የሱዳን ጋዜጠኞች የፕሬስ ነፃነትን ለማፈን እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ተቃወሙ
በፖርት ሱዳን የሚገኙ ሱዳናውያን ጋዜጠኞች የሳዑዲ አረቢያ ንብረት የሆነው የአልሻርክ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሱዳን መንግስት መታገዱን ተከትሎ በፕሬስ ነፃነት ላይ እየደረሰ ያለውን አፈናና የመረጃ ተደራሽነት እያሽቆለቆለ ነው ሲሉ ተችተዋል።
የአል ሻርክ የሱዳን ቢሮ ኃላፊ ካሊድ ኦዋይስ ቅዳሜ ዕለት በተካሄደው የፕሬስ ነፃነት ሲምፖዚየም ላይ እንደተናገሩት ለባለሥልጣናቱ ጥያቄ ቢያቀርብም ለጣቢያው መደበኛ የመዘጋት ምክንያት እንዳልተነገረና የመዝጋት ውሳኔው ብቻ ለጣቢያው ኃላፊዎች በስልክ ብቻ እንደተነገራቸው ተናግረዋል።
የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ባለስልጣናት የካቲት 20 ላይ የአል-ሻርክን ተግባራት በማገድ ስርጭች እንዲያቆም አድርገዋል። እገዳው ቴሌቭዥኝ ጣቢያው በካርቱም ውስጥ ስላለው የሰራዊት ግስጋሴ የአርኤስኤፍ አስተያየትን ያካተተ ዘገባ ካሰራጨ በኋላ ነው። የውጪ የዜና ማሰራጫዎች በግጭት ውስጥ ተደጋጋሚ ችግሮች ገጥሟቸዋል። ከነዚህም መካከል በኤፕሪል 2024 አል-አራቢያን እና አል-ሃዳትን የተሰኙ ጣቢያዎች ከፍቃድ እድሳት ጋር በተገናኘ ታግደው ነበር።
የሱዳኑ የጋዜጠኞች ቡድን ሲኒዲኬትስ ኃላፊ አብደል ሞኒም አቡ ኢድሪስ፣ ይፋዊ መረጃ አለማግኘት እና ተደራሽነት ላይ ገደብ በመኖሩ አሉባልታ እና የተሳሳቱ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ እንዲስፋፉ ምክንያት ሆኗል ብለዋል። በህግ እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ የፕሬስ እና የባለስልጣናት ግንኙነት እንዲኖርም ጠይቀዋል።
የአል-አራቢያ የሱዳን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሊና ያዕቆብ አል ሻርክን የማገድ ውሳኔ ሕጋዊ መሠረት የለውም ብለዋል። የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ በሱዳን እና በሌሎች ሀገራት መካከል ተገቢ ያልሆነ ንፅፅር ማድረጋቸውንም ኃላፊዎቹን ነቅፈዋል። በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙት ጋዜጠኞች ባለሥልጣናቱ "የብሔራዊ ደህንነት" ጽንሰ-ሐሳብ ያለ ግልጽ ትርጉም እየተጠቀሙበት ነው ብለዋል። “ብሔራዊ ደኅንነት” በሚለው ላይ ትክክለኛ ትርጉም እና ስምምነት እንዲደረግ እናም ፕሬስ ለዚህ መስፈርት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል