አዲስ አበባ ባለፋት ሰባት ወራት ፓርኮቿን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘች
አዲስ አበባ ባለፋት ሰባት ወራት ፓርኮቿን ከጎበኙ የተለያዩ ቱሪስቶች ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቷን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አስታውቋል።የኮርፖሬሽኑ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ባለፋት ሰባት ወራት 598 ሺህ 821 ቱሪስቶች የአዲስ አበባን ዋና ዋና ፓርኮች ጎብኝተዋል።
በ2017 በጀት አመት ሰባት ወራት ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር ገልፀው ከዚህ አኳያ ጥሩ የሚባል አፈፃፀም ተመዝግቧል።ባለፈዉ ዓመት ከተሰበሰበው በእጥፍ የሚበልጥ ገቢ ማግኘት ተችሏል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ጊዜ ውስጥ 64 ሚሊዮን 222 ሺህ 515 ብር ገቢ ተገኝቷል።በዚህም የእቅዱን 88 በመቶ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል ሲሉ አስረድተዋል።
የእንጦጦ ፓርክ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ጎብኚዎች በብዛት የሚጎበኝ እንደመሆኑ በርካታ ቁጥር ባላቸው ጎብኚዎች ከተጎበኙት ፓርኮች መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ብሄረፅጌ፣ ፒኮክ፣ ኢትዮ ኩባ የመናፈሻ ስፍራዎች በበርካታ ቱሪስቶች ከተጎበኙት መካከል ይገኙበታል።ኮርፖሬሽኑ ከከተማ ልማት ቢሮ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተጨማሪ 12 ፓርኮችን እንዲሁም በኮሪደር ልማት እየለሙ ያሉ 33 ቦታዎችን መረከቡን የገለፁት አቶ ዋለልኝ ይህም የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ ማድረጉን ተናግረዋል።
በተለይም በኮሪደር አካባቢ የተሰሩት ፓርኮች ለመኖሪያ ቦታ ቅርብ በመሆናቸው እና በውስጣቸውም የተለያዩ የአገልግሎትና የመዝናኛ ስፍራዎችን የያዙ በመሆናቸው ለጉብኝት ተመራጭ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። በቀጣይ እነዚህ ፓርኮች የጎብኚዎችን ቁጥር ይበልጥ በመሳብ የተሻለ ገቢ ማግኘት እንዲቻል ከግሉ ሴክተር ጋር በመተባበር ይህን እውን ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገልጿል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል