በራያ ቆቦ በዘጠኝ ህፃናት ላይ አስገድዶ መድፈር የፈፀመዉ ተከሳሽ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ
በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የቆቦ ከተማ ኗሪ ወጣት ፈንታው አድሴ የተባለ ግለሰብ እድሜያቸው ከ5አመት እስከ 9 አመት ዘጠኝ ህፃናትን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሲሆነ
የቆቦ ከተማ አስ/ር ፓሊስ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል ምርመራውን በሰዉና በህክምና ማስረጃ በማጠናከር አጣርቶ ባቀረበው የወንጀል ምርመራ መዝገብ መሰረት የራያ ቆቦ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት የወንጀል ዓቃቤ-ህግ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(ለ) እና 640(1)(ለ) ድንጋጌዎች መሰረት እድሜያቸው
ከ5አመት እስከ 9 አመት የሆኑ ዘጠኝ ህፃናትን አስገድዶ መድፈርና ተደራራቢ ወንጀሎች በሚል ክስ በራያ ቆቦ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ዓቃቤ-ህግ እንደ ወንጀሉ ክብደት ተከራክሮ ባስረዳው መሰረት የራያ ቆቦ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀን 01/05/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ በተከሰሰበት 13ቱ ክሶች ጥፉተኛ በመባሉ እሱንም ያርማል ሌሎቹንም ያስተምራል ያለዉን በተከሳሽ ላይ የ25 ዓመት ፅኑ እስራት እና የ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ወስኖበታል።
በፍርድ ሂደቱ አስተያየታቸዉን የሰጡት የተጎጅ ቤተሰቦችም ዉሳኔዉ ማንኛም ሰዉ ወንጀል ፈፅሞ በመሰወር ከጥፋት ማምለጥ እንደማይችል የተረጋገጠበትና ማንኛዉም ግለሰብ ከወንጀል ድርጊት መታቀብ እንደሚገባዉ የሚያስተምር ፍርድ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
Via ራያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
#ዳጉ_ጆርናል