#ፈጣሪ በአንድም በሌላም ይናገራል"
ከስራ መውጫ ሰአት ላይ ነው።በመኪናዬ ወደ ቤት እየሄድኩ አንድ የሀይማኖት አባት ቆመው ታክሲ ሲጠብቁ አየኋቸው፡፡
ያው አባት ስለሆኑ ቆም ብዬ ግቡ ልሸኞት አልኳቸው፡፡ደስ እያላቸው እየመረቁኝ ገቡ፡፡
"ለምን ልትሸኘኝ ወደድህ?'' አሉኝ ወደ እኔ እያዩ።
"በረከት ባገኝ ብዬ ነው" አልኳቸው፡፡
መልሰው እንዲ አሉኝ "ምትረዳው ሰው አይነት አይደለም የሚያስባርክህ።
ሰውን መርዳት ነው በረከቱ ወጣትም፣ሴትም፣ አካል ጉዳተኛም፣አዛውንትም፣አንደ እኔ የሀይማኖት አባትም ቢሆኑ ብትረዳው ብታግዘው ትባረክበታለህ ብለው ገሰፁኝ።
"እሺ አባቴ "ብዬ ዝም አልኩ፡፡
"እስኪ ትንሽ ልበልህ' አሉኝ።
"እሺ አባቴ ደስ ይለኛል"አልኳቸው፡፡
ተገኝቶ ነው!
"ዛሬ ሁለት ነገር ነው ለምዕመናን አስተምሬ የመጣሁት።
ስለፀሎት እና ስለአስራት'' አሉኝ እና ....
"ቁርስ በልተሀል?' አሉኝ ድንገት
"አዎን እረ ምሳም በልቻለው'' አልኳቸው፡፡
"ፀልየህ ነበር? "አሉኝ።
አፍሬ ዝም አልኩ
"ሰው ሲገባ ሲወጣ ምንም ነገር ለመጀመር ሲያስብ መጀመሪያ መፀለይ አለበት።አንተ ብትፈቅድ አንተ ብትወድ ብለህ ፀልይ።
አንተ ቅደም ከፊቴ ብለህ ውጣ ከፊትህ ይቀድማል
እንቅፋቶችህን እያነሳ በሰላም አውሎ ያስገባሀል።"
"እሺ አባ"ብዬ ዝም አልኩ፡
አዋ!ሰራዬን አውቀዋለው በፀብ በንጭንጭ የጀመርኩት ቀን ይበዛል በቤቴ፣በስራ ቦታዬ፣በመንገዴ ሁሉ
"ኡፋ፣ኤጭ የበዛበት ነው አውቀዋለው።
"ሁለተኛው አስራት ነው" ብለው ከሀሳብ መለሱኝ።
"አስራት ታወጣለህ?"አሉኝ።
ምንድነው አስራት?
ከምኑም የለሁበት እኮ የስም ክርስትያን ፀሎት
የሌለበት፣ማመስገን የሌለበት፣ መባ፣አስራት የሌለበት ዝም ብሎ ክርስትና።
"አስራት አውጣ ልጄ ከምታገኘው 10 ላይ 1ዱ የእግዛብሄር ነው፡፡አንድም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ መጠበቅ ነው።ሁለትም ትባረክበታለህም ታተርፋበታለህም።ወጣቱ ከደሞዙ አስራት
ማውጣት ከብዶት የ7,000-17,000 ብር ስልክ ገዝቶ በሳምንቱ 'ተሰረኩ ብሎ ሲያብድ እናየዋለን" አሉኝ።
ብዙ አሉኝ በጣም ብዙ.....
እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገራል። እኔንም ተናገረኝ ተመለስ አለኝ።እኔስ ምኔ ሞኝ ነው ተመለስኳ።
አሁን የሁሉ ነገሬ መጀመሪያ ፀሎት ነው፡፡ሳልፀልይ ምንም አልጀምርም ምንም፡፡ ለውጡን አይቼዋለው፡፡ከስንቱ አስመለጠኝ መሰላችው።
አስራትም እንደዛው ከደሞዜም ይሁን በአጋጣሚ ከማገኘው ብር አስራቴን አወጣለው፡፡ ከወር እስከ ወር አልበቃ እያለኝ አጥፊ የነበርኩት ሰውዬ አሁን ሳይቸግረኝ እየኖርኩ ነው፡፡
በአጋጣሚ ያገኘሁት እድሜው በ40ዎቹ አካባቢ ውስጥ ያለ ሰው ሲናገር የሰማሁት ነው፡፡
እውነት ነው 'እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገራል" ማን ነበር 'ተማሪ ካለ መምህር የትም አለ'' ያለው....
#የተካፈልኩት ታሪክ ነው !!
የነገ ሰው ይበለን
#አቤል ወርቁ
https://t.me/+0jzYL5QHqRA0OWQ0
https://t.me/+0jzYL5QHqRA0OWQ0
🖤 @yefkr_kalee 💛
ሼር 🙏