በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሶስት ወራት አምስት የከባድ ማሽነሪ ማሠልጠኛ ተቋማት ታግደዋል
የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የአሽከርካሪ ዘርፍ የ2017 ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመታት እቅድ አፈፃፀም መሰረት ለ 18 ሺ 10 አሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጥ መቻሉን እንዲሁም 55 ሺ 8 መቶ 2 መንጃ ፈቃድ እንዲታደስ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ባለፉት ሶስት ወራት ለ3 ሺ 4 መቶ 35 የኢንተርናሽናል መንጃ ፈቃድ አገልግሎት መሥጠት መቻሉን በባለስልጣኔ የኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም አሰፋው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው ለረጅም ጊዜ የቆዩ የደረጃ መንጃ ፈቃድ እድሳት የተግባር መለማመጃ ቦታ እንዲሁም የቀጠሮ እና የፈተና አጭር የፅሁፍ መልዕክት የነበሩ ክፍተቶች መፈታቱንም ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣኑ 131 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ድጋፍ እና ክትትል ማድረጉን አክለው ገልፀዋል።በተጨማሪም በተደረገው ክትትል ብቁ አሽከርካሪ ለማፍራት የተቀመጠውን አሰራር ተግባራዊ ያላደረጉ 5 የከባድ ማሽነሪ ማሠልጠኛ ተቋማት ፍቃድ መታገዱን ገልፀዋል። እንዲሁም አንድ ማሰልጠኛ ተቋም ህግ እና መመሪያ በመጣሱ ፍቃዱ ተሰርዞበታል ብለዋል። በአስራ አራት የባለስልጣኑ ሰራተኞች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ መወሰዱን ወ/ሮ ሰርካለም አሰፋ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
በሰመኃር አለባቸዉ
#ዳጉ_ጆርናል