በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል
በኦሮሚያ ክልል ከየካቲት 24 እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ15 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣ በ14 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ12 ሰዎች ላይ ቀላል አካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በንብረት ላይ የደረሰው ውድመት በገንዘብ ሲተመን ከ150 ሺ ብር በላይ የሚገመት ሲሆን የሞት አደጋዎቹ በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች የተከሰቱ ናቸው።በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰው አደጋ ከ16 እስከ 55 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራትሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
አብዛኛዎቹ አደጋዎቹ የተከሰቱት በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሲሆን አደጋውን ያደረሱት ወንድ አሽከርካሪዎች ናቸው። የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት፣ በህዝብ ማመላለሻ ፣በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) እና በሞተር ሳይክል የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የአደጋዎቹ መንስኤዎቹ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር እና ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ የቴክኒክ ችግር ፣ለተሽከርካሪ ቅድሚያ አለመስጠት እና ርቀትን ጠብቆ አለማሽከርከር መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል::
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል