ህይወቴ የተቀየረው ይህን ስገነዘብ ነው!
* ሰዎች ሆን ብለው ሊጎዱኝ አይሞክሩም - እነሱ በሚያውቁት መንገድ እራሳቸውን ከጉዳት ለመጠበቅ እየሞከሩ ነው።
* ፍቅር ከቃላት በዘለሉ ቋንቋዎች ሊገለጽ ይችላል፤ እናም እነዚህ ቋንቋዎች ልክ እንደ ቃላት ተቀባይነት አላቸው።
* እሴቶቻችን፣ ሀሳቦቻችን እና ድርጊቶቻችን ሲጣጣሙ አስማት ይፈጠራል (ይህ ታማኝነት ነው!)።
* በሌሎች ላይ ያለኝ ፍርድ፣ እኔ እራሴን መፍረዴን የምቀጥልባቸውን መንገዶች በቀጥታ ያንፀባርቃል።
* ለሌሎች ያለኝ ተቀባይነት፣ ለእራሴ ያለኝን ተቀባይነት በቀጥታ ያንፀባርቃል።
* ይህ የኔ ህይወት ነው - የምሰጠውን ትርጉም፣ የምፅፈውን ታሪክ፣ የምመርጠውን አላማ የምወስነው እኔ ነኝ።