♡ ወንድ ልጅ ተሰጠን ♡
ወንድ ልጅ ተሠጠን ሕፃን ተወለደ
በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ/2/
ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ የተባለው አዳም
ይኸው ተወለደ ኪዳኑን አረሳም
በሞት ጥላ ላለን ጨለማን አራቀ
አማናዊው ፀሀይ ከድንግል ሠረቀ
ተመኝቶ ነበር ሙሴ ገፁን ሊያየው
አይተህኝ አትቆምም ብሎ ከለከለው
እርሱ ጀርባውን ሲያይ አዘልሽው በጀርባሽ
ከሁሉ መረጠሽ በልጁ ፊት በራሽ
ፊታቸውን ጋርደው መላእክት ሲቆሙ
እናቱ ነሽና ክንድሽ ላይ ነው ፍሙ
ይህ እሳት ወረደ ቤተልሔም ግርግም
በእጆችሽ ዳሰስነው አላቃጠለንም
በአባቱ እቅፍ ያለው እስከሚተርከው
አንድስ እንኳን የለም እግዚአብሔርን ያየው
ቢለንም ዮሐንስ በቃለ ወንጌሉ
አየነው በአንች እቅፍ በተለየ አካሉ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈