ደቡብ አፍሪካ ዌስት ባንክን ወደ እስራኤል ለመቀላቀል የቀረበውን ጥሪ አወገዘች
በቀጣዩ 2025 ዓመት የፍልስጥኤል ግዛት የሆነችውን ዌስት ባንክ ወደ እስራኤል የምትጠቃለለበት ዓመት እንደሚሆን የእስራኤል የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች የሰጡትን መግለጫ ደቡብ አፍሪካ አውግዛለች።
የአለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ዲፓርትመንት መግለጫ የተሰማው ስሞትሪች በእስራኤል በኃይል በተያዘው ግዛት ሰፈራዎች እንዲደረግ ዝግጅት ማዘዛቸው ከተናገረ በኋላ ነው። መምሪያው እስራኤል በፍልስጤም ግዛቶች ላይ የምታደርገውን የሰፈራ መስፋፋት እና ጨብ ቀስቃሽ ፖሊሲዎችን በመቃወም በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ወሳኝ ምላሽ እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥቷል።
የእስራኤል የህዝብ ማሰራጫ ጣቢያ ካን ባሳለፍነው ማክሰኞ እንደዘገበው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጥር ወር ስልጣን ሲይዙ የዌስት ባንክን ወደ እስራኤል የመቀላቀል አጀንዳ እንደገና ለማስተዋወቅ አቅደዋል።
እ.ኤ.አ. በ 2020 ኔታንያሁ በዌስት ባንክ እና በዮርዳኖስ ሸለቆ ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ የእስራኤል ሰፈራዎችን በትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ መሰረት ለማካተት አቅደዋል። ኔታንያሁ በትራምፕ የመጀመሪያው አስተዳደር ወቅት ለመጠቅለል ካቀዱት ግዛቶች ከዌስት ባንክ 30 በመቶ ያህሉን ነበር።
እቅዱ ግን በአለም አቀፍ ጫና እና በአሜሪካ ይሁንታ እጦት እውን ሊሆን አልቻለም። አለም አቀፍ ህግ ዌስት ባንክን እና ምስራቅ እየሩሳሌምን ሁለቱንም እንደ "የተያዙ ግዛቶች" ይመለከታቸዋል። ሁሉንም እስራኤላውያን የሚያደርጉትን የሰፈራ ግንባታ ስራዎችን እንደ ህገወጥ ድርጊት ይመለከቷቸዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል