#እንኳንም_ተሳሳትኩ
በአንድ ወቅት አንዲት #የሒሳብ_መምህርት የሚከተለውን በሰሌዳ ላይ ጻፈች፦
👉 9×1= 7
👉 9×2= 18
👉 9×3= 27
👉 9×4= 36
👉 9×5= 45
👉 9×6= 54
👉 9×7= 63
👉 9×8= 72
👉 9×9= 81
👉 9×10= 90
ጽፋ እንደጨረሰችም ወደ ተማሪዎቿ ዞራ ስትመለከት ሁሉም #እየሳቁባት ነው፣ የመጀመሪያውን #እኩልታ (equation) #ተሳስታለችና።
ይህን ጊዜ #መምህርቷ እንዲህ አለች፦ "የመጀመሪያውን #ስህተት_የጻፍኩት በዐላማ ነው፤ ከነገሩ ጠቃሚ ትምህርትን እንድትወስዱ ስለፈለኩኝ። ይኸውም፥ በውጪ ያለው ዓለም እንዴት እንደሚቀበላችሁ ታውቁ ዘንድ ነው። 9 ጊዜ #ትክክለኛ ነገር እንደጻፍኩ ማየት ትችላላችሁ ይሁንና አንዳችሁም ስለዛ አላበረታታችሁኝም፤ ነገር ግን ሁላችሁም ስለ ሠራሁት አንድ ስህተት ሳቃችሁብኝ፣ ነቀፋችሁኝ!
#ትምህርቱም_ይህ_ነው፦
የሰው ልጅ ሚሊዮን መልካም ሥራን ብትሠሩ አያበረታታችሁም ግን አንድ የሠራችሁትን ስህተት ይዞ ይነቅፋችኋል። በዚህ ግን ተስፋ ልትቆርጡ አይገባም... ሁልጊዜም ቢሆን ከሳቅና ከነቀፋ በላይ ወጥታችሁ ቁሙ፣ ጽኑ፣ በርቱም!"
#ልብ_እንበል፦
#መሳሳትን ከፈራን #መሞከር አንችልም፤ መሳሳት መጨረሻችን አይደለም የማወቅ መነሻ እንጂ። ምናልባት #የተማርነውን እንረሳ ይሆናል፣ የተሳሳትነውን ግን አንረሳም። ከብዙዎች የስንፍና ፍፁምነት ይልቅ የእኛ የመሥራት ስህተት እንደሚሻል እናስብ።
https://t.me/Abalibanos333