TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

3 Oct, 17:10

Open in Telegram Share Report

ታዋቂው አሜሪካዊ ዩቲዩበር አይሾውስፒድ በዝና ማማ ላይ ሆኖ ስለሚሰማው ጥልቅ የብቸኝነት ስሜት ይፋ አድርጓል

ገና በ17 ዓመቱ የሚሊዮን ዶላር ባለቤት መሆን የቻለውና በአሁኑ ወቅት የ21 ዓመት ወጣት የሆነው ዳረን ዋትኪንስ ወይም በዓለም አቀፍ ቅፅል ስሙ አይሾውስፒድ፣ በዩቲዩብ ገጹ ላይ ከ62 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል።

በወር እስከ 300 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገቢ የሚያገኘው ይህ ወጣት፣ ከውጭ ለሚመለከተው ሰው ሁሉንም ነገር ያገኘ እና የተሟላ ህይወት የሚኖር ይመስላል።ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው።

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስሙን እየጠሩ ቢጮሁም፣ ወጣቱ ዩቲዩበር አሁንም በውስጡ ጥልቅ ብቸኝነት እንደሚሰማው በቁጭት ይገልጻል። እሱ እንደሚለው፣ በብዙኃኑ ዘንድ መታወቅና በእውነተኛ ማንነት መታወቅ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ።ቀኑን ሙሉ በሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ በስሜት ሲያጅቡትና ስሙን ሲጠሩ ቢውሉም፣ በመጨረሻ ወደ ሆቴል ክፍሉ ሲመለስ የሚጠብቀው ፍጹም ጸጥታ ይበልጥ ስሜቱን እንደሚጎዳው ተናግሯል።

ይህንን የብቸኝነት ስሜት ለመቋቋምም፣ ወጣቱ ዩቲዩበር እውነተኛ ማንነቱን ለመመለስ ቀላል የዕለት ተዕለት ተግባራት ዘወር ማለትን መርጧል። ከእነዚህም ውስጥ ስፖርታዊ ልምምዶችን ማዘውተር፣ ፒያኖ መማር እና ታዋቂ ከመሆኑ በፊት ከሚያውቁት ከእናቱ፣ አባቱ እና ወንድሙ ጋር ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ በዋናነት ይጠቀሳሉ።

የአይሾውስፒድ የህይወት ተሞክሮ አንድ ትልቅ ማህበራዊ እውነታን ለዓለም ማሳየቱን ዳጉ ጆርናል ታዝቧ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስምህን እያወቁት፣ ነገር ግን እውነተኛ ማንነትህን የሚረዳህ እና የምትግባባው ሰው ልታጣ ትችላለህ። በዝና ማማ ላይ መሆን ብዙ ተመልካችን ቢያመጣም፣ እውነተኛ የልብ ጓደኛ ማግኘት የሚቻልባቸውን ሰዎች ቁጥር ግን እጅግ ያሳንሰዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

7.4k 0 13 76
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot