በመቱ ከጋብቻ ውጪ የወለደቻትን ልጅ በመግደል መፀዳጃ ቤት ውስጥ የከተተችዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በኢሊባቡር ዞን መቱ ወረዳ ውስጥ ከጋብቻ ውጪ የወለደቻትን ልጅ በመግደል መፀዳጃ ቤት ውስጥ የከተተችው ግለሰብ በእስራት መቀጣቷ ተገለፀ። የኢሊባቡር ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ለማ ቦይዶ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ተከሳሽ አሚና እንድሪስ የተባለችው የ23 ዓመት ወጣት ሀምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ላይ ሴት ልጅ ከጋብቻ ውጪ የተገላገለች ሲሆን ወዲያውኑ የወለደቻትን ልጅ መፀዳጃ ቤት ውስጥ እንደከተተቻች በማስረጃ ተረጋግጧል::
ተከሳሿ ሳታውቅ ከጋብቻ ውጪ አርግዛ ሴት ልጅ በሰላም ከተገላገለች በኋላ ከጎረቤቷ ባለው መፀዳጃ ቤት ውስጥ በህይወት ያለችውን ልጅ በመክተት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓ ተረጋግጧል። በመፀዳጃ ቤት ውስጥ የተለየ የደም ምልክት የተመለከቱት የቤቱ ባለቤቶች ጉዳዩ እንዲጣራ ለፖሊስ በማመልከታቸው ፖሊስ ባደረገው ማጣራት እና ክትትል ተከሳሿ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዉላለች፡፡
ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላትን ተከሳሽ ከጋብቻ ውጪ በመውለዷ የወላጆቿን እና የአካባቢውን ሰዎች ተፅዕኖ በመፍራት የወለደቻትን ሴት ልጅ ከነ ህይወቷ በመፀዳጃ ቤት ውስጥና መክተቷን ለፖሊስ በሰጠችው ቃል ማረጋገጥም ተችሏል። ፖሊስ አስፈላጊ የተባለውን ምርመራ ሂደት በበቂ ማስረጃ በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ልኳል።
አቃቤህግም ከፖሊስ የተላከለትን የምርመራ መዝገብ በወንጀል ህግ ቁጥር 544 ንዑስ አንቀፅ 2 ልጅን አስቦ ወይም በቸልተኛነት በመግደል ወንጀል ክስ መስርቷል። የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የኢሊባቡር ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ተከሳሿ በአቃቤ ህግ የተመሠረተውን ክስ ማስተባበል ባለመቻሏ እና ጥፋተኛነቷ ሙሉ በሙሉ በመረጋገጡ አሚና እንድሪስ በዘጠኝ አመት እስራት እንድትቀጣ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዉሳኔ ማሳለፉን ምክትል ኢንስፔክተር ለማ ቦይዶ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል፡፡
በሰመኃር አለባቸዉ
#ዳጉ_ጆርናል