በእንግድነት ለበርካታ ቀናት በመቆየቱ ወደ ቤቱ እንዲሄድ የተጠየቀው ግለሰብ በአባወራው ላይ የግድያ ሙከራ በመፈፀሙ በእስራት ተቀጣ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የግድያ ሙከራ የፈጸመው ተከሳሽ ፈይሳ ቢፋ በእስራት መቀጣቱን ያሳያል።
የወንጀሉን ዝርዝር አቃቤ ህግ እንዳስረዳው ተከሳሽ ፈይሳ ቢፋ ሰውን ለመግደል በማሰብ ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 7 ላይ በቀቤና ልዩ ወረዳ ልዩ ስሙ ጀረትማ ተብሎ በሚጠራው መንደር በግል ተበዳይ በአቶ ኢብራሂም ሀሰን መኖሪያ ቤት ውስጥ ተከሳሹ በእንግድነት ለማደር መግባቱን እና በርካያ ቀናትን በመቆየቱ ምክኒያት በቤቱ ባለቤት እንዲሄድ ቢጠየቅም አልሄድም በማለት ግጭቱ ተጀምሯል።
አልሄድም ከማለት ባለፈ እላፍ ንግግሮችን ተናግሮ አንደነበር የተበዳይ ባለቤት እንደተናገሩ የቀቤና ልዩ ወረዳ የወንጀል ጉዳዩች ከፍተኛ አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ በያን ሙሳ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በዕለቱ ተከሳሹ በቤቱ ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውለውን ቢላዋ በማንሳት የግል ተበዳዩን በስለት የቀኝ እጁ ሰዓት ማሰሪያው ላይ አንድ ጊዜ ሲቆርጠው በተጨማሪም የቀኝ እጁ አውራ ጣቱን፣ በቀኝ በኩል መንጋጋውን፣ የቀኝ ጆሮውንና ትከሻውን በቢላዋ በመውጋት ከፍተኛ ደም እንዲፈሰው በማድረግ የቀኝ እጁ ላይ የአጥንት ስብራት ያደረሰበት መሆኑን በክሱ ላይ ገልጿል።
አቃቤ ህግም በ1997 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣው የኤፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27/1 እና አንቀጽ 539 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ ተላልፏል በሚል በከባድ የግድያ ሙከራ ወንጀል ክስፍቅር አቅርቦበታል።የክስ ሂደቱን ሲከታተል የቆየው የቀቤና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ተከሳሽ ፈይሳ ቢፋ በቀለ አቃቤ ህግ የከሰሰውን የከባድ የግድያ ሙከራ ወንጀል ህግ ድንጋጌውን 113 / 2/ መሠረት በማሻሻል ወደ ወንጀል ህግ ቁ 540 ድንጋጌ ወደተራ የግድያ ሙከራ ወንጀል በመቀየር ጥፋተኛ ብሎታል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በማየት የቀረቡትን የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችን በመመዘን ሌላውን ያስተምራል ተከሳሹንም ያርማል በሚል ተከሳሽ ፈይሳ ቢፋን በ5 ዓመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የቀቤና ልዩ ወረዳ የወንጀል ጉዳዩች ከፍተኛ አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ በያን ሙሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል