የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከጋዛ ለተፈቱ ምርኮኞች የ5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አበረከቱ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እንደተናገሩት ከጋዛ ለተፈቱ ምርኮኞች 5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ እና በሃማስ የተያዙ እስራኤላውያንን ነፃ ለማውጣት በጦርነት ከታመሰው የፍልስጤም ግዛት እንዲወጡ ይደረጋል ሲሉ ተደምጠዋል። ኔታንያሁ ስጦታውን ይፋ ያደረጉት በትላንትናው እለት በጋዛ ባደረጉት አጭር ጉብኝት ላይ ሲሆን የእስራኤል ወታደራዊ ኔትዛሪም ኮሪደር በእስራኤል ጦር ሰሜናዊ ጋዛን ከደቡብ ክፍል ለመገንጠል የሚያስችል ቁልፍ መንገድ ባሳዩበት ወቅት ነው።
ለእያንዳንድ ታጋቾች 5 ሚሊዮን ዶላር እንሰጣለን ሲሉ ኔታንያሁ በፍልስጤም ግዛት ባደረጉት አጭር ጉብኝት ተናግረዋል። ምርጫው ታጋቾችን ለሚያስለቅቁ በሙሉ ይህ ነው ግን ውጤቱ አንድ አይነት ይሆናል ሁሉንም ታጋቾች እንመልሳቸዋለን ብለዋል። እስራኤል 101 ምርኮኞች በጋዛ እንደሚቀሩ ገምታለች፣ ምንም እንኳን ከቁጥሩ ውስጥ አንድ ሶስተኛው አሁን ላይ እንደሞቱ ይታመናል። የኔታንያሁ የሽልማት ስጦታ በእስራኤል ውስጥ በምርኮኛ ቤተሰቦች እና ደጋፊዎቻቸው ዘንድ ያስቆጣ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሃማስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደርሱ በመጠየቅ ምርኮኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
ኔታንያሁ ሁሉንም ምርኮኞች ለማስፈታት ብቸኛው መንገድ ወታደራዊ አማራጭ እንደሆነ እና እስራኤል በጋዛ ላይ ያካሄደችው ጦርነት አላማው እስኪሳካ ድረስ እንደሚቀጥል ደጋግመው ተናግረዋል።ቀደም ሲል ከሃማስ ጋር የተደረሰውን የእርቅ ስምምነት ለማፍረስ የናታንያሁ መንግስት የቀድሞ ረዳት የነበሩት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለውጭ ሚዲያ በማጋለጥ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሲሆን የታሳሪው ቤተሰቦች የኔታንያሁ መንግስት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ በቂ እርምጃ አልወሰደም ሲሉ ከሰዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል