የትግስት ዋጋ
ስመጥሩ ግሪካዊ ኤዞፕ አንድ ዝነኛ ተረት አለው፡፡ በዚህ ታዋቂ ተረት ደሃ ና ሞኝ ገበሬ ገጸ ባህሪ አለ፡፡
ይህ ገበሬ ከእለታት አንድ ቀን የእለት ተእለት ስራውን አከናውኖ ወደቤቱ ሲመለስ በመኖሪያው ያልተለመደ ነገር ጠበቀው፡፡ ገበሬው ግራ ተጋባ፡፡ ገበሬውን ግርታ ውስጥ የከተተው
የገበሬው ንብረት የሆነችው ዶሮ የወርቅ እንቁላልን መጣሏ ነበር፡፡
ከዚህ ያልተለመደ ክስተት በኋላ ገበሬው እንቁላሉ የእውነት መሆኑን ሊያጣራ የተለያዩ መንገዶችን ቢሞክር እንቁላሉ እውነተኛ ወርቅ ሆኖ አገኘው፡፡ ይሄኔ ደስታውን ይበልጥ ከፍ ለማድረግ የወርቅ እንቁላሉን በውድ ዋጋ ሸጠወ፡፡
በቀጣይ ተከታታይ ቀናትም ዶሮዋ የወርቅ እንቁላል መጣል የቀጠለች ሲሆን ገበሬውም የወርቅ እንቁላሉን ወደገበያ እያወጣ መሸጡን ቀጠለ፡፡ ኑሮውም በከፍተኛ ፍጥነት ተለውጦ በአካባቢው ቀጭን ጌታ ለመሆን ቻለ፡፡
አንድ ቀን ታዲያ ገበሬው በየእለቱ አንድ እንቁላል ብቻ እየጠበቀ መሸጡ አዋጭ አልመስልህ አለው፡፡ ስለዚህም ዶሮዋን በማረድ በሆድዋ ያለውን እንቁላል በሙሉ ወስዶ ለመሸጥና ሐብቱንም በአንድ ጊዜ እጥፍ ሊያደርግ ወሰነና ዶሮዋን አረዳት፡፡
ይሄኔ ሰውዬው ተደናገጠ፡፡ ምክንያቱም ዶሮዌ ሆድ ውስጥ ምንም እንቁላል ሊያገኝ አልቻለም፡፡
ይህ የብዙዎቻችን ህይወት ነው፡፡
ልክ እንደገበሬው በአንድ ጊዜ የስኬት ቁንጮ ላይ መቀመጥ ስለሚያምረን የስኬት መንስኤ ሊሆነን የሚችለውን ነገር እናርዳለን፡፡
በሂደት የሚመጣን አዎንታዊ ለውጥ በትእግስት መጠበቅ ስለሚያቅተን አተርፍ ባይ አጉዳይ ህነን ባዶ እንቀራለን፡፡
እናስተውል፡፡ ለመታገስ ፈቃደኛ ካልሆንን በገዛ እጃችን ስኬታችንን አርደን ባዶ እንቀራለን፡፡
#ለኔ ና ለእናተ ምክር ነክ ፁሑፍ
https://t.me/Abalibanos333