በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ
በኦሮሚያ ክልል ከህዳር 2 እስከ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ13 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣በ17 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ10 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰው አደጋ ከ12 ዓመት እስከ 65 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
በንብረት ላይ የደረሰው ወድመት በገንዘብ ሲተመን ከሦስት መቶ ሺ ብር በላይ የሚገመት ሲሆን የሞት አደጋዎቹ በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች የተከሰቱ ናቸው።
አደጋዎቹ የተከሰቱት በቀኑ እና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ሲሆን አደጋውን ያደረሱት ወንድ አሽከርካሪዎች ናቸው። የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት፣ በህዝብ ማመላለሻ እና በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) ተሸከርካሪ የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የአደጋዎቹ መንስኤዎቹ ያለመንጃ ፍቃድ ማሽከርከር ፣ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር፣ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር፣ ምልክቶችን አለማክበር ፣የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል::
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል