በአሜሪካ የእንስሳት ድምፅ ረበሸኝ በማለት ለፖሊስ ቅሬታ ያቀረቡት አዛውንት የእንስሳ ድምፅ የመሰላቸው በቤታቸው ውስጥ በድብቅ የሚኖር ሰው ሆኖ ተገኘ
ከቤታቸው ስር የሚሰማው ድምፅ ከእንስሳት የተሰማ ነው ብለው ያሰቡ የካሊፎርኒያ አዛውንት ሴት ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት እርቃኑን ከቤታቸው ስር የሚኖር ሰው በመገኘቱ ድንጋጤ ውስጥ ወድቀዋል።
በሎስ አንጀለስ ኤል ሴሬኖ ሰፈር ነዋሪ የሆኑት የ93 ዓመቷ አዛውንት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ከቤታቸው ስር መስማት የጀመሩት አስደንጋጭ ጩኸት የዱር እንስሳት ይሆናል ብለው ቢገምቱም የሰው መሆኑ ሲገነዘቡ በሕይወታቸው ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል። አዛውንቷ እና ቤተሰባቸው ብዙውን ጊዜ በሌሊት ከቤታቸው ምድር ቤት ያልተለመዱ ድምፆችን ይሰሙ ነበር። እናም ውሻ ወይም የዱር አራዊት ናቸው ብለው ገምተው ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጩኸቱ በተለይ ጠንከር ያለ እና የእግር ኮቴ መሰማት ይጀምራል።
በስፍራው ላይ የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር እንዳለ መጠራጠር ጀመሩ፣ ጉዳዩን ለፖሊስ ባደረጉት ሪፖርይ መሰረት አንድ እርቃኑን እዛው ቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ይኖር የነበረን ሰው ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ ማግኘት ችሏል።ብዙውን ጊዜ ምሽት ላይ ከቤታችን ምድር ቤት ላይ በእንስሳት ድምፅ እንሳቀቅ ነበረ ሲሉ የቤት ባለቤቷ አዛውንት አማች ሪካርዶ ሲልቫ ለኤንቢሲ ሎስ አንጀለስ ተናግራለች። ድምፆቹ እንደ ማንኳኳት የሚመስሉ እና ባለቤቴ ወለሉ ላይ ሲራመድ፣ ከቤቱ ስር ሆነው ያንኳኩ ነበር፣ እናም የሆነ ችግር እንዳለ ይታውቅኃል ብላለች። ያልተጋበዘውን እንግዳ ከቤቱ ስር ማስወጣት ከፍተኛ ስራ የጠየቀ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በግለሰቡ መውጣት ባለመፈለጉ የተነሳ ነው።
ፖሊስ ግለሰቡ ወደ ውጭ ወጥቶ ለማነጋገር ለሰዓታት ያህል አሳልፏል። ከዚያም በፖሊስ ውሾች ሊያስፈራሩት ሞክረዋል፣ ነገር ግን ምንም የተጨነቀ አይመስልም። በመጨረሻ ከቤቱ ምድር ቤት በአስለቃሽ ጭስ አስገድደው ለማስወጣት ችለዋል።በመጀመሪያ ለመውጣት ፈቃደኛ አልሆነም። የፖሊስ ውሾቹን አልፈራም እንዲሁም ሁለት አስለቃች የጋዝ ሙከራዎች አላስፈራሩትም ተብሏል።
ሪካርዶ ሲልቫ እንዳለችው ይህ በጣም ያልተለመደ እንግዳ ነገር ነው፣ ግን ደግሞ ምናልባት ያልተለመደ ላይሆን ይችላል፣በዚህ ዘመን ሰዎች መጠለያ እየፈለጉ በመሆኑ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ። እርቃኑን የነበረው ሰው የ27 ዓመቱ ኢሳክ ቤታንኮርት የተባለ ሲሆን ላለፉት ስድስት ወራት በኤል ሴሬኖ ቤት ውስጥ እንደኖረ ተጠርጥሯል። ቤተሰቡ አሁን ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ለመከላከል በጠቅላላው ቤት ስር ያለውን ባለ 2 ጫማ ከፍታ ያለው የመንሸራተቻ ቦታ ለመዝጋት አቅዷል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል