በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ዉስጥ 45 ሰዎች በፖሊዮ በሽታ መያዛቸው ተነገረ
በኢትዮጵያ ባለፋት አስራ ሁለት ወራት 45 ሰዎች በፖሊዮ በሽታ መያዛቸውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት አስታውቋል።የኢንስቲትዮቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከፓሊዮ ቫይረስ ነፃ እንድትሆን የተለያዩ ስራዎችን ስትሰራ ቆይታለች።
በዚህም በ2009 ላይ ከዋይድ ፖሊዮ ነፃ መሆኗን የሚገልፅ ሰርቲፊኬት አግኝታለች ብለዋል።ይሁን እንጂ ከ2011 ጀምሮ የፖሊዮ በሽታ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ቦታዎች ተከስቷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ባለፋት አስራ ሁለት ወራት አርባ አምስት የፖሊዮ ታማሚዎች ሪፓርት ተደርገዋል።
ከኦሮሚያ ክልል 23፣ ከአማራ 7፣ ከጋምቤላ ደግሞ 6 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።ኢንስቲትዮቱ የተለያዮ በሽታዎችን አስመልክቶ በሚደረጉ ምላሾች ዙሪያ በሳይንሳዊ መረጃ ላይ የተደገፈ ምርምሮችን ሲያከናውን መቆየቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀው የፖሊዮ በሽታን በሚመለከት በቂ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑ አስረድተዋል።
አያይዘውም በዛሬው እለት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለፖሊዮ በሽታ ምላሽ መሆን የሚችል የሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ከጤና ሚኒስቴር፣ከክልል ጤና ቢሮዎች፣ከአለምአቀፍ የፖሊዮ ማጥፋት ፕሮግራም እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከየካቲት 14 እስከ 17 2017 ድረስ በ9 ክልሎችና በአንድ ከተማ መስተዳድር የሚያከናውን ይሆናል።በዘመቻውም 18 ነጥብ 3 ሚሊዮን ህፃናትን ለመከተብ ታቅዷል።
ቅድስት ደጀኔ ከጅግጅጋ ከተማ
#ዳጉ_ጆርናል