸው ተነገረ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በግንዛቤ ላይ የተደገፈ ቁጥጥር፣ የኦፕሬሽን ስራዎች የፓርኪንግ ልማትና አስተዳደር፣ የትራፊክ መብራቶች ተከላና ጥገና እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ትግበራ ሲያከናውን እንደቆየ ተገልጿል ።
በዚህም በሩብ ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ግጭትን አስቀድሞ ለመከላከል በግንዛቤ ተደግፎ በተካሄደው የቁጥጥር ስራ ከ16 ሺህ የሚበልጡ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንቦችን ጥሰው የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸው ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል ።
በተለይም ለትራፊክ ግጭት ቀዳሚ መንስኤዎች ናቸው ተብለው በተለዩ ጥፋቶች በጠጥቶ ማሽከርከር 3452 ፣ በ33 መስመሮች ላይ በተካሄደ የፍጥነት ቁጥጥር ከ7ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች፣ የደህንነት ቀበቶ ሳያድርጉ ያሽከረከሩ 2211 አሽከርካሪዎች ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል ።
በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ ስልክ እያወሩ ያሽከረከሩ 3161 አሽከርካሪዎች የተቀጡ ሲሆኑ በየደረጃው 126 የጭንቅላት መከላከያ ቆብ ሄልሜት ሳያደርጉ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ተቀጠዋል ። ከዚህ በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ መብራት ላይ ለልመና ምጽዋት የሰጡና በጥቃቅን ንግድ እንቅስቃሴ የተለያዩ ቁሶችን የገዙ 300 ደንብ ተላላፊዎች በየደረጃው መቀጣታቸው ተጠቅሷል፡፡
ከዚህ ባለፈም በቁጥጥሩ ስራው ምልክቶችና አመላካቾች እንዲከበሩ ማድረግ፣ በራዳር ቴክኖሎጂ የፍጥነት ቁጥጥርና የማስተማር ስራ፣ በመንገድ ላይ ለረጅም ጊዜ የቆሙ ባለቤት የሌላቸዉን ተሸከርካሪዎች መረጃ በማሰባሰብ እንዲነሱ የማድረግ ስራ መሰራቱ ተነግሯል ።
እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች ብቻ መስመሮችን የማስጠበቅ፣ የመንገድ መጋጠሚያዎችና ተርሚናሎች አካባቢ ስርዓት የማስያዝ ስራ ስለመሰራቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል ።
በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል