በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
📖መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ላንብብ📖
ክፍል ፬(4)
#የመጽሐፍ #ቅዱስ #ህዳግ #አወጣጥ
ህዳግ ማለት በቁሙ ሲፈታ እግር ወይም ግርጌ ይባላል።የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከእግርጌው የሚጻፉት ጥቅሶች ናቸው ህዳግ እሚባሉት።በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የህዳግ ዋነኛው ጠቀሜታ የንባብን፣የምስጢርን፣የምሳሌን ትስስር ከመጻሕፍቱ ጋር የምናነጻጽርበት ነው።ስለ ህዳግ በደንብ ለመረዳት ህዳግ የት እንደሚገኝ አጠቃቀሙ በምን መልኩ መተግበር እንዳለበት ማወቅ ይገባል።በነገራችን ላይ ህዳግን በእጃችን ያለ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንጂ ስልካችን ላይ ባለው application አይኖርም! እና ደሞ ህዳግን በሐዲስ ኪዳን ውስጥ እንጂ በብሉይ ኪዳን ግርጌ አይገኝም።በሐዲስ ኪዳን ማለት ከማቴዎስ ወንጌል እስከ ዮሐንስ ራዕይ ያለው ነው፤ማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ስለ ህዳግ (የመጽሐፍ ቅዱስ ግርጌ)ማሰብ ያለበት ሐዲስ ኪዳንን ሲያነብ ነው።
#ህዳግን #እንዴት #መጠቀም #ይቻላል?
ህዳግን ለመጠቀም መታወቅ ያለበት የህዳጉን ቁጥር አቀማመጥ መረዳት ነው። እስኪ ቀጥለን በምሳሌ እንመልከት
ምስሌ፦የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፬፡፩ ጀምሮ ያለውን ጥቅስ እስከ ቁጥር ፫ እናንብብ?
ማቴ ፬፡
፩ ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ
፪ ወሰደው አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ
፫በኋላ ተራበ።
(መጽሐፍ ቅዱስ ይዘን ብንከታተል ይመረጣል ንባቡን ስንመለከት ህዳግን ለማወቅ አካሄዱን ያሳየናል።
እዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጽ ግርጌ ላይ ስንመለከት
4፡1-11 ማርቆስ 1-12 የሚል እናያለን።በቅደም ተከተል ስንመለከት ማቴዎስ ምዕራፍ ፬(4)፡፩(1) የሚለው የመጽሐፍ ቅዱሱ ምዕራፍ ነው።ከምናነበው ምንባብ ጎን 1,2,3 እያለ የተጻፈው ቁጥር ንባቡ ያለበትን ቁጥር የሚያመለክት ነው።የመጽሐፍ ቅዱስን ግርጌ ስንመለከት ፬(4) የሚለው ቁጥር የመጽሐፍ ቅዱሱን ምዕራፍ ሲገልጽ ፩(1)--፲፩(11) የሚለው በምዕራፍ ፬(4) ውስጥ ያለውን ንባብ ሲያሳይ ማርቆስ ፩(1)--፲፪(12)የሚለው ደግሞ የማትዮስ ወንጌል ምዕራፍ ፬(4) ከቁጥር ፩(1) እስከ ፲፩(11) ድረስ ያለው ንባብ በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፩(1)ቁጥር ፲፪(12) ላይ ይገኛል ማለቱ ነው። በዚህ ምሳሌ መሰረት ሐዲስ ኪዳን ውስጥ ባሉ ምዕራፎች ሁሉ ህዳግን የመጠቀም እውቀትን ማዳበር ይቻላል።መጽሐፍ ቅዱሱን እያያችሁት ካልሞከራችሁ ቲኒሽ ግራ ያጋባል።
በቀጣይ
📖የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም
📖የመጽሐፍ ቅዱስ ዘይቤና
📖መጽሐፍ ቅዱስን በጊዜና በሰዓት ከፋፍሎ የማንበብን ስልት እናያለን
ይቀጥላል https://t.me/Abalibanose333