በገዛ ልጇ ላይ ቂም በመያዝ ልጇን እና ሌሎች ግለሰቦች በምግብ የመረዘችውተከሳሽ በእስራት ተቀጣች
የእኔን ሰብል ቅድሚያ አልሰበሰብክም በማለት ልጇን እና በደቦ አብረውት የሰሩትን ግለሰቦች በአረም መድኃኒት የተመረዘ ምግብ ያበላችው ግለሰብ በእስራት ተቀጥታለች:: በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ ነዋሪ የሆነቸው ነይማ አሕመድ ልጅዋን ለብቻዋ አሣድጋ ለቁምነገር አብቅታ ትዳር አስይዛ ትኖር እንደነበር ተነግሯል። ይህ ብቸኛ ልጅዋ አባስ ጀማል የሚባል ሲሆን እናቱን በስራ ያግዝ እንደነበር ተነግሯል።
በዚህም መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ አስር ሠዓት ላይ እናት ከሚጥለዉ ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ሠብልዋ እንዲሠበሰብላት ሠው በደቦ እንዲያስተባብርላት ልጅዋን አባስ ጀማልን ትእዛዝ ትሠጠዋለች። ልጅዋም ነገ የኔ ሰብል ስለሚሠበሠብ የአንቺ ከዛ ቀጥሎ ይሠበሠባል የሚል ምላሽ ሰጥቷት እንደነበር የምርመራ መዝገቡ ያመለክታል።በልጅዋ ሐሣብ የተናደደችው እናት ለእራስዋ የምታቃቸውን ሰዋች ደቦ ስትለምን የልጅዋ ስለቀደመ ለሌላ ጊዜ የሚል መልስ በማግኘትዋ ንዴት ውስጥ እንደነበረች ተገልጿል ።
በዚህም ነይማ ቆይ የአንተ እሕል ይሠበሠባል የኔ ይበላሻል በማለት ቂም በመያዝ በነጋታው በአረም መድኃኒት የተበከለ ምሣ በአገልግል አዘጋጅታ በመሄድ ምግቡን እንዲበሉ አድርጋለችምግቡን ሣይጠራጠሩ ከበሉት ከአንድ ሠዓት በኋላ ሁሉም ወድቀው አረፋ እየደፈቁ እያለ የአካባቢ ሰው አይቶ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ይዘዋቸው ይሔዳሉ። ሆስፒታል ከደረሱት መካከል አብዲ ኡስማን ,ሙሜ ነጃሽ የተባሉት ሕይወታቸውን ሲያጡ አባስ ጀማል እና ደራርቱ አልዩ የተባሉ ሁለት ሰዎች ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።ፖሊስ የደረሠውን ጉዳት ተከትሎ ነይማን በቁጥጥር ስር ያውላል::ባደረገው ማጣራትም የአገልግል ምግቡ በከፍተኛ የዓረም መድሐኒት የተበከለ መሆኑን በምርምራ በማረጋገጥ ማስረጃ ይይዛል።
ነይማም በልጅዋ ድርጊት በመናደዷ እና በሌሎችም ቂም በመያዝ ድርጊቱን መፈፀምዋን ቃሏን ለፖሊስ ትሰጣለች። በዚሕም ፖሊስ የምርመራ መዝገቡ ተጣርቶ ለአቃቢ ሕግ ይልካል ። አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ሕግ ቁጥር 539 እና 538 በከባድ የግድያ ወንጀል እና መርዛማ ነገሮችን በምግብ ውስጥ በመቀላቀል በመስራት ወንጀል ክስ ይመሰርትባታል።
በአቃቢ ሕግ የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ነይማ አሕመድ በ 2 ሰው ግድያ ና በ2 ሰዎች አካል ማጉደል ጥፋተኛ ተብላ በ25 ዓመት እስራት እንድትቀጣ የወሠነባት መሆኑን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ከምስራቅ ሐረርጌ ዞን አቃቢ ሕግ ፅ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
በኤደን ሽመልስ
#ቢዝነስ